English
1/ The Attorney General shall, without
passing the limit each advocate should
render pro bono service in a given year,
identify and assign pro bono cases to
advocates;
2/ Each Advocate shall have the obligation,
without passing the limit of pro bono
cases in a given year, to receive cases
referred to him by the Attorney General
and render pro bono service;
3/ The Association, based on this
Proclamation and the Advocates’ Code
of Conduct, shall control and monitor
whether an advocate or a law firm has
discharged his obligation in handling of
the cases assigned to him by the
Attorney General for pro bono advocacy
service;
4/ Notwithstanding the provision of Sub-
Article
(1) of this Article, the Attorney
General, after ascertaining the accuracy
and truthfulness of the service, may
recognize the pro bono service for
which the advocate rendered for persons
in need of the pro bono service.
አማርኛ
፩/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እያንዳንዱ ጠበቃ በዓመት
መስጠት ከሚጠበቅበት የነጻ የጥብቅና
አገልግሎት መጠን ሳያልፍ በነጻ የጥብቅና
አገልግሎት ሊስተናገዱ የሚገባቸውን ጉዳዮች
እያጣራ ለጠበቆች ይመራል።
፪/ እያንዳንዱ ጠበቃ በዓመት መስጠት
ከሚጠበቅበት የነጻ የጥብቅና አገልግሎት
ግዴታ ሳያልፍ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
የሚመራለትን የነጻ ጥብቅና አገልግሎት
ተቀብሎ የመስራት ግዴታ አለበት።
፫/ ማኅበሩ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የነጻ የጥብቅና
አገልግሎት እንዲሰጥ የመራለትን ጠበቃ
ወይም የጥብቅና ድርጅት በዚህ አዋጅ እና
በጠበቆች ሥነ-ምግባር ደንብ መሠረት
መፈጸሙን መቆጣጠር እና መከታተል
አለበት።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
ቢኖርም በጠበቃው በኩል ነጻ የሕግ ድጋፍ
አገልግሎት መሰጠት ያለበት ሰው አግኝቶ
አገልግሎቱን በነጻ የሰጠ በሆነ ጊዜ ጠቅላይ
ዐቃቤ ሕግ የአገልግሎቱን ትክክለኛነትና
እውነተኛነት አረጋግጦ እውቅና ሊሰጠው
ይችላል።