English
1/ The members of a law firm may choose
and decide any name to be their firm’s
name.
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-
Article
(1) of this Article, the name
chosen to be the name of the law firm
may be rejected by the Attorney General
for the following reasons:
a) if it is similar with the name of
another existing law firm;
b) if the name misrepresents or
confuses clients in a way not easily
to differentiate it from another law
firm; and
c) when it is contrary to law or public
morality.
3/ To indicate the advocacy service, the
firm name shall be followed by the
words “Limited Partnership” or the
abbreviation “L.P.”
4/ All Documents issued in the name of the
law firm shall clearly contain its name
followed by “Limited Partnership”.
አማርኛ
፩/ የጥብቅና ድርጅት አባላት ማንኛውንም
ሥያሜ የጥብቅና አገልግሎት ድርጅቱ
መጠሪያ እንዲሆን መምረጥ እና መወሰን
ይችላሉ።
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ
ቢኖርም ለጥብቅና ድርጅቱ መጠሪያነት
የተመረጠው ሥም በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
በሚከተሉት ምክንያቶች ተቀባይነት
ላይኖረው የሚችለው፡ሀ) ከሌላ የጸና የጥብቅና ድርጅት ሥም ጋር
ተመሳሳይ ከሆነ፣
ለ) ደንበኞች ድርጅቱን ከሌላ የጥብቅና
ድርጅት በቀላሉ መለየት እንዳይችሉ
በሚያስችል መልኩ ሊያሳስት ወይም
ሊያደናግር የሚችል ከሆነ፣ እና
ሐ) ለሕግ ወይም ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ
ከሆነ።
፫/ የጥብቅና ድርጅት ሥም የጥብቅና ድርጅት
መሆኑን የሚያመለክትና ከሥሙ
በስተመጨረሻ “ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና
ማኅበር” ወይም (“ኃ.የተ.የሽ.ማ”) የሚል ሐረግ
ያለው መሆን አለበት።
፬/ በጥብቅና ድርጅቱ ሥም የሚወጡ ሠነዶች
በሙሉ በግልጽ ሥሙን እና “ኃላፊነቱ
የተወሰነ የሽርክና ማኅበር” የሚለውን ሐረግ
መያዝ አለባቸው።