Article text
፩፻፺፮
197 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ የአክሲዮን ማህበር በባለአክሲዮኖች የሚመረጡ
ቢያንስ ሦስት ቢበዛ አስራ ሦስት ዲይሬክተሮች
ይኖሩታል፤ ከዲይሬክተሮች ቦርድ አባላት መካከል
ከሦስት ሁለት እጅ (2/3ኛ) በማህበሩ የዕለት ተዕለት
ሥራ አመራር ውስጥ የሥራ አስፇጻሚነት
(ኤክስኪዩቲቭ) ሚና የላላቸው መሆን አለባቸው።
፪/ ባለአክሲዮን ያልሆኑ ሰዎች የዲይሬክተሮች ቦርድ
አባል ሆነው ሉመረጡ ይችላለ። ሆኖም ባለአክሲዮን
ያልሆኑት የቦርድ አባላት ቁጥር ከጠቅላላው የቦርድ
አባላት ቁጥር ከአንድ ሦስተኛ መብለጥ የለበትም።
፫/ የቦርድ አባላት ትክክለኛ ቁጥር በመመስረቻ ጽሁፍ
በግልጽ ባልተመለከተ ጊዜ ቁጥራቸው በአክሲዮን
ፇራሚዎች ጉባዔ ይወሰናል።
፬/ በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ማህበር ወይም
ላላ ተቋም አስተዲዲሪ (ዲይሬክተር) ሆኖ ሉሾም
ይችላል፤ ይህ የሆነ እንደሆነ ተመራጩ በሕግ
የሰውነት መብት የተሰጠው ማህበር ለተመረጠባቸው
ዓመታት የሚያገለግል ቋሚ ተወካይ ወዱያውኑ
መመደብ አለበት፤ ቋሚ ተወካዩ የለቀቀ እንደሆነ
ወይም በልላ ማንኛውም ምክንያት ኃላፉነቱን
፩፻፺፯
198 ____________________________________________________ የንግድሕግ
መወጣት ያልቻለ እንደሆነ ምትክ ተወካይ በተቻለ
ፍጥነት መመደብ አለበት።
፭/ ቋሚ ተወካዩ በግለ የማህበሩ ዲይሬክተር አይደለም፤
ሆኖም በግለ የማህበሩ ዲይሬክተር እንደሆነ
በመቆጠር የፍትሐ ብሕር እና የወንጀል
ተጠያቂነትን ጨምሮ ለሁለም ግዳታዎች ከወከለው
በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ማህበር ጋር
በአንድነት ኃላፉ ይሆናል።