Article text
፩/ አንድ የንግድ ሰራተኛ ስለ ራሱም ሆነ ስለ
ሦስተኛ ወገን ሆኖ እሱን የቀጠረው ነጋዳ
ከሚሰራው የንግድ ሥራ ጋር ተመሳሳይ የሆነ
ላላ የንግድ ሥራ ለመሥራት አይፇቀድለትም።
፪/ ሰራተኛው በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገውን ክልከላ ጥሶ በተገኘ ጊዜ ቀጣሪው
ኪሣራ መጠየቅ ይችላል፣ የሥራውንም ውል
ለመሰረዝ ወይም ውለን አላድስም ለማለትም በቂ
ምክንያት ይሆናል።
፫/ በፍትሐ ብሕር ሕግ ቁጥር ፪ሺ፭፻፹፱፤ ፪ሺ፭፻፺
እና ፪ሺ፭፻፺፪ በተመለከተው ሁኔታ መሰረት
ካልሆነና ነጋዳው በቂ ካሣ ለሰራተኛው ለመክፇል
ካልተስማማ በስተቀር ለንግድ ሥራ የተቀጠረው
ሰራተኛ የውለ ዘመን ካለቀ በኋላ ተወዲዲሪ
የሚሆን የንግድ ሥራ አይሰራም የሚል የውል
ቃል የሥራ ውለ ውስጥ ማስገባት አይቻልም።