English
1/ The main objective of a law firm is
providing advocacy service;
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-
Article
(1) of this Article, a law firm can
render services related with advocacy
service; the particulars shall be
determined by a Directive to be issued
by the Attorney General.
አማርኛ
፩/ የጥብቅና ድርጅት ዋነኛ ተግባር የጥብቅና
አገልግሎት መስጠት ነው።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ሥር
የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የጥብቅና
ድርጅት ከጥብቅና አገልግሎት ጋር
ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች አገልግሎቶች
ሊሰጥ ይችላል፤ ዝርዝር አፈጻጸሙ ይህንን
አዋጅ ለማስፈጸም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል።