English
Advocacy Profession Entrance
Qualification Exam Committee
1/ The Advocacy Profession Qualification
Exam Committee, herein after called the
“Exam Committee” is hereby
established by this Proclamation;
2/ The Exam Committee shall have seven
members comprised of the following
bodies which nominated by the
institutions and appionted by the
Attorney General:
a) two representatives from the office
of the Attorney General;
b) three members from Advocates’
Association;
c) one member from the Federal High
Court; and
d) one member from Addis Ababa
University School of Law.
3/ The term of a member of the Exam
Committee shall be two years and no
member shall be elected for more than
two terms;
4/ The Chairperson of the Exam Committee
shall be nominated by Advocate’s
Association;
5/ The meeting of the Exam Committee
shall be conducted as follows:
a) The Committee shall hold its
meeting at any time as may be
necessary;
b) There shall be quorum to conduct a
meeting where more than half of its
members are present; and
c) Decisions shall be passed by a
majority vote. In case of tie,
however, the Chairperson shall
have a casting vote.
አማርኛ
፩/ የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴ ከዚህ
በኋላ “የፈተና ኮሚቴ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ
አዋጅ ተቋቁሟል።
፲፫ሺ፭፻፴፱
፪/ የፈተና ኮሚቴው ከሚከተሉት አካላት
የተውጣጡ በየተቋማቱ የሚመረጡና
በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የሚሾሙ ሰባት አባላት
ይኖሩታል፡ሀ) ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት ተወካዮች፣
ለ) ከጠበቆች ማኅበር ሦስት ተወካይ፣
ሐ) ከፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንድ
ተወካይ፣
መ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሕግ ትምህርት
ቤት አንድ ተወካይ።
፫/ የአንድ የፈተና ኮሚቴ አባል የሥራ ዘመን
ሁለት ዓመት ሲሆን ከሁለት ጊዜ በላይ
በፈተና ኮሚቴ አባልነት ሊመረጥ
አይችልም።
፬/ የፈተና ኮሚቴው ሰብሳቢ በጠበቆች ማኅበር
የሚመረጥ ይሆናል።
፭/ የፈተና ኮሚቴውን ስብሰባ በተመለከተ፡ሀ) ኮሚቴው እንደ አስፈላጊነቱ በማንኛውም
ጊዜ ሊሰበስብ ይችላል፣
ለ) ከኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ
ምልዓተ-ጉባዔ ይሆናል፣ እና
ሐ) የኮሚቴው ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ
ያልፋሉ፤ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል
ከተከፈለ የሰብሳቢው ድምጽ ወሳኝነት
ይኖረዋል።
፲፫ሺ፭፻፵