Article text
፩/ ማንኛውም የአክሲዮን ማህበር አንድ ወይም ከአንድ
በላይ ነጻና ገለልተኛ የሆኑ የውጭ ኦዱተሮች እና
ተለዋጭ ኦዱተሮች ሉኖሩት ይገባል፤ ኦዱተሮችን
፪፻፵፪
243 ____________________________________________________ የንግድሕግ
እና ተለዋጭ ኦዱተሮችን የሚሾመው የማህበሩ
ጠቅላላ ጉባዔ ነው።
፪/ ከማህበሩ ዋና ገንዘብ ውስጥ ቢያንስ ሃያ በመቶ
ድርሻ ያለው ባለአክሲዮን ወይም ባለአክሲዮኖች
ራሳቸው የመረጡትን የውጭ ኦዱተር መሾም
ይችላለ።
፫/ በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ኦዱተር
መሆን ይችላል፤
፬/ የመጀመሪያዎቹ ኦዱተሮች በፇራሚዎች ጉባዔ፤
ቀጣዮቹ ደግሞ በጠቅላላ ጉባዔ ይመረጣለ።