Article text
፩/ በዚህ ሕግ መሰረት ማህበሩ እንዱፇርስ በማህበሩ
የተወሰነ እንደሆነ የመፍረሱ ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን
ጀምሮ በሃያ አንድ ቀናት ውስጥ ማህበሩ
እንዱፇርስ ስለመወሰኑ ሰፉ ስርጭት ባለው ጋዜጣና
በማህበሩ ድረ ገጽ በይፊ መገለጽ አለበት፤
ማስታወቂያውም “በመጣራት ላይ ያለ” የሚል
ሐረግ ተጨምሮበት የማህበሩን ስም፣ የዋና ገንዘቡን
መጠን፣ የፇረሰበትን ምክንያት፣ የሑሳብ አጣሪውን
ስምና አድራሻ እንዱሁም የሥልጣን ወሰን መያዝ
አለበት።
፪/ ማህበሩ እንዱፇርስ የተሰጠው ውሳኔ እና በውሳኔው
መሰረት ሑሳብ አጣሪ መሾሙን የሚያመለክቱ
ሰነድች በማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጥ
እንዱሁም በንግድ መዝገብ መመዝገብ አለባቸው።