Article text
፩/ ነጋዳዎችን የሚመለከቱ የዚህ ሕግ ማናቸውም
ድንጋጌዎች በዕደጥበብ ባለሙያዎች ላይ ተፇጻሚ
አይሆኑም፤
፪/ የዕደጥበብ ባለሙያዎች ማለት የእጅ ጥበብ
ሙያ ኖሯቸው ብቻቸውን ወይም በቤተሰብ
አባላት እየተደገፈ ከሦስት ተቀጣሪ ሰራተኞች
ወይም ተለማማጅ ሰራተኞች በላይ ሳይኖራቸው
የሚሰሯቸውን ሥራዎች ለመሥራት
ከሚያስፇልጋቸው መጠን በላይ ግብዓት ወይም
ጥሬ ዕቃ ሳያከማቹ እንደዚህ ያለውን ራሱን የቻለ
ሥራ እያከናወኑ በእጅ ሥራቸው ብቻ የሚኖሩ
ሰዎች ናቸው፤
፫/ የዕደ ጥበብ ባለሙያዎች ሥራ ሥራቸውን
በአመዛኙ በእጃቸው እየተጠቀሙ የሚሰሩ
፲፩
12 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሲሆኑ፤እንደሁኔታው በአነስተኛ መሣሪያ ወይም
ማሽን ሉጠቀሙ ይችላለ፤
፬/ የዕደ ጥበብ ባለሙያዎች ሥራን የሚመለከት
ልዩ ሕግ ሉወጣ ይችላል።