Article text
፩/ አንድ የንግድ መደብር በአንድ ዋና የንግድ
መሥሪያ ቤት የተወሰነ ለመሆን ይችላል።
እንዱሁም የዋናው መሥሪያ ቤቱ አካል እንደሆኑ
የሚቆጠሩ የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ወይም
የወኪል ጽሕፇት ቤቶች ሉኖሩት ይችላል።
፪/ የንግድ መደብሩ ዋና መሥሪያ ቤት ሳይሸጥ
ወይም ሳይከራይ አንድ ቅርንጫፍ ወይም ወኪል
ጽሕፇት ቤት የተሸጠ ወይም የተከራየ እንደሆነ
እንደ ንግድ መደብር ሽያጭ ወይም ኪራይ
ይቆጠራል።