Article text
፩/ የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ተብልም ቢሆን በእናት
ኩባንያው በተሰጡ ትዕዛዞች የተመራ ተቀጥላ ኩባንያ
በራሱ ሀብት ወይም አቅም ከተጋረጠበት የመፍረስ
ወይም የንብረት መጣራት አደጋ መውጣት
እንደማይችል ከታመነ ፣እናት ኩባንያው ይህ
ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በተቻለ ፍጥነት መፍትሄ
መሆን የሚችል መሰረታዊ የመዋቅር ለውጥ
በተቀጥላ ኩባንያው ላይ ማካሄድ ወይም የኩባንያው
ንብረት እንዱጣራ ሂደቱን መጀመር ይኖርበታል።
፪/ እናት ኩባንያው የዚህን አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተላለፇ እንደሆነ የተገለጸው አደጋ ከተከሰተበት
ጊዜ በኋላ ለመነጩ እና ላልተከፇለ የተቀጥላ
ኩባንያው ዕዲዎች ተጠያቂ ነው።
፫/ እናት ኩባንያው ተቀጥላውን የመራው ተቀጥላውን
በሚጎዲ እና የቡድኑን ጥቅም በሚጻረር አኳኋን
፬፻፲፭
416 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ከሆነ ጉዲት ባደረሰው ትዕዛዝ ምክንያት ተቀጥላው
ለገባበት ያልተከፇለ የተቀጥላው ዕዲ በሙለ ተጠያቂ
ይሆናል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) እና
(፫) መሰረት
የካሣ መብት ጥያቄ የሚቀርበው በተቀጥላ ኩባንያው
ሑሣብ አጣሪ ወይም በንብረት ጠባቂ ብቻ ነው፤
ከተቀጥላው ኩባንያ ዕዲ ከአስር በመቶ ያላነሰ ዕዲ
የያዙ ባለገንዘቦች ጥያቄ ያቀረቡለት እንደሆነ
የኩባንያውን ሑሣብ አጣሪ ወይም እንደነገሩ ሁኔታ
ንብረት ጠባቂው ይህንን የመብት ጥያቄ ማቅረብ
አለበት።