Article text
፩/ የዓይነት መዋጮ የከፇለ ፇራሚ የባለሙያ ግምት
ሪፖርት ማቅረብ አለበት።
፪/ የግምት ሪፖርቱ መዋጮ የተደረጉትን ንብረቶች፣
የእያንዲንደን የዋጋ ግምት እና የአገማመቱን ዘዳ
በዝርዝር መገለፅ ይኖርበታል፤ ሪፖርቱም
ከመመስረቻ ጽሁፈ ጋር መያያዝ አለበት።
፫/ በዓይነት የተከፇለው መዋጮ ግምት የማህበሩን ዋና
ገንዘብ ለማዋጣት የፇረሙት ሰዎች ጉባዔ ከመደረጉ
በፉት በአደራጆችና በምስረታ ኦዱተር መረጋገጥ
አለበት።
፬/ የሚመሰረተው ማህበር አክሲዮኑ ለህዝብ ክፍት
ያልሆነ የአክሲዮን ማህበር የሆነ እንደሆነ በዓይነት
፩፻፷፩
162 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የተከፇለው መዋጮ ግምት በማህበሩ መስራቾች
መረጋገጥ አለበት።
፭/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፫) እና
(፬) ግምቱ
የፀደቀ ቢሆንም የዲይሬክተሮች ቦርድ እና
ኦዱተሮች ማህበሩ በንግድ መዝገብ በተመዘገበ
በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የዓይነት መዋጮውን
ግምት ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለባቸው፤
እንዱሁም የተዋጣው ንብረት እንደነገሩ ሁኔታ
በማህበሩ ስም መመዝገቡንና አስፇላጊው የንብረት
ባለቤትነት ማስረጃ በማህበሩ ስም መዘጋጀቱን
ማረጋገጥ አለባቸው።
፮/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፭) መሰረት በተደረገው
ማጣራትና ምርምራ በመዋጮነት የቀረበው ንብረት
ዋጋ ግምት በአስር በመቶ እና ከዚያም በላይ አንሶ
ከተገኘ መዋጮውን ያስገባው ባለአክሲዮን ልዩነቱን
ማሟላት አለበት፤ መዋጮውን ያስገባው ባለአክሲዮን
ልዩነቱን ካላሟላ የባለአክሲዮኑ የአክሲዮን ድርሻ እና
የማህበሩ ዋና ገንዘብ በጎደለው ልክ መቀነስ አለበት።