Article text
፩/ ማንኛውም ባለአክሲዮን ስለራሱ ወይም ሦስተኛ
ወገንን ወክል ከማህበሩ ጋር የጥቅም ግጭት
በሚያስነሱ ጉዲዮች ላይ ድምፅ መስጠት አይችልም።
፪/ በተለይም የዲይሬክተሮች ቦርድ አባላት ባለአክሲዮን
ቢሆኑም የራሳቸውን ሀላፉነት፣ ተጠያቂነት
እንዱሁም በማህበሩ እና በራሳቸው ጥቅም መካከል
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግጭት በሚያስነሱ
ጉዲዮች ላይ ድምፅ መስጠት አይችለም።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) እና
(፪) መሰረት
ድምፅ የመስጠት መብት የማያሰጡ አክሲዮኖችም
ቢሆኑ የጉባዔውን ምልዓተ ጉባዔ መሟላት
አለመሟላቱን ለመወሰን ቁጥር ውስጥ ይገባለ።
፪፻፸፬
275 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) እና
(፪) የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላላፍ ድምፅ
ከመስጠት መቆጠብ የነበረባቸው ባለአክሲዮኖች
ድምፅ በመስጠታቸው ምክንያት የማህበሩን ጥቅም
የሚጻረር ውሳኔ ከተላለፇ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፫፻፺፩
መሰረት ውሳኔውን መቃወም ይቻላል።