Article text
፩/ የሙያ አገልግልትን ሳይጨምር የዓይነት መዋጮ
የከፇለ ሸሪክ ያለበት ዋስትና በፍትሐ ብሕር ሕጉ
የሽያጭ ውል ክፍል ስለሻጭ ግዳታ በተደነገገው
መሰረት ይሆናል።
፪/ የተከፇለው መዋጮ በንብረት የመጠቀም መብት
ብቻ ከሆነ መዋጮውን የከፇለው ሸሪክ ያለበት
ዋስትና በፍትሐ ብሕር ሕጉ የኪራይ ውል ክፍል
የአከራይን ግዳታ በሚመለከቱት ድንጋጌዎች
መሰረት ይሆናል።
፫/ የተደረገው መዋጮ ገንዘብ የመቀበል መብት ከሆነ
መዋጮውን ያደረገው ሸሪክ ያለበት ዋስትና
በፍትሐ ብሕር ሕጉ የብድር ውል ክፍል
የተበዲሪን ግዳታ በሚመለከቱ ድንጋጌዎች
መሰረት ይመራል።