Article text
፩/ የጉባዔዎች ቃለ-ጉባዔ በጽሁፍ መዘጋጀትና በጉባዔው
በአካል በተገኙ ባለአክሲዮኖች መፇረም አለበት።
፪/ የጉባዔዎቹ ቃለ ጉባዔ በተለይ ከዚህ በታች
የተመለከቱትን ጉዲዮች መያዝ አለበት፡ሀ) የጉባዔውን ጥሪ አደራረግ፤
ለ) የስብሰባውን ቦታና ቀን፤
ሐ) አጀንዲዎችን፤
መ) ቦርድ ካለ በጉባዔው የተገኙ የቦርድ አባላትን
ስም፤
ሰ) በስብሰባው ላይ የተገኙ ባለአክሲዮኖች ብዛትና
የምልዓተ ጉባዔውን ቁጥር፤
ረ) ለጉባዔው የቀረቡ ሰነድች፤
ሰ) የውይይቱን አጭር ማጠቃለያ፤
፫፻፹፩
382 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሸ) የተሰጡት ድምፆች ውጤት፤ እና
ቀ) ጉባዔው ያሳለፊቸውን ውሳኔዎች።
፫/ ምልዓተ ጉባዔው ባለመሟላቱ ምክንያት ጉባዔው
ለመሰብሰብ ሳይችል የቀረ እንደሆነ የጉባዔው
ሰብሳቢ ይኸው በቃለ ጉባዔ እንዱያዝ ያደርጋል።