Article text
፩/ የአክሲዮን ማህበሩ የተቋቋመው በምንም ዓይነት
ቢሆንም በንግድ መዝገብ መግባት አለበት፤ ማህበሩ
የሕግ ሰውነት የሚያገኘው በምዝገባ ይሆናል።
፪/ በልላ ሕግ በተለየ ሁኔታ የተደነገገ ቢኖርም፤
ማህበሩን ማስመዝገብ ያለባቸው አደራጆች ወይም
እንደነገሩ ሁኔታ መስራቾች ወይም በእነዚህ
አካላት ውክልና የተሰጠው ላላ ሰው ነው።
፫/ በልላ ሕግ በተለየ ሁኔታ የተደነገገ ቢኖርም፤
ከምዝገባው ማመልከቻ ጋር በሰነድ አረጋጋጭ
የተረጋገጠ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ማህበሩ ለሕዝብ
ክፍት የሆነ እንደሆነ የማህበሩ መግለጫ፣
የዓይነት መዋጮዎች እና የምስረታ ኦዱት
ሪፖርቶች እንዱሁም የፇራሚዎች ጉባዔ ቃለጉባዔ
ተያይዞ መቅረብ አለበት።
፩፻፷፱
170 ____________________________________________________ የንግድሕግ