English
1/ Notwithstanding the provisions of Article 4 Sub-Article
(2) of this Proclamation,
an Ethiopian or a foreign national of
Ethiopian origin who teaches law in law
schools of higher education institutions
and fulfills the requirements of Article 12 Sub-Article
(1) or Article 13 Sub-
Article
(1) may be granted an Advocacy
License without having to resign from
his teaching post;
2/ A law school instructor who requests for
grant of an advocacy license pursuant to
Sub-Article
(1) of this Article shall
submit an assurance issued by the law
school his advocacy service does not
affect the teaching learning process.
አማርኛ
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ሥር
የተደነገገው ቢኖርም በከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት የሕግ ትምህርት ቤቶች
የሚያስተምር ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ
ኢትዮጵያዊ የሕግ መምህር በአንቀጽ ፲፪
ንዑስ አንቀጽ
(፩) ወይም በአንቀጽ ፲፫ ንዑስ
አንቀጽ
(፩) ላይ የተጠቀሰውን ካሟላ የሕግ
መምህርነት ሙያውን መልቀቅ ሳያስፈልገው
የጥብቅና ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) መሠረት
የሕግ ትምህርት ቤት መምህር የጥብቅና
ፍቃድ እንዲሰጠው ሲያመለክት የጥብቅና
ሥራው የመማር ማስተማር ሂደቱን
የማያስተጓጉል ስለመሆኑ በሕግ ትምህርት
ቤቱ የተሰጠ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት።