Article text
፩/ በኩባንያዎች ቡድን ውስጥ የሚገኝ እያንዲንደ የሕግ
ሰውነት ያለው አካል እና ሀብቱ ራሱን የቻለ ነው፤
ፍርድ ቤቱ በኩባንያዎች ቡድን ውስጥ የሚገኝን
አንድ የሕግ ሰውነት ያለው አካል በተመለከተ
የተከፇተን ሥነ ሥርዓት በልላ የሕግ ሰውነት
ያለው አካል ወይም የተፇጥሮ ሰው ላይ ተፇጻሚ
ሉያደርግ አይችልም።
፪/ በኩባንያዎች ቡድን ውስጥ የሚገኝን አንድ የሕግ
ሰውነት ያለው አካል የተመለከተ ሥነ ሥርዓት
በመጀመሪያ የከፇተው ፍርድ ቤት በቡድኑ ውስጥ
፬፻፷
461 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የሚገኙትን ላልች አካላት በተመለከተ ሥነ
ሥርዓት ለመክፇት የግዛት ሥልጣን አለው፤ ፍርድ
ቤቱ ቡድኑን ለሚመለከቱ ሥነ ሥርዓቶች በሙለ
አንድ መልሶ የማደራጀት ኃላፉ ወይም የከሰረውን
ሰው ንብረት ጠባቂ ሉሾም ይችላል።
፫/ በኩባንያዎች ቡድን ውስጥ የሚገኙ ሁለት ወይም
ከዚያ በላይ የሕግ ሰውነት ያላቸው አካላትን
የሚመለከቱ ሥነ ሥርዓቶች ኢትዮጵያ ውስጥ
በሚገኝ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ ፍርድ ቤቶች
የተከፇቱ ከሆነ የቡድኑን የተለያዩ አባላት
በተመለከተ መልሶ የማደራጀት ዕቅድ ለማዘጋጀት
ወይም በንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያለን ድርጅት
በመንቀሳቀስ ላይ እንዲለ እንዱሸጥ ለማመቻቸት
ፍርድ ቤቱ፣ ተቆጣጣሪዎቹ እና ጠባቂዎቹ በተቻለ
መጠን ተባብረው እና ተቀናጅተው ይሰራለ።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፫) ውስጥ
የተመለከተው ትብብር እና ቅንጅት ፍርድ ቤቱ፣
መልሶ የማደራጀት ኃላፉው እና የከሰረው ሰው
ንብረት ጠባቂ አግባብ ነው ብለው በሚያስቡት
ማንኛውም መንገድ ተግባራዊ ሉደረግ የሚችል
፬፻፷፩
462 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሲሆን በተለይም ደግሞ በሚከተለት መንገድች
ሉከናወን ይችላል፡ሀ) መልሶ የማደራጀት ኃላፉዎችን እና የከሰረውን
ሰው ንብረት ጠባቂዎችን አቀናጅቶ በመሾም፤
ለ) ማናቸውንም አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች
በመለዋወጥ፤
ሐ) የቡድኑ አባላትን ንብረቶች እና ጉዲዮች
አስተዲደር እና ቁጥጥር በማቀናጀት፤
መ) ጉዲዮች የሚሰሙበትን ሥርዓት በማቀናጀት፤
ሰ) መልሶ የማደራጀት ዓለም አቀፍ ዕቅደን
የማጽደቅ ወይም በቡድኑ ውስጥ የሚገኙ
የተለያዩ ወይም የሁለንም አካላት የንግድ
ሥራ እንቅስቃሴ በመንቀሳቀስ ላይ እንዲለ
የንግድ ሥራ የመሸጥ ሥራዎችን
በማቀናጀት።