Article text
ገንዘብን ስለማሳደግ
በዚህ ሕግ አንቀፅ ፬፻፴፬ ንዐስ አንቀጽ
(፪) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩን
መጠባበቂያ ገንዘብ በሙለ ወይም በከፉል ወደ ዋና
ገንዘብ በማዛወር የማህበሩን ዋና ገንዘብ ማሳደግ
ይችላል፤ ሆኖም በሕግ የተወሰነው የመጠባበቂያ ገንዘብ
ወደ ማህበሩ ዋና ገንዘብ እንዱገባ ከተደረገ የቀድሞው
በሕግ የተወሰነው መጠባበቂያ ገንዘብ እንደገና እስኪሟላ
ድረስ ለባለአክሲዮኖች ማንኛውንም ዓይነት ክፍፍል
ማድረግ አይቻልም።