English
1/ An advocate, who is a partner or
employee of a law firm, during the time
of his membership to the partnership or
employment engagement to a specific
law firm, shall be restricted to undertake
the following activities:
a) directly or indirectly, from being a
partner or employee of another law
firm;
b) from directly or indirectly assisting
or collaborating with another law
firm, unless the law firm to which he
is a partner or an employee, with the
view to discharging his assigned firm
duty, authorize him in advance to do
so;
c) from providing advocacy service in
private;
d) receiving advocacy service fee from a
client and use the money for his
personal benefit without the
knowledge and permission of the law
firm;
e) engagement in any other business,
either personally or as an employee,
that may contradict with the purpose
and activities of, and creates conflict
with the interests of, the law firm.
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-
Article
(1) of this Article, unless the
client agrees differently, activities
commenced by any partner or employed
advocate prior to engagement with the
law firm shall be completed on the basis
of prior arrangements.
አማርኛ
፩/ በጥብቅና ድርጅት ውስጥ ሸሪክ ሆኖ የሚሠራ
ማንኛውም ጠበቃ ወይም በጥብቅና ድርጅቱ
ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ሠራተኛ የሽርክና
ወይም የሥራ ቅጥር ዘመኑ ጸንቶ ባለበት ጊዜ
መሳተፍ የማይችልባቸው ተግባራት፡ሀ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሌላ የጥብቅና
ድርጀት ሸሪክ ወይም ሠራተኛ መሆን፣
ለ) በሚሠራበት የጥብቅና ድርጅት ውስጥ
የተጣለበትን ግዴታ ለመወጣት አስፈላጊ
መሆኑ በድርጅቱ ቀደም ብሎ
ካልተፈቀደ በስተቀር በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ መንገድ ሌላ የጥብቅና
ድርጅትን መርዳት ወይም መተባበር፣
ሐ) የግል የጥብቅና አገልግሎት መስጠት፤
መ) የጥብቅና ድርጅቱ ሳያውቅና ሳይፈቅድ
በራሱ ሥም የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ
ከደንበኛ መቀበልና ለግል ጥቅም
ማዋል፤
ሠ) ማንኛውንም ከጥብቅና ድርጅቱ ዓላማና
ተግባር ጋር የሚጣረስና የጥቅም ግጭት
ሊፈጥር የሚችል ሥራ በግሉም ሆነ
ተቀጥሮ መስራት።
፲፫ሺ፭፻፲፰
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
ቢኖርም ማንኛውም ጠበቃ በጥብቅና ድርጅት
ሸሪክ ወይም ተቀጣሪ ከመሆኑ በፊት የያዘው
ጉዳይ ደንበኛው በተለየ ሁኔታ ካልተስማማ
በስተቀር በተያዘበት አግባብ ፍጻሜ ያገኛል።