Article text
፩/ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፫፻፷፮ ንዐስ አንቀጽ
(፩) እና
(፪) መሰረት ፍርድ ቤት ወይም የሚመለከተው
የመንግስት አካል ጉባዔ ስለሚጠራበት ሁኔታ
የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የጉባዔውን አጀንዲ
የሚያዘጋጀው ጥሪ አድራጊው ነው።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተመለከተው
ቢኖርም ከማህበሩ ዋና ገንዘብ አምስት በመቶ ድርሻ
ያላቸው ባለአክሲዮኖች ተጨማሪ አጀንዲ
እንዱያዝላቸው የማድረግ መብት አላቸው፤
ጥያቄያቸውን በተቻለ መጠን የስብሰባ ጥሪ ከመደረጉ
በፉት ካልሆነም በአንቀጽ ፫፻፸ መሰረት የስብሰባ
ጥሪ በተደረገ በሦስት ቀናት ውስጥ ስብሰባውን
ለጠራው አካል በጽሁፍ ማቅረብ አለባቸው።
፪፻፷፫
264 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ በሕግ ወይም በማህበሩ የመመሰረቻ ጽሁፍ ተቃራኒ
ድንጋጌ ከላለ በስተቀር በአጀንዲው ውስጥ
ያልተካተተ ማንኛውም ጉዲይ በጉባዔው ውይይት
ሉደረግበት አይችልም፤ በአጀንዲነት ባይያዝም
ጉባዔው ዲይሬክተሮችን ለመሾምና ለመሻር
ይችላል።
፬/ ምልዓተ ጉባዔ ባለመሟላቱ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፫፻፷፰
እና ፫፻፷፱ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት
በተከታታይ በሚደረጉ የስብሰባ ጥሪዎች መነሻነት
የተሰበሰቡ ጉባዔዎች ለመወያየት የሚችለት
ለመጀመሪያው ጉባዔ በተያዘው አጀንዲ ላይ ብቻ ነው።