English
1/ Any person who meets the requirements
of Article 6 Sub-Article
(1) of this
Proclamation and wishes to engage in
the provision of advocacy services shall
take the qualification examination for
advocacy services;
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-
Article
(1) of this Article, an Ethiopian
or a foreign national of Ethiopian
origin with first degree in law and
served as a law instructor for a
minimum of seven years in an Ethiopian
Higher Education Institution; or as a
judge, public prosecutor, as a legal
advisor or legal professional or as an
attorney in public services or public
enterprises for a minimum of five years;
or as assistant judge, as advocates’
assistant or law clerk in a law firm or
with an advocate, as well as a legal
advisor or as a professional in the field
of law or as an attorney in civil
societies, religious institutions,
international organizations, business
organizations and in other institutions
for a minimum of seven years shall be
granted advocacy license without
having to take the advocacy
examination if he applies within one
year of leaving his post;
3/ Notwithstanding the provisions of Sub-
Article
(2) of this Article, an advocate
with first degree in law and who served
as a Federal First Instance Court
Advocate for five years, may be granted
the All Federal Courts Advocacy
License without having to take the
advocacy qualification examination
leaving his advocacy service;
4/ The Attorney General shall issue an
Advocacy License to the person who is
allowed to take the license by the
Advocacy License Evaluation
Committee.
አማርኛ
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ሥር
የተደነገጉትን የሚያሟላ ማንኛውም በጥብቅና
አገልግሎት መሰማራት የሚፈልግ ሰው
የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና መውሰድ
ይኖርበታል።
‹
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
ቢኖርም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሮት
በኢትዮጵያ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት
ተቋማት ውስጥ በሕግ መምህርነት ለሰባት
ዓመት ያገለገለ፤ በዳኝነት፣ በዐቃቤ ሕግነት፣
በመንግስት መሥሪያ ቤት ወይም በመንግስት
የልማት ድርጅት ውስጥ በሕግ አማካሪነት
ወይም በሕግ ባለሙያነት ወይም በነገረ
ፈጅነት ቢያንስ ለአምስት ዓመት ያገለገለ፤
በረዳት ዳኝነት፣ በጠበቃ ወይም ጥብቅና
፲፫ሺ፬፻፺፮
ድርጅት የሕግ ጉዳይ ጸሐፊነት ወይም
የጠበቃ ረዳትነት እንዲሁም በሲቪል
ማኅበረሰብ ድርጅት፣ በሃይማኖት ተቋማት፣
በዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በንግድ
ድርጅቶችና ሌሎች ተቋማት በሕግ
አማካሪነት ወይም በሕግ ባለሙያነት ወይም
በነገረ-ፈጅነት ቢያንስ ለሰባት ዓመት ያገለገለ
ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ
ሥራውን በለቀቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ
የጥብቅና ፍቃድ ማመልከቻ ያቀረበ እንደሆነ
የጥብቅና ፍቃድ ያለፈተና ሊሰጠው
ይችላል።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ላይ
ተደነገገው ቢኖርም በፌደራል የመጀመሪያ
ደረጃ ጥብቅና ፍቃድ ለአምስት ዓመት
ያገለገለ እና በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው
ጠበቃ የጥብቅና አገልግሎት ሥራውን
ሳይተው የፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት
የጥብቅና ፍቃድ ያለፈተና ሊሰጠው
ይችላል።
፬/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ
ኮሚቴ ፍቃድ እንዲሰጠው ለወሰነለት
ባለሙያ የጥብቅና ፍቃድ ይሰጣል።
፲፫ሺ፬፻፺፯