Article text
፭፻፷፱
570 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ ክፍያዎችን ያቋረጠ ባለዕዲ አቤቱታ ሲያቀርብ
የመክሰር ሥነ ሥርዓት ይከፇታል።
፪/ ባለዕዲው በዚህ መጽሐፍ ርዕስ ሦስት መሰረት
መልሶ የማደራጀት ሥነ ሥርዓት ለመክፇት
አስቀድሞ አቤቱታ ያቀረበ ካልሆነ በስተቀር
ክፍያዎችን ያቋረጠው ባለዕዲ በጣም ቢዘገይ በአርባ
አምስት ቀናት ውስጥ የመክሰር ሥነ ሥርዓት
ለመክፇት ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ አለበት።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) ውስጥ ባለዕዲው
ያለበት ግዳታ በህብረት የሽርክና ማህበር ውስጥ
በእያንዲንደ ማህበርተኛ ላይ እንዱሁም ሁለት
ዓይነት ኃላፉነት ባለበት የሽርክና ማህበር ውስጥ
ኃላፉነታቸው ባልተወሰነ ማህበርተኞች ላይ ተፇጻሚ
ይሆናል።
፬/ የመክሰር ሥነ ሥርዓት፡ሀ) ከባለዕዲው ጋር በአንድነትና በተናጠል ኃላፉ
የሆኑ ሰዎች፤
፭፻፸
571 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ለ) በባለዕዲው ላይ ጊዜው የደረሰ እና መከፇል
ያለበት የክፍያ ጥያቄ ያላቸው አንድ ወይም
ከዚያ በላይ ገንዘብ ጠያቂዎች፤
ሐ) ከመክሰር ሥነ ሥርዓት ውጭ የባለዕዲውን
ንብረት እንዱያጣራ የተሾመ ንብረት አጣሪ፤
መ) ባለዕዲው የንግድ ሥራ ማቋረጡ ባለዕዲውን
ከሚመለከት የወንጀል ሥነ ሥርዓት ግልጽ
በሚሆንበት ጊዜ ማንኛውም ዐቃቤ ሕግ፤
አቤቱታ በሚያቀርቡበት ጊዜም እንዱሁ
ሉከፇት ይችላል።
፭/ በባለዕዲው ላይ በመካሄድ ላይ ባለ ሥነ ሥርዓት
የተነሳ ባለዕዲው ክፍያዎችን ያቋረጠ መሆኑ ግልጽ
በሚሆንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነትም
እንዱሁ የመክሰር ሥነ ሥርዓት ሉያስጀምር ይችላል፣
ባለዕዲው ክፍያዎችን ያቋረጠ መሆኑን ያረጋገጠው
ፍርድ ቤት ጉዲዩን በዚህ መጽሐፍ መሰረት
የመክሰር ፍርድ ለመስጠት ሥልጣን ወዲለው ፍርድ
ቤት ይልካል።
፭፻፸፩
572 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፮/ ባለዕዲው ከአቤቱታው በተጨማሪ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፮፻፴፯ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ውስጥ የተዘረዘሩትን
ሰነድች ማቅረብ አለበት።
፯/ ከአቤቱታቸው በተጨማሪ ገንዘብ ጠያቂዎች በዚህ
ሕግ አንቀጽ ፮፻፴፯ ንዐስ አንቀጽ
(፬) ውስጥ
የተዘረዘሩትን ሰነድች ማቅረብ አለባቸው፤ እንዱሁም
የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ተደርጎ የሚሾመውን
ሰው በተመለከተ ሀሳብ ሉያቀርቡ ይችላለ።