Article text
፩/ የመክሰር ሥነ ሥርዓት በተከፇተበት ቀን ላይ
በዓይነት በባለዕዲው ይዞታ ሥር የሆኑ ግዙፊዊ
ህልዎት ያላቸው እና የላላቸው ተንቀሳቃሽ
መብቶች፣ ዕቃዎች እና ንብረቶች ባለቤት የሆነው
ሰው በዚህ ክፍል ሰባት በተደነገጉት
መሰረት ንብረቶቹን የማስመለስ መብት አለው።
፪/ ለዚህ ክፍል ሰባት ለንብረት ማስመለስ ዓላማና
መብቶች፣ ተመላሽ የሚሆኑ ዕቃዎች እና ንብረቶች
በተለይ የሚከተለትን ያካትታለ፡ሀ) የገንዘብ ሰነድች፤
ለ) በአደራ የተቀመጡ ወይም ለሽያጭ የቀረቡ
ዕቃዎች፤
ሐ) ባለሀብትነታቸው እንደተጠበ ሆኖ የተሸጡ
ዕቃዎች፤
መ) ለባለዕዲው የተላኩ እና ባለዕዲው ወይም
ባለዕዲውን በመወከል እንዱሸጣቸው ሥልጣን
፮፻፲፩
612 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የተሰጠው ሰው በመጋዘኑ የተረከባቸው
ዕቃዎች።
፫/ በገዢው ያልተከፇለ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) ውስጥ ከተመለከቱት መብቶች፣ ዕቃዎች እና
ንብረቶች ሽያጭ የሚመነጩ ክፍያዎችን ማስመለስ
ይቻላል።