Article text
የመውሰድ መብት
፪፻፷፱
270 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ ማንኛውም ባለአክሲዮን ከዚህ ቀጥል
የተመለከቱትንና በማህበሩ ጽህፇት ቤት የሚገኙትን
ሰነድች በማንኛውም ጊዜ የማየት እና ቅጂዎችን
የመውሰድ መብት አለው፡ሀ) የማህበሩን የሑሳብ ሚዛን፣ የትርፍና ኪሳራ
መግለጫ እንዱሁም የንብረት ዝርዝር መዝገብ፤
ለ) ባለፈት የመጨረሻ ሦስት ተከታታይ ዓመታት
በዲሬክተሮች ቦርድና በኦዱተሮች ለጠቅላላ
ጉባዔዎች የቀረቡ ሪፖርቶችን፤
ሐ) የጉባዔዎችን ቃለ ጉባዔና በጉባዔው የተሳተፈ
ባለአክሲዮኖችን መመዝገቢያ ሰነድ፤
መ) ለጉባዔ የሚቀርበውን የውሳኔ ሀሳብ፤
ሰ) በዚህ ሕግ አንቀጽ ፫፻፲፩ ሥር የተመለከተውን
ለማህበሩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች መዝገብ፤
ረ) በበጀት ዓመቱ በማህበሩ ውስጥ ከፍተኛ ክፍያ
ይከፇለው የነበረውን ሰራተኛ ስምና
የተከፇለውን ጠቅላላ ክፍያ መጠን
የሚያሳየውን ሰነድ፤
፪፻፸
271 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሸ) የማህበሩን ባለአክሲዮኖች ዝርዝር የያዘውን
ሰነድ።
፪/ ማንኛውም ባለአክሲዮን በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተመለከቱትን ሰነድች ለማየት ወይም ቅጂ
ለመውሰድ ያቀረበው ጥያቄ በማህበሩ ተቀባይነት
ካላገኘ ለንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ወይም
አግባብ ላለው ላላ የመንግስት አካል በማመልከት
ሰነድቹን የማየት እና ቅጅ የመውሰድ መብት
አለው።
፫/ ያልተከፊፇለ አክሲዮኖችን በጋራ የያዙ
ባለአክሲዮኖችና አክሲዮኖችን በአላባ ወይም በመያዣ
የተቀበለ ገንዘብ ጠያቂዎች በዚህ አንቀጽ
የተመለከቱ የማህበሩን ሰነድች ቅጅ የማግኘት
መብት አላቸው።