Article text
፩/ ቀጥል የተመለከቱት ሰዎች በንግድ መደብር ላይ
ከሕግ የመነጨ የዋስትና መያዣ መብት አላቸው፦
ሀ) የሽያጭ ገንዘብ ሙለ በሙለ ወይም በከፉል
ያልተከፇለው የንግድ መደብር ሻጭ፤
ለ) ነጋዳው ከከሰረ ከነጋዳው ገንዘብ ጠያቂዎች፤
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ (፩)(ለ) ለተመለከተው
ከሕግ በመነጨ የዋስትና መያዣ መብት ላይ
የዚህ ሕግ ሦስተኛው መጽሐፍ ተገቢ ድንጋጌዎች
ተፇጻሚ ይሆናለ።