Article text
፩/ በልላ ሕግ የተደነገጉ ክልከላዎች እንደተጠበቁ ሆኖ፣
በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም በማሻሻያው
መሰረት ልዩ መብት የሚያስገኙ የተለያዩ
አክሲዮኖች እንዱወጡ ማድረግ ይቻላል።
፪/ አንድ ዓይነት መደብ ባላቸው አክሲዮኖች ላይ
የሚጻፇዉ ዋጋና ለባለአክሲዮኖች የሚያስገኙት
መብት እኩል መሆን አለበት።
፫/ ለአንድ የአክሲዮን መደብ የተሰጡ መብቶችን
መለወጥ የሚቻለው የባለ አክሲዮኖች አስቸኳይ
ጠቅላላ ጉባዔ ለውጡ እንዱደረግ በወሰነበት አኳኋን
፩፻፹፩
182 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ልዩ መብት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ልዩ ጉባዔ
ውሳኔውን ሲያጸድቅ ብቻ ነው።