Article text
የሞያ ሥራቸው አድርገው ጥቅም ለማግኘት ሲለ
ከዚህ ቀጥል የተዘረዘሩትን ሥራዎች ወይም
ላልች ተመሳሳይ ሥራዎችን የሚሰሩ ሰዎች
ነጋዳዎች ናቸው፡፩/ የሚንቀሳቀሱ ወይም የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን
ገዝተው ባለበት ሁኔታ ወይም ቀያይረው
ወይም አሻሽለው መልሰው በጅምላ ወይም
በችርቻሮ፣ በሀገር ውስጥ ወይም እንደአግባብነቱ
በውጪ ሀገር የሚሸጡ፤
፪/ ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን
ገዝተው የሚያከራዩ፤
፫/ በሕግ ለንግድ ዓላማ እንዱውል በተሰጠ መሬት
ላይ ባለመብት በመሆን የእርሻና የደን ልማት
ሥራ የሚሰሩ፤
፬/ በሕግ የገጠር መሬት ለመጠቀም ባለመብት ከሆኑ
ሰዎች ውጪ ያለ ላልች ሰዎች አነስተኛ
ከሆነው መጠን በላይ እንስሳትን የማርባት ሥራ
፫
4 ____________________________________________________ የንግድሕግ
እና ከእንስሳት የሚገኙ ምርቶችን የማምረት
ሥራ የሚሰሩ፤
፭/ አነስተኛ ከሆነው መጠን በላይ ዓሣ የሚያጠምደ
እና የሚያረቡ፤
፮/ በፍትሐ ብሕር ሕጉም ሆነ በላልች አግባብነት
ባላቸው ሕጎች መሰረት የዕቃ ማከማቸት
አገልግልት የሚሰጡ፤
፯/ የዕደ-ጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው መጠን በላይ
በሆነ መንገድ የማዕድን፣ የነዲጅ ዘይት ወይንም
የጋዝ ፍለጋ ሥራ የሚሰሩ፣ የሚቆፍሩ ወይም
የሚያወጡና ለእነዚሁ ደጋፉ አገልግልቶች
የሚሰጡ፤
፰/ የዕደ-ጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው መጠን በላይ
በሆነ አኳኋን ለህንፃ፣ ለመንገድም ሆነ ለላልች
ዓይነት ግንባታ ሥራዎች አገልግልት የሚውል
የድንጋይ ማውጣት እና መፍለጥ ሥራዎችን
የሚሰሩ፤
፱/ የዕደ-ጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው መጠን በላይ
በሆነ መንገድ የጨው ማዕድንን የሚያወጡ፤
፲/ የምግብ ዕቃዎችን፣ በተፇጥሮ የሚገኙም ሆነ
ላልች ጥሬ ዕቃዎችንና በግማሽ የተሰሩ
፬
5 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ዕቃዎችን ጨምሮ ከማንኛውን ዓይነት ግዙፍነት
ካላቸው ተንቀሳቃሽ ነገሮች ላልች ዓይነቶች
ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ዕቃዎችን የዕደጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው በላይ አድርገው
የሚያመርቱ፣ የሚለዋዉጡ፣ የሚቀይሩና፣
እነዚህን የሚጠግኑ፤
፲፩/ የዕደ-ጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው መጠን በላይ በሆነ
አኳኋን ቤትን፣ ህንፃን፣ መንገድንና ማንኛውንም
ላላ ዓይነት የግንባታ ሥራና የግንባታ ሥራዎች
ንዐሳን ክፍልችን የመሥራት፣ የመጠገን፤
የማፅዲት ሥራ የሚሰሩ፤
፲፪/ የዕደ-ጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው መጠን በላይ በሆነ
አኳኋን በልላ ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ
የመደልደል፣ የመደቅደቅ፣ የውሃ መውረጃ ቦዮች
የመሰንጠቅ ሥራ የሚሰሩ፤
፲፫/ ሰዎችን፣ እቃዎችን፣ እንደ ፖስታ ባለ የተያዙ
መልዕክቶችን ጨምሮ የዕደ-ጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው
መጠን በላይ በሆነ አኳኋን ማንኛውንም ዓይነት
የማጓጓዝ፣ ዕቃዎችን የማሸግና ከዚሁ ጋር የተያያዙ
ሥራዎችን የሚሰሩ፣
፭
6 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፲፬/ ውሃን በተለያየ መንገድ የማቆር እና የማሰራጨት
ሥራዎች፤
፲፭/ ደረቅና ፍሳሽን ጨምሮ ማንኛውንም ቆሻሻ
የማጓጓዝ፣ የማስወገድ ወይም መልሰው ለጥቅም
እንዱውለ የማድረግ ሥራዎችን የዕደ ጥበብ
ባለሙያ ከሚሰራው በላይ በሆነ መንገድ
የሚሰሩ፤
፲፮/ ኤላክትሪክ፣ ጋዝ፣ ታፍኖ የተያዘ ንፊስ፣
የማሞቂያና የማቀዝቀዣ ሥራ የሚሰሩ፣
የሚያመነጩ፣ የሚያሰራጩ፣ የሚያከፊፍለ እና
የሚሸጡ፤
፲፯/ የዕደ-ጥበብ ባለሙያ ከሚሰራው መጠን በላይ በሆነ
መንገድ ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀሱ ነገሮችን
የመጠገን፣ የማጠብ እና የማፅዲት ሥራዎችን
የሚሰሩ፤
፲፰/ በወረቀት የሚታተሙ ማንኛውንም ዓይነት
የህትመት ሥራዎችን ማተሚያ ቤት በማቋቋም
ማተም፤ በማንኛውም መንገድ የድምፅም ሆነ
ተንቀሳቃሽ ምስልን ጨምሮ የምስል ቀረፃ ሥራ
የሚሰሩ፤
፮
7 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፲፱/ በወረቀት ህትመት፣ በፍቶግራፍ፣ በድምፅ (ኦዱዮ)
ወይንም የድምፅ እና የምስል (ኦዱዮቪዥዋል)
ቀረፃ አማካኝነት ወይም በቴላቪዥን፣ በራዱዮ፣
በኢንተርኔት ወይም ማንኛውንም ዓይነት ሥራን
ወደ ህዝብ ማቅረቢያ መንገድ በመጠቀም ሥራን
አትመው የሚያቀርቡ፤
፳/ ለህዝብ የመዝናኛ ትርዕይት አዘጋጅተው
የሚያቀርቡ እና የመጫወቻ እና የመዝናኛ
ስፍራዎችን ለህዝብ አገልግልት የሚከፍቱ፤
፳፩/ የንግድ ትርኢቶችን ወይም ከእነዚሁ ጋር
ተመሳሳይነት ያላቸውን ሥራዎች የሚሰሩ፤
፳፪/ የራዱዮ ወይም የቴላቪዥን ጣቢያ አቋቁመው
ፕሮግራሞችን የሚያሰራጩ፣
፳፫/ መረጃ ወይም ዜና እና ማንኛውንም ዓይነት ወሬ
የማስተላለፍ ሥራ የሚሰሩ፤
፳፬/ ሽቦም ሆነ ሽቦ-አልባ በሆነ መንገድ እንዱሁም
የሳተላይት እና የኢንተርኔት ቴክኖልጂበመጠቀም
ሰዎችን የማገናኘት (ኮሙኒኬሽን) ሥራዎችን
የሚሰሩ፤፳፭/ የኮምፒዩተር እና ሶፍትዌር
ቴክኖልጂዎችን በመጠቀም መረጃዎችን
፯
8 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የማስተናገድ፣ የማቀናበር፣ የማቅረብ ወይም
የማስቀመጥ ሥራዎችን ሰርተው ለህዝብ
አገልግልት በኢንተርኔት የሚያቀርቡ እና
ከእነዚሁ መረጃዎች ደምበኞቻቸው በኢንተርኔት
እንዱያገኙ ቦታና ኮምፒዩተር የሚያቀርቡ፤
፳፮/ የንግድ ባንክ፣ የኢንቨስትመንት ባንክ፣ የመድን፣
የፊይናንስ አገልግልት ሥራዎች ተብለው
የሚመደቡትን እና ከእነዚሁ ጋር ተያያዥነት
ያላቸውንና ለእነዚሁ ድጋፍ የመስጠት ሥራ
የሚሰሩ፤
፳፯/ የመኝታ ወይም የመስተንግድ አገልግልት
የመስጠት፣ የምግብ ቤት፣ ምግብ አብስል
የማቅረብ፣ የቡና ቤት፣ የመጠጥ ቤት፣ የምሽት
መዝናኛ (ክለብ) ወይም ተመሳሳይ ሥራዎችን
የሚሰሩ፤
፳፰/ ስለላልች በመሆን ስብሰባዎችን፣ ድግሶችን፣
ግብዣዎችን የሚያዘጋጁና የሚያስተባብሩ፣
ለነዚህ አገልግልት የሚውለ ቦታዎችን
የሚያስውቡ፤፳፱/ የጉዞ ወኪልነት ሥራ የሚሰሩ፣
ጉዞዎችን የሚያስተባብሩ፤
፰
9 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፴/ የውበት እና የሰውነት መጠበቂያ፣ የፀጉር
ማስተካከል፣ ማንኛውንም ዓይነት ስፖርትንና
ሰውነት ማሸትን ጨምሮ ሁለም ዓይነት
የጤንነት መጠበቂያ አገልግልቶችን የሚሰጡ፤
፴፩/ ሳይንሳዊ፣ ቴክኒካዊ ወይም ሙያዊ እውቀቶችን
በመጠቀም አነስተኛ ከሆነው መጠን በላይ በሆነ
ሁኔታ የማማከር፣ የኦዱት ወይም መሰል
የእውቀት አገልግልቶችን የሚሰጡ፤
፴፪/ አነስተኛ ከሆነው መጠን በላይ በመደራጀት
የሰዎችንም ሆነ የእንስሳትን የጤና ምርመራ እና
የህክምና አገልግልት መስጠት እንዱሁም
ጤንነትን ለመጠበቅ ወይም ለመከላከል
የሚያስችለ የምክር፣ ክትትል እና የእንክብካቤ
ሥራዎችን የሚሰሩ፤
፴፫/ አነስተኛ ከሆነው መጠን በላይ የትምህርት
አገልግልት የመስጠት፣ እውቀት የማስተላለፍ
እና ማሰራጨት ሥራዎችን የሚሰሩ፤
፴፬/ የንግድ ወኪል፣ የኮሚሽን ወኪል፣ የንግድ ደላላ፣
የአክሲዮን ደላላ በመሆን ሥራ የሚሰሩ፣
፱
10 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ማንኛውንም ዓይነት የሰዎችን የአገናኝነት ሥራ
የሚሰሩ፣
፴፭/ አነስተኛ ከሆነው መጠን በላይ የንብረትም ሆነ
የግል ደህንነትን የመጠበቅ አገልግልት የሚሰጡ፤
፴፮/ ሰነድ ማዘጋጀትን፣ ማባዛትን ጨምሮ ማንኛውንም
ዓይነት የቢሮ ሥራን የሚደግፈ አገልግልቶችን
አነስተኛ ከሆነው መጠን በላይ የሚሰጡ፤
፴፯/ የቀብር ሥራና እና ተያያዥነት ያላቸውን
ሥራዎችን የሚሰሩ።