English
1/ Any advocate or law firm is obliged to
make, in writing, the advocacy service
contract which he or it makes with his
client except legal advice given for a
short period of time; the Association
shall determine by Directive what
would be included in the contract of
advocacy service;
2/ The contract of the advocacy service
shall include the total amount of fee the
client pays to the advocate or law firm,
computation and time of payment and
the extent of the service to be provided;
3/ Every advocate or law firm has the
following obligations:
a) To have an office where he/it
provides the advocacy service;
b) To perform the service without using
intermediary;
c) Not to terminate the advocacy
service contract without good cause
and not to demand more payment
than the one agreed upon on the
contract of service.
4/ Notwithstanding the provision of
paragraph
(a) of Sub-Article
(3) of this
Artilcle, the license issuing authority
shall not require office to grant the
advocate license.
አማርኛ
፩/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሚሰጠው የሕግ ምክር
አገልግሎት ውጭ ከደንበኛው ጋር
የሚያደርገውን የጥብቅና አገልግሎት ውል
በጽሑፍ ማድረግ አለበት፤ የጥብቅና
አገልግሎት ውል ማካተት ስለሚገባቸው
ነገሮች ማኅበሩ በመመሪያ ይወስናል።
፪/ የጥብቅና አገልግሎት ውሉ ደንበኛው ለጠበቃው
የሚከፍለውን አጠቃላይ የገንዘብ ክፍያ፤
የአከፋፈሉን ስልት እና ጊዜ፤ ጠበቃው
በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን የጥብቅና አገልግሎት
የሚያካትት መሆን አለበት።
፲፫ሺ፭፻፪
፫/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት፡ሀ) ለጥብቅና አገልግሎት መስጫ የሚሆን
ቢሮ የማሟላት፣
ለ) የጥብቅና ሥራን በአገናኝ አማካኝነት
ያለመስራት፣ እና
ሐ) የጥብቅና ውልን ያለበቂና ሕጋዊ
ምክንያት ያለማቋረጥ እና በጥብቅና
ውሉ ከተገለጸው የክፍያ መጠን በላይ
ተጨማሪ ክፍያ ከደንበኛ ያለመጠየቅ፤
ግዴታ አለበት።
፬/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ
(፫) ፊደል-ተራ
(ሀ) ላይ የተደነገገው ቢኖርም የጥብቅና ሙያ
አገልግሎት ፍቃድ ሰጪው አካል ቢሮ
ማሟላትን እንደመስፈርት ሊጠይቅ
አይችልም።