English
1/ A law firm shall not be dissolved because
of the death of partners, when a partner
leaves the firm, loss of capacity of a
partner or any change that may put the
partners in trouble;
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-
Article
(1) of this Article, a law firm
may be dissolved in one of the
following grounds:
a) when the partners agree to dissolve
the law firm;
b) when a court declares the law firm
bankrupt;
c) when the advocacy licenses of all
partners are revoked; or
d) when the number of partners who
have valid advocacy license is
reduced to one and it is not possible
to increase the number of partners
who have valid advocacy license at
least to two, within six months.
3/ Notwithstanding the provision of Sub-
Article
(2) paragraph
(d) of this Article,
if the remaining partner presents his
request to the Attorney General before
the lapse of the six month period and
where the Attorney General finds it
necessary, it may allow the extension of
the six months period by three months;
4/ Unless otherwise provided in Sub-Article
(3) of this Article, the partner shall be
jointly and severally liable with the law
firm for obligation of the law firm
where he continues the operation of the
firm for more than six months after
being aware of the fact that the number
of partner of the partnership reduced to
one;
5/ A law firm, when dissolved, shall be
cancelled from the register;
‹
6/ Provisions related to the dissolution of
limited liability partnership provided in
the Commercial Code and other laws,
shall apply to govern the dissolution of
a law firm.
አማርኛ
፩/ የጥብቅና ድርጅት ህልውና በሸሪኮቹ ሞት፣
መልቀቅ፣ ችሎታ ማጣት ወይም ሸሪኮቹን
በሚያውክ ማናቸውም ለውጥ አይፈርስም።
፲፫ሺ፭፻፳፩
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ የጥብቅና ድርጅት
ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ሊፈርስ
ይችላል፡ሀ) የሽርክና ማኅበሩን ለማፍረስ ሸሪኮች
ሲስማሙ፣
ለ) የጥብቅና ድርጅቱ መክሰሩ በፍርድ ቤት
ሲታወጅ፣
ሐ) የሁሉም ሸሪኮቹ የጥብቅና ፍቃድ
ሲሰረዝ፣ ወይም
መ) የጸና የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው ሸሪኮች
ቁጥር ወደ አንድ ዝቅ ሲልና ቁጥራቸው
በጎደለ በስድስት ወራት ውስጥ የጸና
የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው ሸሪኮቹ ቁጥር
ቢያንስ ወደ ሁለት ካላደገ።
፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ፊደል-ተራ
(መ) ድንጋጌ ቢኖርም የስድስት ወራት የጊዜ
ገደብ ከማለፉ በፊት በጥብቅና ድርጅቱ
የቀረው ሸሪክ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጥያቄ
ሲያቀርብ እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጥያቄውን
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የስድስት ወራቱ
የጊዜ ገደብ በሶስት ወራት እንዲራዘም
ሊፈቅድ ይችላል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፫) በተደነገገው
መሠረት ካልሆነ በስተቀር የሸሪኮች ቁጥር
ወደ አንድ ዝቅ ያለ መሆኑን የሚያውቅ ሸሪክ
የጥብቅና ድርጅቱ በዚህ ሁኔታ ከስድስት
ወራት በላይ ሥራውን እንዲቀጥል ካደረገ
ለድርጅቱ እዳ እና ግዴታዎች ከጥብቅና
ድርጅቱ ጋር በአንድነት እና በተናጠል
ተጠያቂ ይሆናሉ።
፭/ የጥብቅና ድርጅት ሲፈርስ ከመዝገብ
ይሰረዛል።
፲፫ሺ፭፻፳፪
፮/ ኃላፊነቱ የተወሰነ ማኅበርን መፍረስ
የሚመለከቱ በንግድ ሕጉ ወይም በሌሎች
ሕጎች የተቀመጡ ድንጋጌዎች የጥብቅና
ድርጅት መፍረስን በሚመለከት ተፈጻሚ
ይሆናሉ።