ይህ አዋጅ “የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፵፱ /፪ሺ፲፫" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። ፲፫ሺ፬፻፹፩ This Proclamation can be cited as “Federal Advocacy Service Licensing and Administration Proclamation No.1249/2021”.
፩/ “ጠበቃ” ማለት የግል የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት በዚህ አዋጅ መሠረት ፍቃድ የተሰጠው ሰው ሲሆን፤ በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፰ ላይ ለተደነገገው ዓላማ በውጭ ሀገር ሕግ መሠረት የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ የተሰጠውን ሰውም ያካትታል፤ ፪/ “የጸና የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ፍቃድ” ማለት በዚህ አዋጅ የተመለከቱትን መስፈርቶች ላሟላ ሰው የሚሰጥ ፍቃድ ነው፤ ፫/ “የታክስ ክሊራንስ” ማለት አንድ የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ፍቃድ ያለው ሰው ላገኘው ገቢ ግብር ስለመክፈሉ ከግብር አስገቢው አካል የሚሰጥ ማስረጃ ነው፤ ፬/ “የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅት” ማለት የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ድርጅት ነው፤ ፭/ “የጥብቅና ሙያ አገልግሎት” ማለት የገንዘብ ክፍያ በመቀበል ወይም ወደፊት የሚገኝ ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ወይም ያለክፍያ በጠበቃ ወይም በጥብቅና ድርጅት የሚሰጥ ማንኛውም የሕግ አገልግሎት ሲሆን የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡ሀ) በሕግ ጉዳዮች ላይ ምክር መስጠት፤ ከወንጀል ጉዳዮች ውጪ የማደራደር ሥራ፣ ለ) የሕግ ሠነድ ማዘጋጀት ወይም በደንበኛው ሥም ሠነድን ማቅረብ፣ ፲፫ሺ፬፻፹፪ ሐ) በፍርድ ቤቶች፣ አስተዳደራዊ ጉባዔዎች፣ ከፊል የዳኝነት ሥልጣን ባላቸው አካላት፤ በግልግል ዳኝነት ጉባዔዎች እና በሌሎች አማራጭ የሙግት መፍቻ መድረኮች ደንበኛን ወክሎ መቅረብ እና መከራከር። ፮/ “ማኅበር” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፯ መሠረት የተቋቋመ የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ማኅበር ነው፤ ፯/ “ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፱፻፵፫/፪ሺ፰ መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነው፤ ፰/ “ደንበኛ” ማለት የጥብቅና አገልግሎት ተቀባይ ሰው ነው፤ ፱/ “አገናኝ” ማለት የጥብቅና አገልግሎትን በሚመለከት ጠበቃን ወይም የጥብቅና ድርጅትን እና ባለጉዳይን በማገናኘት ከአንዱ ወይም ከሁለቱም ወገን ክፍያ ወይም ኮሚሽን በመቀበል ወይም ወደፊት ለመቀበል በማሰብ ባለጉዳዩን በማግባባትና በማሳመን ባለጉዳዩ እርሱ የመረጠለትን ጠበቃ እንዲይዝ የሚያደርግ ወይም የሚያግባባ ማንኛውም ሰው ነው፤ ፲/ “የጥብቅና ሥራን በአገናኝ አማካኝነት መስራት” ማለት በፍርድ ቤቶች፣ በማረሚያ ቤቶች፣ በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በሌሎች የፍትሕ ተቋማት ወይም በማንኛውም ስፍራ አገናኞችን በማሰማራት ወይም በተሰማሩ አገናኞች ወይም ከየፍትሕ ተቋማቱ ኃላፊዎች ወይም ሠራተኞች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር የጥብቅና አገልግሎት ፈላጊዎች ወደ ጠበቃው ወይም የጥብቅና ድርጅቱ እንዲመጡ የማድረግ ተግባር ነው፤ ፲፫ሺ፬፻፹፫ ፲፩/ “ነጻ የጥብቅና አገልግሎት” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፩ ንዑስ አንቀጽ (፩) ሥር ለተዘረዘሩት የጥብቅና አገልግሎት ፈላጊዎች እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች ለተመለከቱ ሰዎች በአነስተኛ ክፍያ ወይም ያለምንም ክፍያ በጠበቃ ወይም በጥብቅና ድርጅት የሚሰጥ የጥብቅና አገልግሎት ነው፤ ፲፪/ “የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ” ማለት በጠበቃ ወይም ጥብቅና ድርጅት ሥር በመሆን በጠበቃ በኩል የሚቀርቡ ክሶችን፣ ማመልከቻዎችን፣ ይግባኞችን፣ አቤቱታዎችን፣ መልሶችን እና ሌሎች ሕግ ነክ ሠነዶችን በማዘጋጀት ወይም በማረም ጠበቃን የሚያግዝ ሰው ነው፤ ፲፫/ “የጠበቃ ረዳት” ማለት በጠበቃ ወይም ጥብቅና ድርጅት ሥር በመሆን ጠበቃን የሚያማክር፣ ለጠበቃው የሕግ አስተያየት የሚያዘጋጅ፣ የተዘጋጁ ክሶችን፣ ማመልከቻዎችን፣ ይግባኞችን፣ አቤቱታዎችን ወይም መልሶችን ፍርድ ቤት ወይም በሌላ የሕግ ሰውነት ባለው ተቋም ዘንድ በመገኘት የሚያቀርብ፤ ለሚመለከተው አካል የሚያደርስ፣ የክስ ወይም የይግባኝ መዝገብ የሚያስከፍት፤ መጥሪያዎችን፣ የውሳኔ ግልባጮችን እና ሌሎች ለጠበቃው መድረስ ያለባቸውን ሠነዶች ከሚመለከተው አካል በመቀበል ለጠበቃው የሚያደርስ ሰው ነው፤ ፲፬/ “መዝገብ” ማለት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚዘጋጅና የጥብቅና ፍቃድ የተሰጣቸው ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች ሙሉ መረጃ የሚመዘገብበት ባህር መዝገብ ወይም የመረጃ ቋት ነው፤ ፲፭/ “የሥነ-ምግባር ደንብ” ማለት የጠበቆች እና ጥብቅና ድርጅቶች ሥነ-ምግባርን አስመልክቶ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጣ ደንብ ነው፤ ፲፫ሺ፬፻፹፬ ፲፮/ “ሥልጠና” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት በማኅበሩ ወይም ማኅበሩ እውቅና በሰጠው ተቋም አማካኝነት ለጠበቆች በሥራ ላይ እያሉ የሚሰጥ የሕግ ሥልጠና ነው፤ ፲፯/ “ተቋም” ማለት ተከታታይ የሕግ ሥልጠና የሚሰጥ ድርጅት ነው፤ ፲፰/ “ቦርድ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፷፱ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የተቋቋመ የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ነው፤ ፲፱/ “ሕገ መንግስት” ማለት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት ነው፤ ፳/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ ፵፯ መሠረት እውቅና የተሰጠው ክልል ነው፤ ፳፩/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤ ፳፪/ በዚህ አዋጅ በወንድ ጾታ የተገለፀው የሴትንም ጾታ ያካትታል። Unless the context requires otherwise, in this Proclamation: 1/ “Advocate” means a person licensed to provide private advocacy services pursuant to this Proclamation. For the purpose provided under Article 8 of this Proclamation, foreign national Advocate who is granted advocacy service license pursuant to foreign law, is regarded as an Advocate; 2/ “Valid Advocacy License” means a license granted for the person who fulfills the requirements specified under this Proclamation; 3/ “Tax Clearance” means a certificate given, as an evidence of paying income tax, by a tax collecting authority to advocate license holder; 4/ “Law Firm” means an organization established to provide advocacy service; 5/ “Advocacy Service” means any kind of legal service provided by an advocate or a law firm for payment of a fee or in expectation of direct or indirect future benefit, or pro bono, including the following: a) providing consultation on legal issues; conducting negotiations except in criminal cases; b) drafting legal documents or submitting documents on behalf of a client; c) representing a client and litigating before courts of law; administrative tribunal; quasi-judicial institutions; arbitral bodies and other alternative dispute resolution forums. 6/ “Association” means the Ethiopian Federal Advocates’ Association established pursuant to Article 57 of this Proclamation; 7/ “Attorney General” means the Federal Attorney General established pursuant to Proclamation No. 943/2016; 8/ “Client” means a person who receives advocacy services; 9/ “Intermediary” means any person who introduces a potential client seeking advocacy services or otherwise persuades him to engage the services of an advocate or law firm of his choice, in consideration of immediate or future payment or commission from one or both parties; 10/ “Providing Advocacy Services through an Intermediary” means a practice by which an advocate or law firm recruits clients through an Intermediary, whether assigned for the purpose or already working as such, who establish relationships, including relationships motivated by mutual personal enrichment, with public officials working in courts, prison administration authorities, police stations, other justice organs or any place to procure his or its service; 11/ “Pro Bono Advocacy Service” means an advocacy service provided by an advocate or law firm at minimal or no charge to persons listed under Article 31 Sub-Article (1) of this Proclamation as in need of such services and to persons who provided by other relevant laws; 12/ “Law-Clerk” means a person who works for and assists an advocate or law firm in drafting or editing statements of claim, pleadings, applications, appeals, statements of defense and other legal and related documents; 13/ “Advocate’s Assistant” means a person who, works for an advocate or a law firm and provides advice; prepare legal documents; present to the court or other legal institutions signed statements of claim, letters, appeals, pleadings, or statement of defense and appeals ;deliver the same to such institutions; file statement of claim or an appeal; collect and deliver to the advocate or law firm court summons, copies of decisions or orders or other documents that are intended to reach the advocate; 14/ “Register” means a book of records or data base prepared and maintained by the Attorney General containing full and up- to-date record of all licensed advocates and law firms; 15/ “Code of Conduct” means a code of conduct to be issued pursuant to this Proclamation governing the professional ethics and conduct of advocates and law firms; 16/ “Training” means a legal on job training offered to advocates by the Association or an Institution accredited by the Association to offer such trainings; 17/ “Institution” means an organization which offers continuing professional legal training; 18/ “Board” means the Advocates’ Administration Board established under Article 69 Sub-Article (1) of this Proclamation; 19/ “Constitution” means the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia; 20/ “Region” means State recognized under Article 47 of the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia; 21/ “Person” means natural or juridical person; 22/ In this Proclamation any expression in the masculine gender includes the feminine gender.
ይህ አዋጅ የጥብቅና ፍቃድ በተሰጣቸው የፌደራል ጠበቆች፣ የጥብቅና ድርጅቶች እንዲሁም በሀገር ውስጥ በሚሰሩ የውጭ ሀገር ጠበቆች ወይም የጥብቅና ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። ፲፫ሺ፬፻፹፭ This Proclamation shall be applicable on federal advocates and law firms licensed under this Proclamation as well as foreign national advocates or law firms working within the country.
፩/ ማንኛውም ሰው ፍቃድ ሳይኖረው የጥብቅና አገልግሎት መስጠት አይችልም። ፪/ የጥብቅና ፍቃድ ቋሚ ሥራ ላለው ሰው አይሰጥም። ፫/ ማንኛውም የጥብቅና ፍቃድ ማግኘት የሚፈልግ ሰው በዚህ አዋጅ የተደነገጉ መስፈርቶችን ማሟላት አለበት። ፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) እንደተጠበቀ ሆኖ ማንም ሰው በጾታ፤ በሃይማኖት፤ በቋንቋ፤ በዘር ወይም በማኅበራዊ አመጣጡ፤ በፖለቲካ አመለካከቱ፤ በንብረቱ፤ በትውልዱ፤ በአካል ጉዳት ወይም ማንኛውንም ተመሳሳይ ሁኔታ መሠረት በማድረግ ፍቃድ አይከለከልም። 1/ No person shall provide advocacy services without having a license; 2/ Advocacy license shall not be given to a person having a permanent job; 3/ A person who wishes to obtain an advocacy license shall fulfill the requirements provided in this Proclamation; 4/ Without prejudice to Sub-Article (2) of this Article, no person shall be denied a license on grounds of gender, religion, language, ethnic or social background, political persuasion, economic status, origin, physical disability or other similar conditions.
፩/ ስለራሱ ጉዳይ የሚከራከር ሰው፤ ፪/ ያለክፍያ ለትዳር ጓደኛው፤ ለወላጁ፤ ለልጁ፤ ለአያቱ፤ ለእህቱ፤ ለወንድሙ፤ ለትዳር ጓደኛው ወላጆች፤ እንዲሁም ሞግዚት ወይም አሳዳሪ ለሆነለት ሰው የሚከራከር ሰው፣ ፫/ ከሥራው ጋር በተያያዘ ጉዳይ የሚከራከር ዐቃቤ ሕግ፣ ፲፫ሺ፬፻፹፮ ፬/ ሕጋዊ ሰውነት ባለው የንግድ ድርጅት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት፤ ሕዝባዊ ድርጅት፣ የሃይማኖት ተቋም፣ የሙያ ማኅበር፣ ዓለም አቀፍ ድርጅት ወይም በሌላ አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት በተቋቋመ ድርጅት ተቀጥሮ የተወከለ ሰው፣ ፭/ የመንግስት መሥሪያ ቤትን ወይም የልማት ድርጅትን በሚመለከት የሚከራከር ማንኛውም የመንግስት መሥሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ባለስልጣን ወይም ኃላፊ ወይም በእርሱ የተወከለ ሰው፣ ወይም ፮/ ማንኛውም የሠራተኛ ማኅበር መሪ ወይም ማህበሩ የሚወክለው ሰው። The following persons may provide advocacy services without the need for an advocacy license: 1/ Any person handling his own case; 2/ A person who represents, without charge, his spouse, parent, child, grandparent, sister, brother, the parent of his spouse, a person to whom he is the designated tutor or guardian; 3/ A Public prosecutor on cases related to his job; 4/ A person employed and assigned by a business organization having legal personality, a civil society organization, public organization, religious institution, professional association, international organization; or institution established in accordance with the relevant law; 5/ An official or head of a public enterprise or a person bestowed with power of attorney by such organs who litigate on behalf of public office or public enterprise; or 6/ Any leader or designated representative of a labor union.
፩/ ማንኛውም በጥብቅና ሙያ መሰማራት የሚፈልግ ሰው የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡ሀ) የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ፣ ለ) እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው፣ ሐ) ለመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት ተቋም ድርጅቱን ከመልቀቁ በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ ዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ እና የመልካም ሥነ-ምግባር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ እና ፲፫ሺ፬፻፹፯ መ) በሕግ ሙያ የሚፈለገውን የሥራ ልምድ ያሟላ እና እንደ አስፈላጊነቱ ፍቃድ ለማግኘት የሚሰጠውን የሙያ መግቢያ ፈተና ያለፈ። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል-ተራ (ለ) የተመለከተው ቢኖርም ከኢትዮጵያ ውጪ ካለ እውቅና ካለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተሰጠው ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ (፪)፣ አንቀጽ ፲፫ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና አንቀጽ ፲፬ ንዑስ አንቀጽ (፪) ሥር የተመለከተውን መስፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ የጥብቅና ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ሰው አስፈላጊ ሠነዶችን በማያያዝ የጥብቅና ፍቃድ ማመልከቻውን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቅረብ ይኖርበታል። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል-ተራ (መ) መሠረት የሚቀርበው የፈተና ውጤት ዋጋ የሚኖረው ውጤቱ በታወቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከቀረበ ብቻ ነው። 1/ Any person who wishes to join the advocacy profession may obtain advocacy license by fulfilling the following requirements: a) to be an Ethiopian national or a foreign national of Ethiopian origin; b) have a minimum of first degree in law from a recognized Ethiopian Higher Education Institution; c) able to present a statement from his most recent employer indicating that, in his last two years of employment, he had not been subjected to measures for serious disciplinary infractions and can produce proof of good conduct; and d) meet the work experience required in the legal profession and pass any qualification examination that may be necessary to obtain advocacy license. 2/ Notwithstanding Sub-Article (1) Paragraph (b) of this Article, any person who received his first degree in law from a recognized Higher education institution abroad may be granted advocacy license provided he fulfills the criteria set out under Article 12 Sub-Article (2), Article 13 Sub-Article (2) and Article 14 Sub- Article (2) of this Proclamation; 3/ A person who fulfills the requirements provided under Sub-Article (1) of this Article shall present his application for advocacy license along with necessary documents, to the Attorney General. 4/ The result of any qualification examination referred to in Sub-Article (1) paragraph (d) of this Article shall be valid only if it is presented within a year.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች ያላሟላ ከሆነ፤ ፲፫ሺ፬፻፹፰ ፪/ ታስቦ በሚፈጸምና ከሙያ ሥነ-ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ ጽኑ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ከተባለ እና አግባብነት ባለው ሕግ ያልተሰየመ ከሆነ፤ ፫/ በሕግ አገልግሎት እንዳይሰማራ በሕግ ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ከሆነ ነው። A person shall not get an advocacy license if: 1/ He does not fulfill the requirements provided under Article 6 Sub-Article (1) of this Proclamation; 2/ He is found guilty of an offence committed intentionally and has relevance with professional misconduct that is punishable with rigorous imprisonment of three years and above and has not been reinstated under the appropriate law; 3/ He is interdicted by law or judicially interdicted from engaging in the provision of legal services.
፩/ በውጭ ሀገር ሕግ መሠረት የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ ያለው ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት በያዘው የውጭ ሀገር ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለደንበኞቹ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት የሚችለው፦ ሀ) ጉዳዩ ፍቃድ የተሰጠበትን ሀገር ሕግን በሚመለከት ሲሆን፤ እና ለ) በዚህ አዋጅ መሠረት የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ ካገኘ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ጋር በመሆን ብቻ ነው። ፪/ በዚህ አዋጅ መሠረት የተደነገጉ የጥብቅና አገልግሎት የማያሰጡ፣ ወይም የሥነ- ምግባር እርምጃ የሚያስወስዱ ግዴታዎች እንደ አግባብነታቸው የጥብቅና አገልግሎት በሚሰጡ የውጭ ሀገር ጠበቃ እና የጥብቅና ድርጅት ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ። ፲፫ሺ፬፻፹፱ Firms 1/ A foreign national advocate or law-firm with valid advocacy license granted in a foreign country may use his foreign license to render advocacy service to clients in Ethiopia under the following conditions: a) where the case involves the law of the Country that issued the advocacy license; and b) only in partnership with an advocate or law-firm licensed under this Proclamation. 2/ The grounds for denial of an advocacy license under this Proclamation or the imposition of disciplinary measures shall also apply, as appropriate, to advocacy service providers holding a foreign license.
፩/ በዚህ አዋጅ መሠረት የፌደራል የጥብቅና ፍቃድ የሚሰጠው በጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ ውሳኔ መሠረት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነው። ፪/ አመልካቹ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሠረት የተሟላ ማመልከቻ ባቀረበ ፴ ቀናት ውስጥ የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ ተገቢ የሚለውን ውሳኔ መስጠት አለበት። ፫/ የጥብቅና ፍቃድ ማመልከቻ ተቀባይነት ካላገኘ የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማመልከቻው ተቀባይነት ያላገኘበትን ምክንያት የኮሚቴውን ውሳኔ ባወቀ በ፲ የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ለአመልካቹ ማሳወቅ አለበት። ፬/ የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ፍቃድ እንዲሰጥ ከወሰነ በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ የጥብቅና ፍቃዱን ለአመልካቹ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል መስጠት አለበት። ፭/ የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ በሚሰጥበት ጊዜ በፍቃድ ደብተር ላይ መጠቀስ ያለባቸው ነጥቦች ዝርዝር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። ፮/ የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴው ማመልከቻውን ውድቅ ካደረገው አመልካቹ ማመልከቻው ውድቅ መደረጉን ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለቦርዱ ማቅረብ ይችላል። ፲፫ሺ፬፻፺ ፯/ በቦርዱ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን የውሳኔ ግልባጭ ከደረሰው ጊዜ ጀምሮ ባሉት ፴ ቀናት ውስጥ ይግባኙን ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። 1/ An advocacy license, under this Proclamation, shall be issued by the Attorney General according to the decision of the Advocacy License Evaluation Committee; 2/ Advocacy License Evaluation Committee shall give decision it deems appropriate on an application no longer than 30 days from the submission of a complete application as provided under Article 6 Sub-Article (3) of this Proclamation; 3/ If an application is rejected, the Attorney General, based on the decision of Advocacy License Evaluation Committee, shall notify the applicant in writing the grounds for rejection within 10 working days of knowing the decision of the Committee; 4/ If the Advocacy License Evaluation Committee accepts an application pursuant to sub-Article (1) of this Article, it shall issue the license through Attorney General to the applicant within 15 working days of the decision; 5/ The particulars to be mentioned on the document evidencing the advocacy license shall be determined by a Directive to be issued by the Attorney General; 6/ If Advocacy License Evaluation Committee rejects an application, the applicant, within 15 working days from the day he is notified about the rejection, may lodge complaints to the Board; 7/ A party aggrieved by the decision of the Board may appeal to the Federal First Instance Court within 30 days of receiving copy of the decision.
የቃለ መሐላ ፈጻሚውን እምነት ለማስተናገድ ሊደረጉ የሚችሉ ምክንያታዊ ለውጦች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ የሚሰጠው ጠበቃ የሚከተለውን ቃለ መሀላ በጽሑፍ ያረጋግጣል፡- «እኔ ዛሬ ቀን ዓ.ም የፌደራል የጥብቅና ፈቃድ ስቀበል የሀገሪቱን ሕገ-መንግስት እና ሕጎች ላከብር እና ላስከብር፤ ለፍትሕ ሥርዓቱ ተልዕኮ መሳካት በመልካም ሥነ-ምግባር በሙያዬ በቅንነት እና በታማኝነት በመስራት የምወክላቸውን ደንበኞቼን ጥቅም ሕግ በሚፈቅደው አግባብ ላስከብር፤ ከተከራካሪዎቼ እና ከሙያ ባልደረቦቼ ጋር በመግባባት እና በመከባበር ልሰራ እና፤ ባለኝ እውቀት እና ችሎታ ለሕግ የበላይነት ተገቢውን እገዛ ለማድረግ ቃል እገባለሁ» Without prejudice to reasonable adjustments that may be made in order to accommodate the religious beliefs of the person taking an oath, any person to be issued with an advocacy license shall take the following oath in writing: “I......................................,in receiving this Federal Advocacy License on this.......................day of 20....,do swear and solemnly affirm that I shall observe and ensure the observance of the Constitution and the laws of the land; to serve the objectives of the justice system by discharging my duties with honesty and integrity and protect the interests of my clients according to law; to work with my colleagues and opposing parties in a spirit of understanding and mutual respect and contribute my share, to the fullest extent of my knowledge and ability, for the realization of rule of law.”
፩/ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ፣ ፪/ የፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ፣ እና ፫/ የፌደራል ልዩ ጥብቅና ፍቃድ፤ ናቸው። ፲፫ሺ፬፻፺፩ The types of advocacy license are: 1/ The Federal First Instance Court Advocacy License; 2/ All Federal Courts Advocacy License; and 3/ The Federal Special Advocacy License.
፩/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ይሰጠዋል፡ሀ) እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ እና በሕግ ሙያ ቢያንስ ሶስት ዓመት የሥራ ልምድ፤ ወይም በሕግ በዲፕሎማ የተመረቀ እና በሕግ ሙያ አምስት ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፣ ለ) ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና ፍቃድ መግቢያ ፈተና ያለፈ፣ ሐ) ለመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት ተቋም ድርጅቱን ከለቀቀበት ጊዜ በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ ዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ፣ እና መ) መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል። ፲፫ሺ፬፻፺፪ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል-ተራ (ሀ) ሥር የተመለከተው ቢኖርም ከኢትዮጵያ ውጪ ካለ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ ሙያ ለአምስት ዓመት ካገለገለ እና ሌሎች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል። Advocacy License 1/ Any Ethiopian citizen or foreign national of Ethiopian origin who fulfills the following requirements shall be granted the Federal First Instance Court Advocacy License:- a) has graduated with a first degree in law from a recognized Ethiopian Higher Education Institution and has a minimum of three years of professional experience in the field of law; or has graduated with diploma in law and has a minimum of five years of professional experience in the field of law; b) has passed the entrance qualification examination set for the particular type of advocacy license; c) produces evidence, from his immediate past employer, that certifies that he had not been subjected to grave disciplinary measures for violation of serious misconduct in the two years prior to departure; and d) Produce a certificate of good conduct from his immediate past employer. 2/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (1) paragraph (a) of this Article, a Federal First Instance Court Advocacy License may be granted to a person who graduated with first degree in law from a recognized foreign Higher Education Institution and has a minimum of five years of professional experience in the field of law in Ethiopia and fulfills the other requirements listed under Sub- Article (1) of this Article.
፩/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ይሰጠዋል፡ሀ) እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው እና በሕግ ሙያ ቢያንስ የአምስት ዓመት ልምድ ያለው፣ ለ) እንደ አስፈላጊነቱ ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና ፍቃድ መግቢያ ፈተና ያለፈ፣ ሐ) ለመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት ተቋም ድርጅቱን ከለቀቀበት ጊዜ በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ ዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ፣ እና መ) መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል። ፲፫ሺ፬፻፺፫ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል-ተራ (ሀ) ሥር የተመለከተው ቢኖርም ከኢትዮጵያ ውጪ ካለ እውቅና ካለው ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ ሙያ ለሰባት ዓመት ካገለገለ እና ሌሎች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ሥር የተመለከቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ የፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል። 1/ Any Ethiopian citizen or a foreign national of Ethiopian origin who fulfills the following requirements shall be granted the All Federal Courts Advocacy License: a) has graduated with first degree in law from a recognized Ethiopian Higher Education Institution and has a minimum of five years of professional experience in the field of law; b) as may be necessary, has passed the entrance qualification examination set for the particular type of advocacy license; c) produces evidence, from his immediate past employer, that certifies he had not been subjected to disciplinary measures for violation of serious misconduct in the two years prior to departure; and d) Produce a certificate of good conduct from his immediate past employer. 2/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (1) paragraph (a) of this Article, All Federal Courts Advocacy License may be granted to a person who graduated with a first degree in law from a recognized foreign higher education institution if he has a minimum of seven years of professional experience in the field of law in Ethiopia and fulfills the other requirements listed under Sub-Article (1) of this Article.
፩/ የፌደራል ልዩ የጥብቅና ፍቃድ፡ሀ) የሕብረተሰቡን አጠቃላይ መብት እና ጥቅም ለማስከበር በነጻ አገልግሎት ለሚሰጥ ሰው ወይም ድርጅት፣ ወይም ለ) አቅም ለሌላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ለሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሕግ ትምህርት ቤቶች እና የሕግ መምህራን ሊሰጥ ይችላል። ፪/ ማንኛውም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል-ተራ (ሀ) መሠረት የፌደራል ልዩ የጥብቅና ፍቃድ ማግኘት የሚፈልግ ሰው የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡- ፲፫ሺ፬፻፺፬ ሀ) እውቅና ካገኘ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው እና በሙያው ቢያንስ ፭ ዓመት ያገለገለ ወይም እውቅና ካገኘ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው እና በሙያው ቢያንስ ፭ ዓመት ያገለገለ ባለሙያ ያለው ተቋም ወይም ድርጅት፣ ለ) ከሚወክለው የሕብረተሰብ ክፍል ወይም ደንበኛ ክፍያ የማይቀበል፤ እና ሐ) መልካም ሥነ-ምግባር ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል። ፫/ ማንኛውም የፌደራል የጥብቅና ፍቃድ ያለው ሰው ልዩ የጥብቅና ፍቃድ ሳያስፈልገው የልዩ ጥብቅና አገልግሎት መስጠት ይችላል፤ ነገር ግን ይህን አገልግሎት ከመስጠቱ በፊት ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት። ፬/ የፌደራል ልዩ የጥብቅና ፍቃድ የተሰጠው ሰው ወይም ድርጅት የጥብቅና አገልግሎቱን ሲሰጥ ይህን አዋጅ እና የጠበቃ ሥነ-ምግባር ደንብን በተከተለ መልኩ መፈጸም አለበት። ፲፫ሺ፬፻፺፭ 1/ The Federal Special Advocacy License may be granted to: a) a person or organization that provides pro bono advocacy services to protect the public interest and rights; or b) law instructors and law Schools of Higher Education Institutions who provide pro bono advocacy services to individuals and sections of society who lack financial means to pay for such service. 2/ Any person who wishes to obtain the Federal Special Advocacy License under Sub-Article (1) paragraph (a) of this Article shall fulfill the following requirements: a) has a first degree in law from a recognized Higher Education Institution and a minimum of five years of professional experience in the field of law; or institution or organization who have a lawyer graduated with first degree in law from a recognized Ethiopian Higher Education Institution and has a minimum of five years of professional experience in the field of law; b) does not receive payment from his client or section of the society he represents; and c) produce a certificate of good conduct from the concerned body. 3/ Any federal advocacy license holder may render special advocacy service without issuing Special Advocacy License; However, before rendering the service the advocate shall inform in writing the Attorney General; 4/ Any person or organization who is granted the Federal Special Advocacy License, in the discharge of his or its duties, shall comply with this Proclamation and the Advocates’ Code of Conduct. ‹
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ (፪) ሥር የተደነገገው ቢኖርም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሕግ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምር ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሕግ መምህር በአንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ (፩) ወይም በአንቀጽ ፲፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተጠቀሰውን ካሟላ የሕግ መምህርነት ሙያውን መልቀቅ ሳያስፈልገው የጥብቅና ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የሕግ ትምህርት ቤት መምህር የጥብቅና ፍቃድ እንዲሰጠው ሲያመለክት የጥብቅና ሥራው የመማር ማስተማር ሂደቱን የማያስተጓጉል ስለመሆኑ በሕግ ትምህርት ቤቱ የተሰጠ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት። School instructors 1/ Notwithstanding the provisions of Article 4 Sub-Article (2) of this Proclamation, an Ethiopian or a foreign national of Ethiopian origin who teaches law in law schools of higher education institutions and fulfills the requirements of Article 12 Sub-Article (1) or Article 13 Sub- Article (1) may be granted an Advocacy License without having to resign from his teaching post; 2/ A law school instructor who requests for grant of an advocacy license pursuant to Sub-Article (1) of this Article shall submit an assurance issued by the law school his advocacy service does not affect the teaching learning process.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ (፩) ሥር የተደነገጉትን የሚያሟላ ማንኛውም በጥብቅና አገልግሎት መሰማራት የሚፈልግ ሰው የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና መውሰድ ይኖርበታል። ‹ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሮት በኢትዮጵያ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሕግ መምህርነት ለሰባት ዓመት ያገለገለ፤ በዳኝነት፣ በዐቃቤ ሕግነት፣ በመንግስት መሥሪያ ቤት ወይም በመንግስት የልማት ድርጅት ውስጥ በሕግ አማካሪነት ወይም በሕግ ባለሙያነት ወይም በነገረ ፈጅነት ቢያንስ ለአምስት ዓመት ያገለገለ፤ በረዳት ዳኝነት፣ በጠበቃ ወይም ጥብቅና ፲፫ሺ፬፻፺፮ ድርጅት የሕግ ጉዳይ ጸሐፊነት ወይም የጠበቃ ረዳትነት እንዲሁም በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት፣ በሃይማኖት ተቋማት፣ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በንግድ ድርጅቶችና ሌሎች ተቋማት በሕግ አማካሪነት ወይም በሕግ ባለሙያነት ወይም በነገረ-ፈጅነት ቢያንስ ለሰባት ዓመት ያገለገለ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሥራውን በለቀቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የጥብቅና ፍቃድ ማመልከቻ ያቀረበ እንደሆነ የጥብቅና ፍቃድ ያለፈተና ሊሰጠው ይችላል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ላይ ተደነገገው ቢኖርም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ጥብቅና ፍቃድ ለአምስት ዓመት ያገለገለ እና በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ጠበቃ የጥብቅና አገልግሎት ሥራውን ሳይተው የፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ያለፈተና ሊሰጠው ይችላል። ፬/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ ፍቃድ እንዲሰጠው ለወሰነለት ባለሙያ የጥብቅና ፍቃድ ይሰጣል። ፲፫ሺ፬፻፺፯ 1/ Any person who meets the requirements of Article 6 Sub-Article (1) of this Proclamation and wishes to engage in the provision of advocacy services shall take the qualification examination for advocacy services; 2/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (1) of this Article, an Ethiopian or a foreign national of Ethiopian origin with first degree in law and served as a law instructor for a minimum of seven years in an Ethiopian Higher Education Institution; or as a judge, public prosecutor, as a legal advisor or legal professional or as an attorney in public services or public enterprises for a minimum of five years; or as assistant judge, as advocates’ assistant or law clerk in a law firm or with an advocate, as well as a legal advisor or as a professional in the field of law or as an attorney in civil societies, religious institutions, international organizations, business organizations and in other institutions for a minimum of seven years shall be granted advocacy license without having to take the advocacy examination if he applies within one year of leaving his post; 3/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (2) of this Article, an advocate with first degree in law and who served as a Federal First Instance Court Advocate for five years, may be granted the All Federal Courts Advocacy License without having to take the advocacy qualification examination leaving his advocacy service; 4/ The Attorney General shall issue an Advocacy License to the person who is allowed to take the license by the Advocacy License Evaluation Committee.
፩/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥብቅና ፍቃድ የተሰጣቸውን ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች ሙሉ መረጃ ዘመናዊ በሆነ መንገድ መመዝገብ አለበት። ፪/ በምዝገባ ሥርዓቱ ውስጥ የሚካተቱ ዝርዝር ነጥቦች ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። ፫/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት አዲስ የመዘገባቸውን ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች ሥም ዝርዝር በየሶስት ወሩ ለማኅበሩ ማሳወቅ ይኖርበታል። ፬/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥብቅና ፍቃድ የተሰጣቸውን ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች መረጃ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን በተለያየ መንገድ ይፋ ያደርጋል። 1/ The Attorney General shall maintain a state-of-the-art that contains full information about register of advocates and law firms that have been granted advocacy licenses; 2/ The particulars required in the registration process shall be determined by a Directive to be issued by the Attorney General; 3/ The Attorney General shall notify the Association, every three months, the list of newly licensed and registered advocates and law firms pursuant to Sub-Article (1) of this Article; 4/ The Attorney General shall make accessible the information, about licensed advocates and law firms, to the society in different ways.
፩/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ፤ የጠበቃ ረዳት ወይም ሌሎች ለሥራው የሚያስፈልጉ ሠራተኞችን መቅጠር የሚችል ሲሆን የጥብቅና ድርጅት ከነዚህ ከተጠቀሱት ሠራተኞች በተጨማሪ ጠበቃ ሊቀጥር ይችላል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ቅጥር የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ቅጥሩ በተፈጸመ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማሳወቅ እና ማስመዝገብ አለበት። ፲፫ሺ፬፻፺፰ ፫/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የሚከተሉትን በሕግ ጉዳይ ጸሐፊነት ወይም በጠበቃ ረዳትነት መቅጠር አይችልም፡ሀ) የጥብቅና ፍቃዱ የታገደን ወይም የተሰረዘን ሰው፣ ለ) ስሙ ከመዝገብ የተፋቀን ሰው፣ ሐ) ከመሥሪያ ቤቱ በዲስፕሊን ጥፋት የተባረረን ሰው፣ መ) ከሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ ወንጀል ተከሶ የተቀጣ እና ያልተሰየመን ሰው፣ ሠ) ቋሚ ሥራ ያለውን ሰው፣ ወይም ረ) የሕግ ትምህርት ወይም በሕግ ሙያ የሥራ ልምድ የሌለውን ሰው። Law Firms 1/ Any advocate or law firm may employ law clerks, advocates’ assistants, or other support staff necessary for its work; a law firm may also employ advocates; 2/ An Advocate or law firm that has employed pursuant to Sub-Article (1) of this Article shall, within two months of the execution of the employment contract, notify the Attorney General of the said employment and have them registered therein; 3/ No advocate or law firm may employ the following persons as law clerks or advocates’ assistants: a) a person whose advocacy license has been suspended or revoked; b) a person whose name has been struck off from the Advocates’ Register; c) a person dismissed from his previous position for disciplinary misconduct; d) a person who was convicted and punished for an offence related to professional misconduct and not reinstated; e) a person who has permanent job; or f) a person without training in law or lacking experience in the field of law.
፩/ የጥብቅና ፍቃድ በየዓመቱ ፍቃዱ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መታደስ አለበት። ፪/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ፍቃዱን ሳያሳድስ ከቀረ በሚቀጥለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚጣልበትን የገንዘብ ቅጣት ከፍሎ ፍቃዱ ይታደስለታል። ፲፫ሺ፬፻፺፱ ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ ጠበቃው ወይም የጥብቅና ድርጅቱ ፍቃዱን ያላሳደሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑን የሚያሳይ አሳማኝ ማስረጃ ካቀረበ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚጣልበትን የገንዘብ ቅጣት ከፍሎ በቀጣዩ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የጥብቅና ፍቃዱ ሊታደስለት ይችላል። ፬/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት በዚህ አንቀጽ መሠረት ፍቃዱን ያላሳደሰ እንደሆነ የዲስፕሊን ክስ ይቀርብበታል። 1/ An advocacy license shall be renewed every year within a month of its last validity date; 2/ Any advocate or firm that fails to renew his or its license within the period provided in Sub-Article (1) of this Article, upon payment of fine the amount of which shall be determined by a Directive to be issued by the Attorney General, may renew his or its license within the following one month; 3/ An advocate or Law firm that proves he or it has not renewed the license within the period prescribed under Sub-Article (2) of this Article due to force majeure, may renew the license having paid the fine determined by the Directive to be issued by the Attorney General. 4/ Any advocate or law firm that has not renewed his or its license according to this Article, shall be charged for disciplinary misconduct.
፩/ የግብር ክሊራንስ ማስረጃ፤ ፪/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴ ንዑስ አንቀጽ (፬) መሠረት አስገዳጅ የሕግ ሥልጠና ከተራዘመለት ጠበቃ በስተቀር ጠበቃው በዚህ አዋጅ የተቀመጠውን የሥልጠና ግዴታ ማጠናቀቁን የሚገልጽ ማስረጃ፤ ፫/ ለጠበቆች ማኅበር መክፈል የሚጠበቅበትን የአባልነት መዋጮ መክፈሉን የሚያረጋግጥ ከማኅበሩ የሚሰጥ ማስረጃ፤ ፬/ እድሜው ከ፸ ዓመት በላይ የሆነ ጠበቃ ሕጋዊ ከሆነ የጤና ተቋም የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጤና ሁኔታ ላይ ያለ ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ፤ እና ፲፫ሺ፭፻ ፭/ በዓመት ውስጥ መስጠት የሚጠበቅበትን ነጻ የጥብቅና አገልግሎት ስለመስጠቱ የሚያረጋግጥ ማስረጃ። License Any advocate or law firm shall present the following evidences to renew his/its license: 1/ Tax clearance certificate; 2/ With the exception of the advocate whose mandatory training was rescheduled pursuant to Article 30 Sub- Article (4) of this Proclamation, evidence showing that the advocates completed the mandatory training prescribed by this Proclamation; 3/ Evidence given by the Association which certifies that the advocate has discharged his duty of paying membership contribution; 4/ Evidence from a health institution, for those advocates above 70 years old, which certifies that the advocate is fit and in good health condition to provide advocacy service; and 5/ Evidence showing that the Advocate discharged his duty of providing pro bono service expected of him in a year.
፩/ ማንኛውም ጠበቃ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት የጥብቅና ፍቃዱን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መመለስ አለበት፡ሀ) ከሙያው ውጭ በሆነ ሥራ በቋሚነት የተሰማራ እንደሆነ፣ ለ) የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት ያልቻለ እንደሆነ፣ ሐ) የጥብቅና አገልግሎት ለማቆም ከወሰነ። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ጠበቃው ፍቃድ ለመመለስ ሲያመለክት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥብቅና ፍቃድ ደብተሩን ወዲያውኑ መረከብ አለበት፣ ሆኖም የጥብቅና አገልግሎቱን ማቋረጡን የሚገልጽ ማስረጃ ለጠበቃው የሚሰጠው ጠበቃው ከሚመለከተው አካል የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ይዞ ሲቀርብ ይሆናል። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ፍቃዱን የመለሰ ጠበቃ ወደ ጥብቅና ሥራው መመለስ ከፈለገ ፍቃዱን መልሶ ሊወስድ ይችላል፣ ሆኖም ጠበቃው ከጥብቅና አገልግሎቱ ከሁለት ዓመት በላይ ተለይቶ የቆየው ከሕግ ሙያ ውጪ በሆነ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ከሆነ ፍቃዱ የሚመለስለት ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና መግቢያ ፈተና ወስዶ ካለፈ ብቻ ነው። ፲፫ሺ፭፻፩ 1/ Any Advocate shall return his advocacy license to the Attorney General for the following reasons: a) when he permanently engaged in jobs other than advocacy service; b) when he is unable to render advocacy service; c) when he decides to terminate providing advocacy service. 2/ When an advocate applies to return his license pursuant to Sub-Article (1) of this Article, the Attorney General shall immediately receive the license of advocacy Service. However, it is only when the advocate produces tax clearance certificate, the evidence of termination of advocacy service shall be provided to him. 3/ An advocate who returned his advocacy license pursuant to Sub-Article (1) of this Article may get his license back if he wants to resume Advocacy service; however, an advocate who dissociated himself from advocacy service for more than two years can get back his license only when he passes the entrance exam set for his class of license.
፩/ በደንበኛ፣ በፍርድ ቤት ወይም በማንኛውም አግባብ ባለው አካል የጥብቅና ፍቃድን እንዲያሳይ ሲጠየቅ የማሳየት ግዴታ አለበት፤ ፪/ የጥብቅና ፍቃዱን በማንኛውም ሁኔታ ለሌላ ሰው መጠቀሚያ ወይም መገልገያ አሳልፎ መስጠት የለበትም። Service Every advocate or law firm: 1/ Has the duty to show his/its advocacy license when requested by his Client, the Court or any appropriate body; 2/ He or it is never allowed to give his or its license for others to make use of it or get benefit out of it.
፩/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሚሰጠው የሕግ ምክር አገልግሎት ውጭ ከደንበኛው ጋር የሚያደርገውን የጥብቅና አገልግሎት ውል በጽሑፍ ማድረግ አለበት፤ የጥብቅና አገልግሎት ውል ማካተት ስለሚገባቸው ነገሮች ማኅበሩ በመመሪያ ይወስናል። ፪/ የጥብቅና አገልግሎት ውሉ ደንበኛው ለጠበቃው የሚከፍለውን አጠቃላይ የገንዘብ ክፍያ፤ የአከፋፈሉን ስልት እና ጊዜ፤ ጠበቃው በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን የጥብቅና አገልግሎት የሚያካትት መሆን አለበት። ፲፫ሺ፭፻፪ ፫/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት፡ሀ) ለጥብቅና አገልግሎት መስጫ የሚሆን ቢሮ የማሟላት፣ ለ) የጥብቅና ሥራን በአገናኝ አማካኝነት ያለመስራት፣ እና ሐ) የጥብቅና ውልን ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት ያለማቋረጥ እና በጥብቅና ውሉ ከተገለጸው የክፍያ መጠን በላይ ተጨማሪ ክፍያ ከደንበኛ ያለመጠየቅ፤ ግዴታ አለበት። ፬/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፫) ፊደል-ተራ (ሀ) ላይ የተደነገገው ቢኖርም የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ፍቃድ ሰጪው አካል ቢሮ ማሟላትን እንደመስፈርት ሊጠይቅ አይችልም። Related Obligations 1/ Any advocate or law firm is obliged to make, in writing, the advocacy service contract which he or it makes with his client except legal advice given for a short period of time; the Association shall determine by Directive what would be included in the contract of advocacy service; 2/ The contract of the advocacy service shall include the total amount of fee the client pays to the advocate or law firm, computation and time of payment and the extent of the service to be provided; 3/ Every advocate or law firm has the following obligations: a) To have an office where he/it provides the advocacy service; b) To perform the service without using intermediary; c) Not to terminate the advocacy service contract without good cause and not to demand more payment than the one agreed upon on the contract of service. 4/ Notwithstanding the provision of paragraph (a) of Sub-Article (3) of this Artilcle, the license issuing authority shall not require office to grant the advocate license.
፩/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጥብቅና አገልግሎት ሥራውን በታማኝነት የመስራትና ለፍትሕ አጋር የመሆን ግዴታ አለበት። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ጠቅላላ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ያለበቂ ምክንያት ጉዳይን ያለማጓተት፣ ምስክሮችን በሀሰት ያለማደራጀት፣ ሀሰተኛ ማስረጃ ያለማቅረብ ወይም ያለማስቀረብ፣ ተዘጋጅቶ የመቅረብና ተገቢውን ክርክር የማድረግ፤ የሕግ መሠረት የሌለውንና የማያዋጣ ጉዳይን ያለመያዝ፤ የደንበኛውን ወይም ባለጉዳዩን ምስጢር ያለማውጣት እና ሌሎች መሰል የሥነምግባር ግዴታ አለበት። ፲፫ሺ፭፻፫ ፫/ ሌሎች መሰል ከጠበቃ ሥነ-ምግባር ጋር የተያያዙ ግዴታዎች በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ በቦርዱ ወይም በማኅበሩ ሀሳብ አመንጪነት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል ተዘጋጅቶ በሚኒስተሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ የሚወሰን ይሆናል። 1/ Any advocate or law firm has the obligations to perform his or its advocacy service honestly and in a manner that ensures loyalty to justice; 2/ Without prejudice to the general provision provided under Sub-Article (1) of this Article, any advocate or law firm has the duty, not to unduly delay cases without good cause; not to organize false witnesses; not to produce false evidence or cause such evidence to be produced; appear before the court duly prepared and make competent arguments; reject cases which have no cause of action and legal basis; keep the confidentiality of his client’s information and respect other similar codes of conduct; 3/ Other similar codes of conduct related with advocates’ conduct that are initiated by the Attorney General, Board or Association, are prepared by the Attorney General and determined by a Regulation to be issued by the Council of Ministers.
የሕግ ሥልጠና ዓላማ ጠበቆች የሙያ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚያስችል ወቅታዊ እውቀትና ክህሎት በቀጣይነት እንዲኖራቸው ማስቻል ነው። The purpose of legal training is to enable Advocates acquire up-to-date knowledge and excellence to discharge their professional responsibility.
፩/ ማንኛውም ጠበቃ በዓመት ውስጥ በድምሩ ከ፳፬ እስከ ፴ ሰዓት የሚደርስ የሕግ ሥልጠና የመውሰድ ግዴታ አለበት። ፪/ የሕግ ሥልጠናው በተከታታይ ወይም በዚያው ዓመት ውስጥ በተለያየ ጊዜ ሊሰጥ ይችላል። ፫/ በሕግ ሥልጠና የሚሸፈኑ የሥልጠና ዘርፎችን፣ የሥልጠና ጊዜውን ርዝመት፤ አጠቃላይ የሥልጠና አሰጣጥ መርሃ-ግብር፤ የሥልጠና ክፍያ እና ሌሎች ከሥልጠና ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ ማኅበሩ በሚያወጣው መመሪያ ይወስናል። ፲፫ሺ፭፻፬ 1/ Any advocate has the duty to take training on the subject of law on aggregate from 24 up to 30 hours in a given year; 2/ The training on the subject of law may be offered in continuity or in different cycles within that year; 3/ The subjects to be covered by the training, the duration of the training, general training program procedures, training fee and other issues related with training shall be determined by the Directive to be issued by the Association.
፩/ የሕግ ሥልጠና የሚሰጠው በማኅበሩ እውቅና በሚሰጠው ተቋም ይሆናል። ፪/ የጥብቅና ድርጅቶች በስራቸው ያሉ ጠበቆችን ሥልጠና እንዲሰጡ በማኅበሩ እውቅና ሊሰጣቸው ይችላል። ፫/ ማኅበሩ ለጥብቅና ድርጅት ወይም ለተቋም እውቅና ከመስጠቱ በፊት የሚሰጡ የሥልጠና ዓይነቶችን ቀድሞ ማጸደቅ ይኖርበታል፤ ሆኖም በቅድሚያ የጸደቁት የሥልጠና ዓይነቶች በማኅበሩ ወደፊት ሊሻሽሉ፣ ሊታገዱ፣ ወይም ሊሠረዙ ይችላሉ። ፬/ የተከታታይ የሕግ ሥልጠና ሰጪዎች እውቅና የሚያገኙበት ሥነ-ሥርዓት እና መሥፈርቶች በተመለከተ ማኅበሩ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። 1/ Training shall be offered by an institution accredited by the Association; 2/ The Association may give accreditation for the law firms in order to give training for the advocates under their control; 3/ The Association has to approve, in advance, the type of training courses before giving accreditation to the law firm or an institution; however, approved subjects for training may in the future be amended, suspended, or cancelled by the Association; 4/ The procedures and requirements under which institutions that offer legal training are accredited shall be determined by a Directive to be issued by the Association.
፩/ የሥልጠና ተቋሙ በሥልጠና ላይ ያሉትን ሠልጣኞች ሥልጠና ከጀመሩበት እንዲሁም ሥልጠና ያጠናቀቁ ሠልጣኞችን ሥልጠናውን ካጠናቀቁበት ጊዜ ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማኅበሩ ማሳወቅ አለበት። ፪/ ማንኛውም ጠበቃ ማኅበሩ ባሳወቀው የሥልጠና ጊዜ ለመሰልጠን የማያስችል በቂ ምክንያት ካለው ምክንያቱን ለማኅበሩ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት። ፲፫ሺ፭፻፭ 1/ The training institution has the duty to report to the Association about the trainees within one month of the commencement of the training program for those who are already under active training program and from the completion of the training for those who have completed their training; 2/ Any Advocate who is unable, for good cause, to take his training on the program set by the association shall notify in writing this to the association.
፩/ ማንኛውም ጠበቃ በዚህ ንዑስ ክፍል የተቀመጡትን የሕግ ሥልጠና ግዴታዎች ሳያሟላ የቀረ እንደሆነ ማኅበሩ ይህንኑ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት። ፪/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከተከታታይ የሥልጠና ግዴታ ጋር ተያይዞ ያለበቂ ምክንያት የሥልጠና ግዴታውን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆነ ጠበቃ ላይ የዲስፕሊን ክስ ሊመሰርትበት ይችላል። 1/ If any advocate fails to comply with the training obligations provided in this Section, the Association shall notify this fact, in writing, to the Attorney General; 2/ The Attorney General may charge, for the violation of disciplinary rules, an advocate who, without good cause, is not willing to comply with his mandatory training program.
፩/ ማንኛውም ጠበቃ በአሳማኝ ምክንያት ማኅበሩ በሚያወጣው የሥልጠና ጊዜ ውስጥ የሥልጠና ግዴታውን መውሰድ ካልቻለ ጠበቃው ሥልጠናውን ማኅህበሩ ባወጣው ጊዜ ውስጥ መውሰድ ስላለመቻሉና የሥልጠና ጊዜው እንዲራዘምለት ማኅበሩ ከያዘው የሥልጠና ጊዜ ከአንድ ወር በፊት ቀድሞ ለማኅበሩ በማመልከቻ ማሳወቅ አለበት። ፪/ ጠበቃው የሥልጠና ጊዜው እንዲራዘምለት የሚያቀርበው ማመልከቻ ሥልጠናውን መውሰድ እንዳይችል ያደረገውን ምክንያት፣ ሥልጠናውን ለመውሰድ ያደረገውን ጥረት፤ እና በቀጣይ መቼና በምን አግባብ እንደሚወስድ ያለውን እቅድ የሚገልጽ መሆን አለበት። ፲፫ሺ፭፻፮ ፫/ ማኅበሩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት የቀረበለት ማመልከቻ አሳማኝ ሆኖ ካገኘው የሥልጠና ጊዜውን በዚያው ዓመት ውስጥ ጠበቃው በጠየቀው ጊዜ ወይም እራሱ በመሰለው ጊዜ ሊቀይርለት ይችላል፤ ማኅበሩ ጥያቄውን ከተቀበለው የቅያሪውን ሁኔታ ወይም ጥያቄውን ካልተቀበለው ያልተቀበለው መሆኑን በ፲፭ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ለጠበቃው ማሳወቅ አለበት። ፬/ ጠበቃው በዓመት መውሰድ የሚጠበቅበትን የሕግ ሥልጠና ግዴታ በዚያው ዓመት አጠቃሎ መውሰድ ካልቻለ እና ሥልጠናውን ያልወሰደው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ስለመሆኑ ማስረጃ ካቀረበና ማኅበሩ ካመነበት ጠበቃው ያልወሰደውን የሥልጠና ጊዜ ወደ ቀጣይ ዓመት በማሸጋገር በቀጣይ ዓመት መውሰድ ከሚጠበቅበት የሥልጠና ግዴታ ጋር ደርቦ እንዲወስድ ሊፈቅድለት ይችላል። ፲፫ሺ፭፻፯ Training 1/ If any advocate, for good cause, is unable to take the training within the period scheduled by the Association, he has to notify this, a month in advance, by a written application to the Association along with his request for the extension of time; 2/ The application which the advocate submits shall specify the reasons why he was not able to take the training in due time, the effort he made to take the training and his plan as to when and how he would take the training in the future; 3/ If the Association, after considering the application mentioned under Sub- Article (2) of this Article, found the reasons convincing, then it can reschedule the program based on the advocate’s request or, as it may deem necessary, anytime within the given year. If the Association accepts the request, it shall notify the advocate in writing the extension it has made or the rejection of the request within 15 days; 4/ If it is not possible for the advocate to take the training in that same year for reasons beyond his control which is supported by evidence and such reasons have convinced the Association, then the Association may reschedule the training period for the advocate to take the training in the following year in addition to the training he is expected to take in that same year.
፩/ ማንኛውም በጥብቅና ድርጅት ውስጥ ሸሪክ ሆኖ ወይም ተቀጥሮ የሚሰራ ጠበቃ፤ ወይም በግሉ የሚሰራ ጠበቃ እንደጉዳዩ ክብደት እና ቅለት እየታየ በዓመት ከሶስት ጉዳይ ያልበለጠ ነጻ የጥብቅና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፤ አገልግሎቱ የሚሰጠውም፡ሀ) የመክፈል አቅም ለሌላቸው ሰዎች፣ ለ) ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ ለሲቪክ ማኅበራት፤ እና ለማኅበረሰብ ተቋማት፣ ሐ) ፍርድ ቤት የጥብቅና አገልግሎት እንዲያገኙ ለሚጠይቅላቸው ሰዎች፣ መ) ሕግን፤ የሕግ ሙያን እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ለሚሰሩ ኮሚቴዎች እና ድርጅቶች፤ ነው። ፪/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ለሕዝብ ነጻ የጥብቅና አገልግሎት ግዴታውን መወጣቱን የሚገልጽ ማህደር መያዝ የሚኖርበት ሲሆን፤ ማህደሩም እያንዳንዱ አገልግሎት የተሰጠበትን ቀን፣ ዓይነቱን እና የወሰደውን ጊዜ የሚገልጽ መሆን አለበት። ፲፫ሺ፭፻፰
፩/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እያንዳንዱ ጠበቃ በዓመት መስጠት ከሚጠበቅበት የነጻ የጥብቅና አገልግሎት መጠን ሳያልፍ በነጻ የጥብቅና አገልግሎት ሊስተናገዱ የሚገባቸውን ጉዳዮች እያጣራ ለጠበቆች ይመራል። ፪/ እያንዳንዱ ጠበቃ በዓመት መስጠት ከሚጠበቅበት የነጻ የጥብቅና አገልግሎት ግዴታ ሳያልፍ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚመራለትን የነጻ ጥብቅና አገልግሎት ተቀብሎ የመስራት ግዴታ አለበት። ፫/ ማኅበሩ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የነጻ የጥብቅና አገልግሎት እንዲሰጥ የመራለትን ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት በዚህ አዋጅ እና በጠበቆች ሥነ-ምግባር ደንብ መሠረት መፈጸሙን መቆጣጠር እና መከታተል አለበት። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም በጠበቃው በኩል ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት መሰጠት ያለበት ሰው አግኝቶ አገልግሎቱን በነጻ የሰጠ በሆነ ጊዜ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአገልግሎቱን ትክክለኛነትና እውነተኛነት አረጋግጦ እውቅና ሊሰጠው ይችላል። 1/ The Attorney General shall, without passing the limit each advocate should render pro bono service in a given year, identify and assign pro bono cases to advocates; 2/ Each Advocate shall have the obligation, without passing the limit of pro bono cases in a given year, to receive cases referred to him by the Attorney General and render pro bono service; 3/ The Association, based on this Proclamation and the Advocates’ Code of Conduct, shall control and monitor whether an advocate or a law firm has discharged his obligation in handling of the cases assigned to him by the Attorney General for pro bono advocacy service; 4/ Notwithstanding the provision of Sub- Article (1) of this Article, the Attorney General, after ascertaining the accuracy and truthfulness of the service, may recognize the pro bono service for which the advocate rendered for persons in need of the pro bono service.
ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ሥራውን በአግባቡ ሳይወጣ በመቅረቱ ምክንያት በደንበኛው ላይ ሊደርስ ለሚችል ጉዳት ካሳ የሚሆን የሙያ ኃላፊነት መድን ሊይዝ ይችላል። ፲፫ሺ፭፻፱
፩/ ለጠበቃ ወይም ለጥብቅና ድርጅት የሙያ ኃላፊነት መድን የሰጠ መድን ሰጪ የመድን ውሉ ሲቋረጥ ወይም ግዴታው እንዳይፈጸም ሊያደርግ የሚችል ሁኔታ ሲፈጠር ሁኔታውን ወዲያውኑ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማሳወቅ አለበት። ፪/ መድን ሰጪው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተቀመጠውን ግዴታውን ባለመወጣቱ ለሚደርሰው ጉዳት ኃላፊነት አለበት።
፩/ ከሙያ ሥራው ጋር በተገናኘ በይዞታው ወይም በአስተዳደሩ ሥር የሚገኝን የደንበኛው ወይም የሶስተኛ ወገንን ንብረት አስተዳደርን ጥበቃ ከራሱ ንብረት ፍጹም በማይገናኝበት ሁኔታ ለይቶ ማስተዳደር አለበት፤ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተጠቀሱትን የደንበኛው ወይም የሶስተኛ ወገን ንብረቶች የሚመለከቱ ማናቸውንም ሠነዶች ጉዳዩ ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አምስት ዓመት ድረስ የመያዝ ግዴታ አለበት። Every advocate or law firm has the following obligations: 1/ Administer and keep his client’s or third
፩/ በጠበቃው ወይም የጥብቅና ድርጅቱ እጅ የሚገኝ የደንበኛ ገንዘብ ከጠበቃው ወይም ከጥብቅና ድርጅቱ በተለየ ሂሳብ ውስጥ መቀመጥ አለበት። ፲፫ሺ፭፻፲ ፪/ ቦርዱ ጠበቆች ወይም የጥብቅና ድርጅቶች የደንበኞች አደራ ሂሳብ ለመያዝ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች በመመሪያ ሊወሰን ይችላል። ፫/ የደንበኛው የአደራ ሂሳብ በጠበቃው ወይም በጥብቅና ድርጅቱ ማንቀሳቀስ የሚቻለው ክፍያ ሊፈፀምባቸው የሚገቡ ሥራዎች መከናወናቸውን እና በደንበኛው ሥም መደረግ ያለባቸው ወጪዎች በበቂ ማስረጃ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። ፬/ ጠበቃው ወይም የጥብቅና ድርጅቱ የደንበኛ ወይም የሶስተኛ ወገን ጥቅም ያለበት ገንዘብ ወይም ሌላ ንብረት ሲቀበል ለደንበኛው ወይም ለሶስተኛ ወገን ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት። ፭/ በዚህ አዋጅ ከተመለከተው ወይም በሕግ ወይም ከደንበኛው ጋር በተደረገ ስምምነት ካልተፈቀደ በስተቀር አንድ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ለክፍያ ያልዋለ በአደራ ሂሳብ ውስጥ የተቀመጠን ገንዘብ ደንበኛው ወይም መብት ያለው ሶስተኛ ወገን ሲጠይቅ ወይም ጉዳዩ ሲጠናቀቅ ወዲያውኑ ከበቂና የተሟላ ሪፖርት ጋር ማስረከብ አለበት። 1/ A client’s money which is under the possession of an advocate or a law firm shall be kept in a different account from that of the advocate’s or the law firm’s private account; 2/ The Board, by Directive, may determine the requirements advocates or law firms must fulfil to keep their clients’ trust account; 3/ The advocate or the law firm can only transact his/its client’s trust account and pay money when activities, which need payment, are undertaken and the expenses are supported by evidences issued in the name of the client; 4/ The advocate or the law firm, when it receives money or other property that involves the interest of the client or the third party, shall immediately notify the situation to his/its client or to the third
በዚህ አዋጅ መሠረት የጸና የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው ቢያንስ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠበቆች አንድ ላይ በመሆን የጥብቅና ድርጅት ማቋቋም ይችላሉ። ፲፫ሺ፭፻፲፩ At least two or more advocates, who have a valid advocacy service license issued under the provisions of this Proclamation, may together establish a law firm.
፩/ የጥብቅና ድርጅት ዋነኛ ተግባር የጥብቅና አገልግሎት መስጠት ነው። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የጥብቅና ድርጅት ከጥብቅና አገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች አገልግሎቶች ሊሰጥ ይችላል፤ ዝርዝር አፈጻጸሙ ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። 1/ The main objective of a law firm is providing advocacy service; 2/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (1) of this Article, a law firm can render services related with advocacy service; the particulars shall be determined by a Directive to be issued by the Attorney General.
፩/ የጥብቅና ድርጅት ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር አደረጃጀት ይኖረዋል። ፪/ የጥብቅና ድርጅት፡ሀ) ውል መዋዋል፣ ለ) የንብረት ባለቤት መሆን፣ ሐ) በሥሙ መክሰስና መከሰስ እና የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት የሚኖረው ሌሎች መብት እና ግዴታዎች ይኖረዋል። ፫/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪኮች ለሶስተኛ ወገን የሚኖርባቸው ኃላፊነት በጥብቅና ድርጅቱ ውስጥ ባላቸው የመዋጮ ድርሻ ልክ የተወሰነ ይሆናል። ፬/ የጥብቅና ድርጅት አባላትን የሚመለከት ለውጥ ቢመጣም የጥብቅና ድርጅት ህልውና ይቀጥላል። ፭/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶፪ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የጥብቅና ድርጅት የጥብቅና አገልግሎት መስጠቱ በኢትዮጵያ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ሕጎች መሠረት አገልግሎቱን የንግድ ወይም የኢንቨስትመንት ሥራ አያሰኘውም። ፲፫ሺ፭፻፲፪ Responsibility of a Law Firm 1/ The organizational structure of a law firm shall be Limited Partnership; 2/ A law firm shall have the following rights and obligations: a) to make contract; b) to own property; c) to sue and be sued on its own name and has rights and obligations which other juridical persons have. 3/ The liability of partners in a law firm to third parties shall be limited to the share each partner has in the firm; 4/ The law firm shall continue to exist despite changes on the membership of the firm; 5/ Without prejudice to Article 52 Sub- Article (1) of this Proclamation, the provision of advocacy service by a law firm does not make the service a business or investment as defined under the Ethiopian Commercial Code and the Investment Law.
፩/ የጥብቅና ድርጅት አባላት ማንኛውንም ሥያሜ የጥብቅና አገልግሎት ድርጅቱ መጠሪያ እንዲሆን መምረጥ እና መወሰን ይችላሉ። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ ቢኖርም ለጥብቅና ድርጅቱ መጠሪያነት የተመረጠው ሥም በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚከተሉት ምክንያቶች ተቀባይነት ላይኖረው የሚችለው፡ሀ) ከሌላ የጸና የጥብቅና ድርጅት ሥም ጋር ተመሳሳይ ከሆነ፣ ለ) ደንበኞች ድርጅቱን ከሌላ የጥብቅና ድርጅት በቀላሉ መለየት እንዳይችሉ በሚያስችል መልኩ ሊያሳስት ወይም ሊያደናግር የሚችል ከሆነ፣ እና ሐ) ለሕግ ወይም ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ ከሆነ። ፫/ የጥብቅና ድርጅት ሥም የጥብቅና ድርጅት መሆኑን የሚያመለክትና ከሥሙ በስተመጨረሻ “ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር” ወይም (“ኃ.የተ.የሽ.ማ”) የሚል ሐረግ ያለው መሆን አለበት። ፬/ በጥብቅና ድርጅቱ ሥም የሚወጡ ሠነዶች በሙሉ በግልጽ ሥሙን እና “ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር” የሚለውን ሐረግ መያዝ አለባቸው። 1/ The members of a law firm may choose and decide any name to be their firm’s name. 2/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (1) of this Article, the name chosen to be the name of the law firm may be rejected by the Attorney General for the following reasons: a) if it is similar with the name of another existing law firm; b) if the name misrepresents or confuses clients in a way not easily to differentiate it from another law firm; and c) when it is contrary to law or public morality. 3/ To indicate the advocacy service, the firm name shall be followed by the words “Limited Partnership” or the abbreviation “L.P.” 4/ All Documents issued in the name of the law firm shall clearly contain its name followed by “Limited Partnership”.
፩/ የጥብቅና ድርጅት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በመመዝገብ ይቋቋማል። ፲፫ሺ፭፻፲፫ ፪/ የጥብቅና ድርጅት ለማቋቋም የሚከተሉት ሠነዶች ከማመልከቻ ጋር ተያይዘው ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መቅረብ አለባቸው፡ሀ) የሸሪኮቹን ሙሉ ሥምና ፊርማ የያዘ ማመልከቻ፣ ለ) የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ፤ ሐ) የሸሪኮቹ የጥብቅና ፍቃድ ቅጂ፣ እና መ) ሸሪኮች ድርጅቱን ለመመስረት የተስማሙበትን የሽርክና ስምምነት፤ የጥብቅና ድርጅቱን ሥም፤ የሽርክና ማኅበሩን የቆይታ ዘመን፤ የድርጅቱን ዓላማ በአጭሩ የተገለጸበት እና በምስረታ ሂደት ድርጅቱን የሚወክለው ሸሪክ የተሰየመበት ቃለ-ጉባዔ። ፫/ የጥብቅና ድርጅት መመስረቻ ጽሑፍ በንግድ ሕጉ ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር መመስረቻ ጽሑፍ ሊያካትታቸው የሚገቡ ዝርዝሮችን ማካተት ይኖርበታል። ፬/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የቀረቡለት ሠነዶች ከዚህ አዋጅና አግባብነት ካላቸው ሌሎች ሕግጋት ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ካረጋገጠ ማመልከቻውን በተቀበለ በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ የጥብቅና ድርጅቱን ይመዘግባል፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ይሰጣል። ፲፫ሺ፭፻፲፬ ፭/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የቀረቡለት ሠነዶች ከዚህ አዋጅና አግባብነት ካላቸው ሌሎች ሕጎች ጋር የሚጣረሱ ናቸው ብሎ ካመነ ማመልከቻውን በተቀበለ በ፳ የሥራ ቀናት ውስጥ ውድቅ ማድረግና ማመልከቻው ውድቅ እንዲሆን መነሻ የሆነውን ምክንያት በመግለጽ ለአመልካቹ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት። ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) መሠረት ያቀረበው ማመልከቻ ውድቅ የተደረገበት አካል ቅሬታውን ማመልከቻው ውድቅ መደረጉን ባወቀ በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ ለቦርዱ ማቅረብ ይችላል። ፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፮) መሠረት ቦርዱ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔ በተሰጠ በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። Formation 1/ A law firm shall be established upon registration by the Attorney General; 2/ The following documents shall be submitted to the Attorney General, along with the application, to form the firm: a) an application that contains the full name of the partners and their signature; b) Memorandum of Association of the firm; c) copies of the advocacy licenses of each partner; and d) the Partnership agreement with which the partners agreed to form the firm; name of the firm; duration of the partnership; a brief minutes which purports the purpose of the firm and minute in which the representative of the firm nominated in the process of establishment. 3/ The Memorandum of Association of a law firm shall contain the particulars, stated in the Commercial Code, which Memorandum of Association of Limited Liability Partnership should contain; 4/ The Attorney General, after verifying that the documents submitted to it are in compliance with the requirements of this Proclamation and other relevant laws, shall, within 15 working days of receiving the application, register the firm and issue certificate of registration; 5/ If the Attorney General is convinced that the documents submitted to it are in contradiction with the provisions of this Proclamation and other relevant laws, it shall, within 20 working days, reject the request and notify the applicant, in writing, the grounds for rejection; 6/ The person whose application was rejected pursuant to Sub-Article (5) of this Article may file his complaints to the Board within 15 working days of knowing the rejection of the application; 7/ A party who has grievance on the decision given by the Board as provided under Sub-Article (6) of this Article, may lodge an appeal to the Federal First Instance Court within 15 working days of the decision.
፩/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪኮች ዋነኛው መዋጮ ክህሎት መሆን አለበት። ፪/ ሸሪኮች መዋጮዎችን በገንዘብ ወይም በዓይነት ማዋጣት ይችላሉ። ፫/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪኮች የመዋጮ መጠን የድርጅቱን ዓላማ ለማሳካት የሚበቃ መሆን ያለበት ሆኖ በገንዘብ የሚደረገው መዋጮ ከሃምሳ ሺህ ብር ማነስ የለበትም። ፬/ ገንዘብ ባልሆነ ማናቸውም መንገድ በጥብቅና ድርጅት ሸሪክ የሚደረግ መዋጮ ዋጋ በሁሉም ሸሪኮች ስምምነት እና አግባብነት ባላቸው ሕግጋትና ደንቦች ይወሰናል። ፲፫ሺ፭፻፲፭ 1/ The main contribution of partners of a law firm shall be their skill. 2/ Partners may make their contributions in cash or in kind. 3/ The amount of contribution of partners of a law firm shall be sufficient to materialize the purpose of the law firm; In this regard, the contribution in cash shall not be less than Fifty Thousand Birr. 4/ The value of contributions of partners other than cash shall be determined by the agreement of all the partners and relevant laws and Regulations.
፩/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪክ የሚከተሉት መብቶች አሉት፡ሀ) በጥብቅና ድርጅቱ ስብሰባዎች የመካፈል እና ድምጽ የመስጠት፣ ለ) በድርሻው መጠን ከጥብቅና ድርጅቱ ትርፍ ወይም የጥብቅና ድርጅቱ ሲከስም ከተጣራው የማኅበሩ ሀብት ከሚተርፈው ሀብት የመካፈል፤ ሐ) የጥብቅና ድርጅቱን አጠቃላይ አሠራር የመከታተል፣ የማወቅ፤ መ) በሽርክና ስምምነት፣ በዚህ አዋጅና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች የተመለከቱ፣ ወይም ከሽርክና ማኅበሩ ተፈጥሮ የሚመነጩ ሌሎች መብቶችና ጥቅሞችን የመጠቀም። ፪/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪክ የሚከተሉት ግዴታዎች አሉበት፡ሀ) ለጥብቅና ድርጅቱ መክፈል የሚጠበቅበትን መዋጮ በወቅቱ መክፈል፣ ለ) በማናቸውም ጊዜ የጥብቅና አገልግሎት ድርጅቱን ዓላማ ለማሳካት በትጋት የመሥራት፣ ሐ) ለራሱ ጥቅም የሚያስገኝ ቢሆንም ባይሆንም የጥብቅና ድርጅቱን ጥቅም ከሚጻረሩ ድርጊቶች ወይም ኃላፊነትን ከሚያጓድሉ ተግባራት መታቀብ፣ እና ፲፫ሺ፭፻፲፮ መ) በሽርክና ስምምነት፤ በዚህ አዋጅ፣ አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች፣ በሽርክና ስምምነት የተመለከቱ ወይም ከሽርክና ማኅበሩ ተፈጥሮ የሚመነጩ ሌሎች ግዴታዎችን የመወጣት። 1/ A partner of a law firm shall have the following rights: a) the right to participate and vote in the meetings of the firm; b) based on his contribution, to share profits of the firm or the proceeds of liquidated assets of the firm at the time of dissolution; c) to get information about and follow up the activities of the law firm; d) get rights and benefits emanates from the partnership agreement, this Proclamation and other relevant laws or other rights and benefits that emanate from the nature of the firm; 2/ The partner of a law firm shall have the following obligations: a) pay the firm’s membership contribution on time; b) work diligently, at any time, to materialize and achieve the purpose of the law firm; c) refrain from acts that may hamper discharging his responsibilities and activities that are detrimental to the interests of the law firm, whether to his personal benefit or not; and d) Discharge his obligations provided in the partnership agreement, in this Proclamation, other relevant laws or obligations indicated by the partnership agreement or emanate from the nature of limited partnerships.
በጥብቅና ድርጅቱ የሽርክና ስምምነት በተለየ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር የማኅበሩ ሸሪኮች የድርጅቱን ትርፍ እና ኪሳራ ወይም የጥብቅና ድርጅቱ ሲከስም ከተጣራው የማኅበሩ ሀብት የሚተርፈውን ሀብት በድርጅቱ ውስጥ ባላቸው ድርሻ መጠን የመካፈል መብት አላቸው። Unless otherwise provided in the partnership agreement of the law firm, the partners of the law firm shall distribute, among themselves, profit and loss or proceeds of liquidated assets of the firm at the time of dissolution in accordance with the share contributions they hold in the firm.
፩/ አግባብነት ባለው ሌላ ሕግ የተጣለው ክልከላ እንደተጠበቀ ሆኖ የጥብቅና ድርጅቱን ለሚለቅ ሸሪክ የድርሻው ዋጋ እና የትርፍ ድርሻው ሊከፈለው ይገባል፤ ፪/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪክ በሚሞት ጊዜ ሸሪኩ ሊከፈለው የሚገባ ያልተከፈለው የትርፍ ድርሻ ለሕጋዊ ወራሾቹ ይተላለፋሉ። 1/ Without prejudice to the restrictions imposed by other laws, a partner who leaves the firm shall be paid the value of his share and dividend; 2/ When a partner of a law firm dies, a dividend which should have been paid to him shall devolve to his heirs.
የጥብቅና ድርጅት ባለቤት መሆን የሚችሉት የጸና የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው ጠበቆች ብቻ ናቸው። ፲፫ሺ፭፻፲፯ The owner of a Law Firm shall only be Advocates who have a valid advocacy license.
፩/ በጥብቅና ድርጅት ውስጥ ሸሪክ ሆኖ የሚሠራ ማንኛውም ጠበቃ ወይም በጥብቅና ድርጅቱ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ሠራተኛ የሽርክና ወይም የሥራ ቅጥር ዘመኑ ጸንቶ ባለበት ጊዜ መሳተፍ የማይችልባቸው ተግባራት፡ሀ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሌላ የጥብቅና ድርጀት ሸሪክ ወይም ሠራተኛ መሆን፣ ለ) በሚሠራበት የጥብቅና ድርጅት ውስጥ የተጣለበትን ግዴታ ለመወጣት አስፈላጊ መሆኑ በድርጅቱ ቀደም ብሎ ካልተፈቀደ በስተቀር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሌላ የጥብቅና ድርጅትን መርዳት ወይም መተባበር፣ ሐ) የግል የጥብቅና አገልግሎት መስጠት፤ መ) የጥብቅና ድርጅቱ ሳያውቅና ሳይፈቅድ በራሱ ሥም የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ ከደንበኛ መቀበልና ለግል ጥቅም ማዋል፤ ሠ) ማንኛውንም ከጥብቅና ድርጅቱ ዓላማና ተግባር ጋር የሚጣረስና የጥቅም ግጭት ሊፈጥር የሚችል ሥራ በግሉም ሆነ ተቀጥሮ መስራት። ፲፫ሺ፭፻፲፰ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም ማንኛውም ጠበቃ በጥብቅና ድርጅት ሸሪክ ወይም ተቀጣሪ ከመሆኑ በፊት የያዘው ጉዳይ ደንበኛው በተለየ ሁኔታ ካልተስማማ በስተቀር በተያዘበት አግባብ ፍጻሜ ያገኛል። Law Firms 1/ An advocate, who is a partner or employee of a law firm, during the time of his membership to the partnership or employment engagement to a specific law firm, shall be restricted to undertake the following activities: a) directly or indirectly, from being a partner or employee of another law firm; b) from directly or indirectly assisting or collaborating with another law firm, unless the law firm to which he is a partner or an employee, with the view to discharging his assigned firm duty, authorize him in advance to do so; c) from providing advocacy service in private; d) receiving advocacy service fee from a client and use the money for his personal benefit without the knowledge and permission of the law firm; e) engagement in any other business, either personally or as an employee, that may contradict with the purpose and activities of, and creates conflict with the interests of, the law firm. 2/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (1) of this Article, unless the client agrees differently, activities commenced by any partner or employed advocate prior to engagement with the law firm shall be completed on the basis of prior arrangements.
፩/ የጥብቅና ድርጅት በሸሪኮች ውሳኔ በተሾሙ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቁጥር ባላቸው ሥራ-አስኪያጆች ይተዳደራል። ፪/ የጥብቅና ድርጅት ሥራ-አስኪያጅ ከድርጅቱ ሸሪኮች መካከል የሚመረጥ መሆን አለበት። ፫/ የጥብቅና ድርጅት ሥራ-አስኪያጅ ድርጅቱን በዋናነት ያስተዳድራል፣ ማንኛውንም ሕጋዊ የድርጅቱን መብት ለማስጠበቅና የድርጅቱን ግዴታ ለመወጣት የጥብቅና ድርጅቱን ይወክላል፣ የድርጅቱ ተጠሪ ይሆናል፣ ድርጅቱን ወክሎ ይከሳል፣ ይከስሳል፣ ይከራከራል፣ ጠበቃ ወይም ሶስተኛ ወገን ይወክላል። ፬/ የጥብቅና ድርጅቱ ሥራ-አስኪያጅ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት የግል ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሚፈጸመው ስህተት ምክንያት በሶስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ሥራ-አስኪያጁ እና የጥብቅና ድርጅቱ በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ ይሆናሉ። ፭/ ጉዳት የደረሰበት ሰው ጉዳት አድራሹ ሥራአስኪያጅ ሥራውን ለማከናወን ኃላፊነት ያልተሰጠው መሆኑን የሚያውቅ የነበረ ከሆነ የጥብቅና ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም። ፲፫ሺ፭፻፲፱ ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፬) እና (፭) ከተመለከተው ውጪ ከውል ወይም በሌላ በማንኛውም ሁኔታ ለሚመጣ ግዴታ ኃላፊ የሚሆነው የጥብቅና ድርጅቱ ነው። 1/ A Law Firm shall be managed by one or more managers appointed by the partners’ decision. 2/ The manager of the law firm shall be elected from among partners of the law firm. 3/ The manager of a law firm shall mainly administer the firm; represent the law firm to defend its interests and discharge the firm’s obligations; represent the firm; on behalf of the firm sue, defend, contest, give power of attorney to an advocate or a third party. 4/ The manager of the law firm and the firm shall be jointly and severally liable for the damages caused to third parties by the actions of the manager while performing his duty with the view to get personal gain. 5/ The Law Firm shall be relieved from liability where the injured party knew of the fact that the manager who caused the damage did not have the power to carry out the undertaking. 6/ The Law Firm shall be liable for any obligation except the one stated in Sub- Articles (4) and (5) of this Article whether arising out of contract or any other situation.
፩/ ሥራ-አስኪያጁ በሽርክና ስምምነቱ፣ በዚህ አዋጅ እና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች መሠረት የተጣሉበትን ግዴታዎች መወጣት አለበት። ፪/ የጥብቅና ድርጅት ሥራ-አስኪያጅ ድርጅቱ፣ በውስጠ ደንቦች፣ በሽርክና ስምምነቱ፣ በዚህ አዋጅ እና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች መሠረት የተጣሉበትን ግዴታዎች መወጣቱን ማረጋገጥ አለበት። ፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) የተጠቀሰው ጠቅላላ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ሥራ-አስኪያጁ፡ሀ) አጠቃላይ የጥብቅና ድርጅቱን የጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ እንቅስቃሴ የመቆጣጠር፣ ለ) ከደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መቀበል እና መፍታት፤ አግባብ ሆኖ ሲያገኘው ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ፣ ሐ) የድርጅቱን የሥራ ክንውን ሪፖርት የማዘጋጀትና ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የማቅረብ፣ መ) ድርጅቱን ኦዲት የማስደረግና መክፈል የሚጠበቅበትን ታክስ በታክስ ሕጉ መሠረት በወቅቱ የማሳወቅና የመክፈል ግዴታ አለበት። ፲፫ሺ፭፻፳ 1/ The manager shall be responsible to discharge his duties in accordance with the partnership agreement, this Proclamation and other relevant laws; 2/ The manager of a law firm shall ensure that the firm discharges its duties and responsibilities provided in the by-laws of the partnership, the partnership agreement, this Proclamation and other relevant laws; 3/ Without prejudice to the general provisions of Sub-Articles (1) and (2) of this Article, the manager shall perform the following activities: a) monitor the activities of delivering the advocacy service by the firm in general; b) receive and solve grievances presented by clients and refer it to the appropriate body when he finds it appropriate; c) prepare the performance report of the firm and report it to the appropriate body; d) get the firm audited; declare and pay taxes according to the tax law.
፩/ የጥብቅና ድርጅቱ በሽርክና ስምምነት ወይም ተፈጻሚነት ባለው ሌላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተሰወነ በስተቀር ቢያንስ ከግማሽ በላይ ድርሻ ያላቸው አባላቱ ከተገኙ ምልዓተ-ጉባዔ ይሆናል። ፪/ የጥብቅና ድርጅቱ ሸሪኮች በተለየ ሁኔታ ካልተስማሙ በስተቀር የጥብቅና ድርጅቱ ውሳኔዎች የሚጸድቁት ስብሰባ ላይ ከተገኙት ሸሪኮች ቢያንስ ፷ በመቶ ድርሻ ያላቸውን ድምጽ ድጋፍ ሲያገኝ ነው። ፫/ የጥብቅና ድርጅቱ ሸሪኮች በተለየ ሁኔታ ካልተስማሙ በስተቀር የማኅበሩን መመስረቻ ጽሑፍ ለማሻሻል ስብሰባ ላይ ከተገኙት አባላት የሁለት ሶስተኛ ይሁንታ ድምጽ ማግኘት ይኖርበታል። ፬/ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ የጥብቅና ድርጅት የስብሰባ ሥነ-ሥርዓትና የውስጥ አሠራሩን በተመለከተ ውስጠ-ደንብ ሊያወጣ ይችላል። 1/ Unless otherwise provided by the firm’s partnership agreement or other applicable laws, there shall be a quorum to conduct the general meeting when at least members who have more than half of the share attend the meeting; 2/ Unless the partners of the law firm agreed otherwise, decisions shall be passed when partners who have at least 60 percent share of the capital of the firm vote in favour; 3/ Unless the partners of the law firm agreed otherwise, to amend the Memorandum of Association of the law firm 2/3 (two third) of the partners who attend the meeting shall vote in favour; 4/ Without prejudice to the provisions of this Article, the law firm may determine meeting procedures and Internal Procedure of the law firm by issuing By-laws.
ማንኛውም የጥብቅና ድርጅት ወይም ሸሪክ የግብር አከፋፈል አግባብነት ባላቸው የሽርክና ማኅበርን የተመለከቱ የግብር ሕጎች የሚወሰን ይሆናል። The payment of tax of any law firm or a partner shall be decided according to relevant tax laws of partnership association.
፩/ የጥብቅና ድርጅት ህልውና በሸሪኮቹ ሞት፣ መልቀቅ፣ ችሎታ ማጣት ወይም ሸሪኮቹን በሚያውክ ማናቸውም ለውጥ አይፈርስም። ፲፫ሺ፭፻፳፩ ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የጥብቅና ድርጅት ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ሊፈርስ ይችላል፡ሀ) የሽርክና ማኅበሩን ለማፍረስ ሸሪኮች ሲስማሙ፣ ለ) የጥብቅና ድርጅቱ መክሰሩ በፍርድ ቤት ሲታወጅ፣ ሐ) የሁሉም ሸሪኮቹ የጥብቅና ፍቃድ ሲሰረዝ፣ ወይም መ) የጸና የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው ሸሪኮች ቁጥር ወደ አንድ ዝቅ ሲልና ቁጥራቸው በጎደለ በስድስት ወራት ውስጥ የጸና የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው ሸሪኮቹ ቁጥር ቢያንስ ወደ ሁለት ካላደገ። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ፊደል-ተራ (መ) ድንጋጌ ቢኖርም የስድስት ወራት የጊዜ ገደብ ከማለፉ በፊት በጥብቅና ድርጅቱ የቀረው ሸሪክ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጥያቄውን አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የስድስት ወራቱ የጊዜ ገደብ በሶስት ወራት እንዲራዘም ሊፈቅድ ይችላል። ፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) በተደነገገው መሠረት ካልሆነ በስተቀር የሸሪኮች ቁጥር ወደ አንድ ዝቅ ያለ መሆኑን የሚያውቅ ሸሪክ የጥብቅና ድርጅቱ በዚህ ሁኔታ ከስድስት ወራት በላይ ሥራውን እንዲቀጥል ካደረገ ለድርጅቱ እዳ እና ግዴታዎች ከጥብቅና ድርጅቱ ጋር በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናሉ። ፭/ የጥብቅና ድርጅት ሲፈርስ ከመዝገብ ይሰረዛል። ፲፫ሺ፭፻፳፪ ፮/ ኃላፊነቱ የተወሰነ ማኅበርን መፍረስ የሚመለከቱ በንግድ ሕጉ ወይም በሌሎች ሕጎች የተቀመጡ ድንጋጌዎች የጥብቅና ድርጅት መፍረስን በሚመለከት ተፈጻሚ ይሆናሉ። 1/ A law firm shall not be dissolved because of the death of partners, when a partner leaves the firm, loss of capacity of a partner or any change that may put the partners in trouble; 2/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (1) of this Article, a law firm may be dissolved in one of the following grounds: a) when the partners agree to dissolve the law firm; b) when a court declares the law firm bankrupt; c) when the advocacy licenses of all partners are revoked; or d) when the number of partners who have valid advocacy license is reduced to one and it is not possible to increase the number of partners who have valid advocacy license at least to two, within six months. 3/ Notwithstanding the provision of Sub- Article (2) paragraph (d) of this Article, if the remaining partner presents his request to the Attorney General before the lapse of the six month period and where the Attorney General finds it necessary, it may allow the extension of the six months period by three months; 4/ Unless otherwise provided in Sub-Article (3) of this Article, the partner shall be jointly and severally liable with the law firm for obligation of the law firm where he continues the operation of the firm for more than six months after being aware of the fact that the number of partner of the partnership reduced to one; 5/ A law firm, when dissolved, shall be cancelled from the register; ‹ 6/ Provisions related to the dissolution of limited liability partnership provided in the Commercial Code and other laws, shall apply to govern the dissolution of a law firm.
በሽርክና ስምምነቱ ከተፈቀደው ውጭ በያዙት ጉዳይ ላይ ያልተገባ ተግባር ካልፈፀሙ ወይም ሥራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ወይም በማታለል ወይም አውቀው ባደረሱት ጉዳት ካልሆነ በስተቀር ከጥብቅና አገልግሎት መስጠት ጋር በተያያዘ በጠበቆችና ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች አማካኝነት በደንበኞች እና ሌላ ሶስተኛ ወገን ላይ የሚደርስ ጉዳት በጥብቅና ድርጅቱ የደረሰ ጉዳት እንደሆነ ተቆጥሮ ድርጅቱ ኃላፊነት ይወስዳል። The law firm shall be liable to clients and other third parties for damages caused, in the normal course of service, by advocates and support staff unless the advocates and support staff, contrary to the partnership agreement, committed unacceptable act on the cases at their hand or failed to discharge their respective duties or committed cheating or deliberately caused damages.
፩/ የጥብቅና ድርጅቱ ገንዘብ ጠያቂዎች ከድርጅቱ ማናቸውም ሀብት ላይ ገንዘብ መጠየቅ ይችላሉ። ፪/ ከጥብቅና ድርጅቱ ላይ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ከሸሪኮች የግል ንብረት ላይ ገንዘብ መጠየቅ አይችሉም። 1/ Creditors who demand payment from the law firm can exercise their right against any asset of the firm; 2/ Creditors who demand payment from the law firm have no right to proceed against the personal properties of the partners of the firm.
በዚህ አዋጅ እና በንግድ ሕጉ ስለኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር የተቀመጡት ግዴታዎች እንደተጠበቁ ሆነው የጥብቅና ድርጅት የሚከተሉት ግዴታዎች አሉበት፡- ‹ ‹፩/ ከሸሪኮቹ የሙያ ኃላፊነት መድን በተጨማሪ የጸና የሙያ ኃላፊነት መድን መግዛትና ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ይዞ መገኘት፣ ፲፫ሺ፭፻፳፫ ፪/ ተገቢውን የሂሳብ ሠነድ መያዝ፣ ፫/ የደንበኞቹን ምስጢር መጠበቅ፣ ፬/ በውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ኦዲት መደረግ፣ ፭/ ይህንን አዋጅ፣ አግባብነት ያላቸውን ሌሎች ሕጎችና የሙያ ሥነ-ምግባር ደንቦችን ማክበር፣ እና ፮/ በሽርክና ስምምነቱ ላይ ማሻሻያዎች ሲያደርግ ማሻሻያው በተፈረመ በ፴ ቀናት ውስጥ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ግልባጩን የማቅረብ። Without prejudice to the provisions of this Proclamation and the provisions of the Commercial Code with regard to limited partnership, a law firm has the following obligations: 1/ The obligation to buy and secure professional indemnity insurance in addition to the policies bought by the partners; 2/ Keep appropriate books of account; 3/ Keep the confidential information of its clients; 4/ Get audited by External Auditor annually; 5/ Respect and observe this Proclamation, other relevant laws and Professional Code of Conducts; and 6/ Submit, within 30 days of execution, copies of minutes of amendment of the partnership agreement to the Attorney General.
፩/ ማንኛውም የጥብቅና ድርጅት ሸሪክ ከማኅበሩ ስለሚወጣበት ሁኔታ እና የወጣ ሸሪክን ድርሻ በተመለከተ ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበርን የተመለከቱ አግባብነት ያላቸው የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ፪/ በዚህ አዋጅ ከሚመራው ጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ተፈጥሮ ጋር የማይቃረኑ እስከሆነ ድረስ የንግድ ሕጉ እና አግባብነት ያላቸው ሌሎች ሕጎች በዚህ አዋጅ በሚቋቋም የጥብቅና ድርጅት ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ። ፲፫ሺ፭፻፳፬ 1/ The relevant Commercial Code provisions on Limited Liability Partnership shall be applicable regarding conditions of the departure of a partner from the law firm and share of a partner leaving the law firm; 2/ Commercial Code of Ethiopia and other relevant laws shall be applicable on a law firm constituted under this Proclamation as long as they do not contradict with the nature of the law firm governed under this Proclamation.
፩/ የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ማኅበር ከዚህ በኋላ “ማኅበሩ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። ፪/ ማኅበሩ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት አለው። ፫/ ማኅበሩ ሁሉንም ፍቃድ የተሰጣቸው የፌደራል ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በአባልነት ያቀፈ ነው። ፬/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጥብቅና ፍቃድ ሲሰጠው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማኅበሩ አባል ይሆናል። 1/ The Federal Advocates’ Association, herein after called the “The Association” is hereby established by this Proclamation. 2/ The Association has its own legal personality. 3/ The Association has all licensed federal advocates and law firms as its members. 4/ Every advocate or law firm shall become member of the Association without any precondition when he/it is issued with the advocacy license.
የማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ቅርንጫፍ ቢሮዎች ሊከፍት ይችላል። The Head Office of the Association shall be in Addis Ababa and it may open branch offices in different parts of the Country as may be necessary.
፩/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይህ አዋጅ ከጸናበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ የማኅበሩን የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ይጠራል። ፲፫ሺ፭፻፳፭ ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የተጠራው ጠቅላላ ጉባዔ የማኅበሩን አመራር አካላት ይሰይማል። 1/ The Attorney General shall call the Association’s first general meeting within six months’ of entering into force of this Proclamation; 2/ The meeting called pursuant to Sub- Article (1) of this Article shall nominate the management of the Association.
፩/ የማኅበሩ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ከአባላቱ የሚሰበሰብ መዋጮ ይሆናል። ፪/ ማኅበሩ ከሌሎች ሕጋዊ ምንጮች የሚያገኛቸው ገቢዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ራሱን እስኪችል ድረስ ከመንግስት የገንዘብ እና ሌሎች ድጋፎች ይደረጉለታል። 1/ The main source of income of the Association shall be periodic contributions of its members; 2/ Without prejudice to the incomes the Association may derive from other sources, it shall get financial and other supports from the Government until it is self sufficient.
፩/ ማኅበሩ የሚከተሉት አመራር አካላት ይኖሩታል፡ሀ) ጠቅላላ ጉባዔ፣ ለ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ሐ) ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት፣ መ) ዋና ጸሐፊ፣ እና ሠ) ሌሎች ሠራተኞች። ፪/ ማኅበሩ እንደ አስፈላጊነቱ ሥራውን ለማከናወን ኮሚቴዎች ወይም በሥሩ የሚሰሩ የሥራ ክፍሎች ሊያደራጅ ይችላል። Association 1/ The Association shall have the following administrative organs: a) General Meeting; b) Executive Committee; c) President and Vice President; d) General Secretary; and e) Other Staff. 2/ The Association may, to discharge its activities properly, set up committees or departments under it as may be necessary.
፩/ ተከታታይ የሕግ ሥልጠናን በበላይነት ይመራል፤ የተከታታይ የሕግ ሥልጠናን የሚመለከቱ የአዋጁን ድንጋጌዎች ያስፈጽማል፤ ፪/ የተከታታይ የሕግ ሥልጠና ሰጪዎችን እውቅና ይሰጣል፤ ፲፫ሺ፭፻፳፮ ፫/ ይህንን አዋጅ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ሕጎች በሚጥሱ የተከታታይ የሕግ ሥልጠና ሰጪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤ ፬/ ከተከታታይ የሕግ ሥልጠና ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ክፍያዎችን በተመለከተ መመሪያ ያወጣል፤ ያስፈጽማል፤ ፭/ የአደራ ሂሳብ አፈጻጸምን አስመልክቶ መመሪያ አዘጋጅቶ ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀርባል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ ፮/ ማናቸውም የአደራ ሂሳብ አያያዝና አመራር በትክክል እየተካሄደ መሆኑን ለመቆጣጠር በማናቸውም ጊዜ የኦዲት ምርመራ እንዲካሄድ ሊያደርግ ይችላል፤ ፯/ ከአደራ ሂሳብ አያያዝ ጋር የሚነሱ የደንበኞች ቅሬታዎችን ይቀበላል፣ ማናቸውንም ሰው በማነጋገር ምርምራ ለማድረግ ይችላል፤ ፰/ ከአደራ ሂሳብ ጋር የተያያዘ ሥራን በአግባቡ ያለመወጣት ሁኔታ ሲከሰት ጉዳዩ በዲስፕሊን ጉባዔ ታይቶ ውሳኔ እንዲያገኝ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሊመራው ይችላል፤ ፱/ ከአደራ ሂሳብ ከሚገኝ ወለድ ወይም ማናቸውም ገቢ አጠቃቀምን አስመልክቶ መመሪያ ያዘጋጃል፣ በጠቅላላ ጉባዔው ሲጸድቅ በተግባር ያውላል፤ ፲/ በዚህ አዋጅ ሌሎች አንቀጾች ለማኅበሩ የአደራ ሂሳብን አስመልከቶ የተሠጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፤ ፲፩/ ስለአደራ ሂሳብ ምንነት፣ አያያዝና፣ ሪፖርት አደራረግ እንዲሁም መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ተገቢው ግንዛቤ እንዲፈጠር ተከታታይ ሥልጠናዎችን ይሰጣል ወይም እንዲሠጡ ያደርጋል፤ ፲፫ሺ፭፻፳፯ ፲፪/ የደንበኞች ጥቅም መጠበቁን ያረጋግጣል፤ እንዲሁም የደንበኞችን ጥቅም ለማስጠበቅ ጠቀሜታ ያላቸው የጠበቃ መብቶች መከበራቸውን ይከታተላል፤ ፲፫/ የሕግ ትምህርት ጥራት እንዲጠበቅ፤ የሕግ የበላይነት እንዲከበር፤ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፤ የጥብቅና ሙያ እና አጠቃላይ የኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ፲፬/ የጥብቅና አገልግሎትን በተመለከተ የሕግ ጥናት በማድረግ የጥናት ውጤቱን ተግባራዊ ያደርጋል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ ፲፭/ የማኅበሩ አባላት ይህን አዋጅና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች እና መመሪያዎችን በማክበር የጥብቅና አገልግሎትን እየሰጡ መሆኑን ይከታተላል። Association The Association shall have the following powers and responsibilities: 1/ Supervise continuing legal training, cause the implementation of the provisions of this Proclamation on continued legal training; 2/ Accredit those institutions who offer continuing legal training; 3/ Take appropriate measures on those institutions who offer legal training and violate the provisions of this Proclamation and other relevant laws; 4/ Issue and implement a Directive on the payment of tuition related with continuing legal training; 5/ Prepare and present a Directive concerning the administration of trust account to the General Meeting; and implement same when it is approved; 6/ Cause audit investigation, at any time on any trust account, to monitor and ensure whether a trust account is properly managed; 7/ Receive complaints of clients in relation to trust account management, interrogate and investigate any person; 8/ Refer cases of mismanagement of trust account to the Attorney General for action before the Discipline Committee; 9/ Draft a Directive concerning the usage of interest and any income generated from trust account and implement same when it is approved by the General Meeting; 10/ Perform other activities, in relation to trust account, given to the Association in other provisions of this Proclamation; 11/ Offer trainings or cause to be offered continuing legal training, with the view to create awareness, on the meaning of trust account, accounting, reporting and precautionary measures that have to be taken in relation to trust account; 12/ Ensure that the interests of clients are respected and follow up whether advocates’ rights, which have implications on ensuring clients’ rights as well, have been protected and respected; 13/ Contribute to the advancement and development of quality of law education, rule of law, enforcement of human rights and the profession of advocacy service and the Ethiopian legal system as a whole; 14/ Make study with regard to advocacy service, implement the study and submit same to the concerned body and monitor the implementation; 15/ Monitor whether the members of the Association are providing advocacy service in compliance with this Proclamation, other relevant laws and Directives.
ጠቅላላ ጉባዔው በዚህ አዋጅ መሠረት ፍቃድ የተሰጣቸውን ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በሙሉ የሚያካትት ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፩/ የማኅበሩን ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት ይሾማል፣ ይሽራል፤ ፪/ የማኅበሩን ስትራቴጂክ እቅድ፣ ዓመታዊ እቅድና በጀት ያጸድቃል፤ ፫/ የአባላትን መዋጮ መጠን ይወስናል፤ ፲፫ሺ፭፻፳፰ ፬/ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን እና የውጪ ኦዲተሮችን ሪፖርት ይመረምራል፣ ያጸድቃል፤ ፭/ ለአባላቱ ጠቅላላ ጥቅም እና ለፍትሕ ተደራሽነት ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ይወስናል፤ ፮/ የውጭ ኦዲተሮችን ይሾማል፤ ፯/ በሌሎች የማኅበሩ አካላት የሚሰጡ ውሳኔዎች ከሕዝብ ጥቅም እና ከማኅበሩ ዓላማ ጋር የሚጣጣሙ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ፰/ ለማኅበሩ ሌሎች አካላት በግልጽ ባልተሰጡ ጉዳዮች ላይ ይወስናል፤ ፱/ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ይሾማል፤ ፲/ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሥልጣኑን በከፊል ለሌላ አካል በውክልና ሊሰጥ ይችላል፤ ፲፩/ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፣ ያሻሽላል፣ ያጸድቃል። Meeting The General Meeting comprises advocates and law firms licensed pursuant to this Proclamation and shall have the following powers and duties: 1/ Appoint or remove the President and Vice President of the Association; 2/ Approve the Association’s strategic and annual plan as well as budget; 3/ Determine the amount of membership contribution; 4/ Consider and approve the Executive Committee and External Auditors’ reports; 5/ Decide on issues beneficial to the general interest of its members and accessibility of justice; 6/ Appoint External Auditors; 7/ Ensure that decisions given by other subsidiary organs of the Association are in compliance with public interest and the purposes of the Association. 8/ Decide on issues which are not specifically given to other organs of the Association; 9/ Appoint Executive Committee members; 10/ Delegate, when it is necessary, its powers and authorities, partially, to another organ; 11/ Issue the Memorandum of Association of the Association amend and approve same.
፩/ ማኅበሩ የአስፈፃሚነት ሥልጣን ያለው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይኖረዋል። ፪/ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሰባት አባላት ይኖሩታል። ፫/ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላላ ጉባዔው አባላት መካከል ተመርጠው ይሾማሉ። ፲፫ሺ፭፻፳፱ 1/ The Association shall have an Executive Committee which has the power of execution. 2/ The Executive Committee shall have seven members. 3/ Members of the Executive Committee shall be appointed by electing from members of the General Meeting.
፩/ ማኅበሩን ያስተዳድራል፤ ፪/ የማኅበሩን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ይጠራል፤ ፫/ የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔዎችን ይፈጽማል፣ ያስፈጽማል፤ ፬/ በጠቅላላ ጉባዔው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፤ ፭/ የሠራተኞችን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፤ ፮/ የሠራተኞችን ደመወዝና አበል ይወስናል፤ ፯/ ፕሬዚዳንቱ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሥራቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል። Committee The Executive Committee shall have the following powers and Duties: 1/ Administer the Association; 2/ Call the annual General Meeting of the Association; 3/ Execute and cause the execution of the decisions of the General Meeting; 4/ Perform other tasks assigned to it by the General Meeting; 5/ Issues employees administrative manual; 6/ Determine the salaries and allowances of employees; 7/ Control and monitor whether the President and Vice President perform their duties and responsibilities properly.
፩/ ፕሬዚዳንቱ አጠቃላይ የማኅበሩን ሥራ የሚመራ ሆኖ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔው እና ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይሆናል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሬዚዳንቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡- ፲፫ሺ፭፻፴ ሀ) ማኅበሩን ወክሎ ውል ይዋዋላል፣ ይከሳል፣ ይከሰሳል፣ ማኅበሩ በሚከስበት፣ በሚከሰስበት ወይም በሌላ ተመሳሳይ የሕግ ጉዳይ ማኅበሩን ወክሎ የሚቀርብ ጠበቃ ይወክላል፣ የማኅበሩን ጉዳይ ማስፈጸም እንዲችል የማኅበሩን ሠራተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን እንደ አስፈላጊነቱ ይወክላል፤ ለ) የማኅበሩን ዓመታዊ እቅድ፣ በጀት፣ የሥራ ክንውን እና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያቀርባል፤ ሐ) ለሥራ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ረቂቅ ያዘጋጃል፣ በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴው ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ መ) በማኅበሩ የሰው ኃይል አስተዳደር መመሪያ መሠረት የማኅበሩን ሠራተኞች ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፤ ሠ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የማኅበሩን ሥራዎች ያሰራል፤ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ባለው ግንኙነት ማኅበሩን ይወክላል፤ ረ) የጠቅላላ ጉባዔና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን ይከታተላል፤ ሰ) በጠቅላላ ጉባዔውና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡ ፲፫ሺ፭፻፴፩ ፫/ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት፡ሀ) ፕሬዚዳንቱ በማይኖሩበት ጊዜ ወይም ሥራውን ሊሰራ በማይችልበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፤ ለ) በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወይም በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል። Vice President 1/ The President shall manage the general business of the Association and is accountable to the General Meeting and the Executive Committee; 2/ Without prejudice to the provisions of Sub-Article (1) of this Article, the President shall have the following powers and duties: a) on behalf of the Association, concludes contract, sue, defend; appoint an advocate, to represent the Association, who brings an action or defends the Association or defends the interests of the Association in similar matters; appoint the employee of the Association or a third party to represent the Association as may be necessary; b) prepare and submit, to the Executive Committee, the annual activity plan, budget, performance and financial reports; c) prepare draft Directives necessary for the functions of the Association and implement same when approved by the General Meeting; d) hire and administer the employees of the Association based on the Human Resources Manual of the Association; e) perform the activities of the Association and represent the Association in its relation with third parties in accordance with the Directive given to him by the Executive Committee; f) follow up the implementation of the decisions of the General Meeting and the Executive Committee; g) perform other tasks assigned to him by the General Meeting and the Executive Committee. 3/ The Vice President of the Association: a) act on behalf of the President when he is absent or unable to discharge his duties and responsibilities; b) perform other tasks assigned to him by the Executive Committee or the President.
፩/ ዋና ጸሐፊው በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ የሚሾም ሆኖ ተጠሪነቱ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እና ለፕሬዚዳንቱ ይሆናል፤ ፪/ ዋና ጸሐፊው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡ሀ) የማኅበሩን የእለት ተእለት ሥራ ይመራል፣ ያከናውናል፤ ለ) የጠቅላላ ጉባዔውና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ቃለ-ጉባዔዎች በአግባቡ መያዛቸውንና መጠበቃቸውን ያረጋግጣል፤ ሐ) ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመማከር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን የስብሰባ አጀንዳ ያዘጋጃል፤ መ) ሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ በሌላ ሁኔታ እንዲፈጸም የመወሰን ሥልጣኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ጸሐፊው ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በመሆን የማኅበሩን የባንክ ሂሳብ ይከፍታል፤ ያንቀሳቅሳል፤ ፲፫ሺ፭፻፴፪ ሠ) የማኅበሩን የንብረት አስተዳደር እና የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት በአግባቡ መዘርጋቱን እና የሂሳብ ሠነዶች በአግባቡ መያዛቸውን ያረጋግጣል፤ ሰ) የማኅበሩ ንብረትና ሂሳብ ተቀባይነት ባለው የሂሳብ ዘዴ መያዙን ያረጋግጣል፤ ሸ) ሌሎች በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እና በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል። 1/ The Secretary General shall be appointed by the Executive Committee and shall be accountable to the Executive Committee and the President. 2/ The Secretary General shall have the following powers and duties: a) manage and perform the day to day activities of the Association; b) ensure that the minutes of the General Meeting and the Executive Committee are properly maintained and kept; c/ prepare the agenda of meeting of the Executive Committee in consultation with the President; d/ without prejudice to the power of the Executive Committee to decide otherwise, jointly with other employees of the Association, open and transact the bank accounts of the Association; e) ensure that the property administration and the accounting systems of the Association are properly placed and financial documents are kept properly; f) ensure that the properties and accounts of the Association are kept in a system that is acceptable; g) perform other tasks assigned to him by the Executive Committee and the President.
ሰለ ጠቅላላ ጉባዔው እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አመራር አካላት አደረጃጀት፣ ኃላፊነት፤ ስለ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ሠራተኞች የሥራ ድርሻ፣ የምርጫና ስብሰባ ሥነሥርዓት፣ የማኅበሩ ልዩ ልዩ አካላት የሥራ ዘመን እና ሌሎች ለማኅበሩ በሕግ የተሰጡ ሥልጣንና ተግባራት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ማኅበሩ በሚያወጣው ውስጠ-ደንብ ይወሰናሉ። Association’s By-Laws Organization of the management of the General Meeting and the Executive Committee; their responsibility; about the president, vice president and other employees job, election and meeting procedures; durations of the Association’s different organs and other issues related with powers and duties given to the Association shall be decided by the by- laws.
፩/ የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ከዚህ በኋላ “ቦርዱ” እየተባለ የሚጠራው በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። ፲፫ሺ፭፻፴፫ ፪/ ቦርዱ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቅራቢነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሾሙ ከሚከተሉት አካላት የተውጣጡ ሰባት አባላት ይኖሩታል፡ሀ) ከጠበቆች ማኅበር ሶስት፣ ለ) ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት፣ ሐ) ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ፣ መ) በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከሆኑ የሕግ ትምህርት ቤቶች አንድ ተወካይ። ፫/ የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን ሶስት ዓመት ሲሆን አንድ አባል ከሁለት የሥራ ዘመን በላይ መመረጥ አይችልም። ፬/ የቦርዱ ሰብሳቢ እና ጸሐፊ ከቦርዱ አባላት መካከል በአባላቱ ይመረጣል። 1/ The Advocates’ Administration Board, herein after called the “The Board” is hereby established by this Proclamation; 2/ The Board shall have seven members comprised of the following bodies which nominated by the Attorney General and appionted by the Prime Minister: a) Three members from the Advocates’ Association; b) Two members from the Attorney General; c) One member from the Federal Supreme Court; and d) One member from the School of Law among government Universities in Addis Abeba. 3/ The term of a Board member shall be three years and no member shall be elected for more than two terms; 4/ The Chairperson and Secretary of the Board shall be elected by the members from among members of the Board.
፩/ በማኅበሩ የሚወሰዱ እርምጃዎችና ውሳኔዎች፤ እንዲሁም በማኅበሩ በሚወጡ መመሪያዎች እና ሌሎች ተመሳሳይ ሠነዶች ሕጋዊነት ላይ ቁጥጥር የማድረግ፤ ፪/ በማኅበሩ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ተቀበሎ መመርመር እና ውሳኔ መስጠት፤ ፲፫ሺ፭፻፴፬ ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፸፮ ንዑስ አንቀጽ (፬) መሠረት የዲስፕሊን ጉባዔው፤ አንቀጽ ፸፰ መሠረት የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴው፤ እንዲሁም በአንቀጽ ፹ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ በሚሰጡት ውሳኔ ላይ የሚቀርብ ቅሬታን ተቀብሎ መመርመር፤ ውሳኔ መስጠት፤ ፬/ ቅሬታውን በሚመረምርበት ወቅት ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት ይረዳል ብሎ ካመነ አዲስ ማስረጃ አስቀርቦ የማየት፤ ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) የተጠቀሱት ኮሚቴዎች ወይም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይም ጉባዔው በአግባቡ ያላጣራው ወይም ያላጤነው ፍሬ-ነገር ወይም ማስረጃ ካለ ጉዳዩን ውሳኔ ለሰጠው አካል በድጋሚ እንዲታይ ለአንድ ጊዜ መልሶ የመምራት፤ ፮/ ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች ሊይዙት የሚገባውን የሙያ ኃላፊነት መድን መጠን፤ እና የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ መጠንና የአከፋፈል ሥርዓትን በመመሪያ የመወሰን። The Board shall have the following powers and duties: 1/ Ensure and monitor the legality of measures taken, and decisions passed, by the Association as well as the legality of Directives and other similar documents issued by the Association; 2/ Investigate and decide up on grievances raised on the decisions of the Association; 3/ Investigate and decide upon grievances raised on the decisions of the Discipline Committee as provided under Article 76 Sub-Article (4), Advocacy Profession Entrance Qualification Exam Committee as provided under Article 78 and the Advocacy License evaluation Committee as provided under Article 80 Sub-Article (1) of this Proclamation; 4/ Cause the production of new evidence, while investigating the grievance, if it is convinced that the production of such evidence would assist justice to prevail; 5/ Remand, for one time, issues, facts or evidence which were not duly considered, to the Committees or the Attorney General mentioned under Sub- Article (3) of this Article for further consideration. 6/ Decide, through Directives, on the professional indemnity insurance that shall be secured by advocates and law firms; the amount of fee for advocacy service and its computation.
፩/ ቦርዱ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት ውስጥ ጽሕፈት ቤት ይኖረዋል። ፪/ የቦርዱ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይመደባሉ፤ ጽሕፈት ቤቱ የሚሰራው ሥራ ዝርዝር ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። ፫/ የቦርዱ አባላት የቦርዱን ሥራ በሚፈጸሙበት ጊዜ ሊከፈላቸው የሚገባ ክፍያ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይሸፈናል። ፲፫ሺ፭፻፴፭ ፬/ ስለቦርዱ በጀት አስተዳደርና ስለቦርድ አባላት ክፍያ ዝርዝሩ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል። 1/ The Board shall have an office within the office of the Attorney General. 2/ The employees of the Board shall be assigned by the Attorney General. The duties and responsibilities of the office shall be determined by a Directive to be issued by the Board. 3/ The allowance that should be paid to the Board members, while in the performance of their duty, shall be covered by the Attorney General. 4/ The particulars of the administration of the budget of the Board and allowance to be paid to its members shall be determined by a Directive to be issued by the Attorney General.
፩/ ቦርዱ በዓመት ቢያንስ አራት ጊዜ ይሰበሰባል። ፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ሰብሳቢው በማንኛውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ፫/ ቦርዱ የአባላቱን መደበኛ ሥራ በማይጎዳና የቦርዱ ሥራ በማይስተጓጎል መልኩ የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል። ፬/ ከቦርዱ አባላት ቢያንስ አምስቱ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል። ፭/ የቦርዱ ውሳኔ የሚሰጠው በስምምነት ይሆናል፤ ሆኖም ስምምነት ባልተገኘ ጊዜ በስብሰባው በተገኙ አባላት አብላጫ ድምጽ ሲደገፍ ይሆናል፤ ድምጽ እኩል ለእኩል በተከፈለ ጊዜ የቦርዱ ሰብሳቢ የደገፈው ወገን አብላጫ ይሆናል። ፮/ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የውስጥ አሠራር ሥርዓት በተመለከተ የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች ሳይቃረን በመመሪያ ሊወስን ይችላል። ፲፫ሺ፭፻፴፮ 1/ The Board shall meet at least four times within a year; 2/ Without prejudice to the provision of Sub-Article (1) of this Article, the chairperson at any time may call an extraordinary meeting; 3/ The Board shall put a system whereby the regular personal responsibilities of its members and their activities as Board members shall not be affected; 4/ There shall be a quorum to conduct a meeting when at least five members attend a meeting; 5/ The Board shall pass decisions by agreement; when there is no agreement reached it pass decisions by a majority vote of members present; In case of tie, the chairperson shall have a casting vote; 6/ Without prejudice to the provisions of this Article, the Board, without contradicting the provisions of this Proclamation, may issue a Directive that determines its Internal Procedure to conduct business.
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፸ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና (፫) መሠረት በቦርዱ በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን ይግባኙን ውሳኔውን ባወቀ በ፴ ቀናት ውስጥ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። Board A party who has grievance on the decision given by the Board pursuant to Sub-Articles (2) and (3) of Article 70 of this Proclamation may appeal, within 30 days of knowing the decision, to the Federal High Court.
በዚህ አዋጅ የተቋቋሙት የጠበቆች ዲስፕሊን ጉባዔ፣ የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴ እና የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ ተጠሪነት ለቦርዱ ይሆናል። The Advocates’ Discipline Committee; the Advocacy Profession Entrance Qualification Exam Committee; and Advocacy License Evaluation Committee which are established under this Proclamation, shall be accountable to the Board.
፩/ የጠበቆች ዲስፕሊን ጉባዔ ከዚህ በኋላ “ዲስፕሊን ጉባዔው” እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። ፪/ ዲስፕሊን ጉባዔው ከሚከተሉት አካላት የተውጣጡ በየተቋማቱ ተመርጠው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የሚሾሙ ሰባት አባላት ይኖሩታል፡ሀ) ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት ተወካይ፣ ለ) ከጠበቆች ማኅበር አራት ተወካይ፣ እና ሐ) ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ተወካይ። ፲፫ሺ፭፻፴፯ ፫/ የአንድ አባል የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ሲሆን ከሁለት ጊዜ በላይ ሊመረጥ አይችልም። ‹፬/ የዲስፕሊን ጉባዔው ሰብሳቢ ከአባላቱ ውስጥ በጉባዔው አባላት ይመረጣል። ፭/ ዲስፕሊን ጉባዔው፡ሀ) እንደ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ መሰብሰብ ይችላል፣ ለ) ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል፣ ሐ) ውሳኔዎችን በድምጽ ብልጫ ያሳልፋል፤ ሆኖም ድምጽ እኩል ሲሆን በሰብሳቢው በኩል ያለው ድምጽ የጉባዔው ውሳኔ ሆኖ ይጸድቃል። ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፭) ከፊደል-ተራ (ሀ)-(ሐ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ጉባዔው የራሱን የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል። Committee and its Structure 1/ The Advocates’ Discipline Committee, herein after called the “Discipline Committee,” is hereby established by this Proclamation; 2/ The Committee shall have seven members comprised of the following bodies which nominated by the institutions and appionted by the Attorney General: a) two members from the Attorney General; b) four members from Advocates’ Association; and c) one member from the Federal Supreme Court. 3/ The term of a member shall be two years and no member shall be elected for more than two terms; 4/ The Chairperson of the Committee shall be elected by the members from among the Committee members; 5/ The Committee shall perform its tasks as follows: a) may meet at any time as may be necessary; b) there shall be a quorum to conduct a meeting when more than half of its members are present; c) decisions shall be passed by a majority vote. In case of tie, however, the Chairperson shall have a casting vote. 6/ Without prejudice to the provisions of Sub-Article (5) paragraph (a)-(c) of this Article, the Committee may issue its own procedure of meeting.
፩/ የጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች የሥራ አፈጻጸም ከሙያ ሥነ-ምግባር ደንብ ጋር የተጣጠመ መሆኑን መከታተል የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፤ ፲፫ሺ፭፻፴፰ ፪/ ይህንን አዋጅ ወይም የጠበቆች የሥነ-ምግባር ደንብ ወይም መመሪያ በመተላለፍ በጠበቃ እና ጥብቅና ድርጅት ላይ የሚቀርብ ክስን ይመረምራል፤ ክሱ ጠበቃውን ወይም የጥብቅና ድርጅቱን የሚያስቀርብ መሆን አለመሆኑን ይወስናል፤ ፫/ ክሱ እና ማስረጃው ጠበቃውን የሚያስቀርብ መሆኑን ከወሰነ ጠበቃው መልሱን በ፴ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ እንዲያቀርብ በመጥሪያ ላይ በመግለጽ ክሱን ለጠበቃው ይልካል፤ ፬/ በጠበቃው ወይም በጥብቅና ድርጅት ላይ የቀረበውን ክስ እና ማስረጃ፤ እንዲሁም በጠበቃው በኩል የተሰጠ መልስ እና ማስረጃ ከመረመረ እና ካከራከረ በኋላ ውሳኔ ይሰጣል፤ ፭/ የጠበቆች ሥነ-ምግባር ብቃት የሚጎለብትበትን፤ የጥብቅና ሙያ ክብር የሚጠበቅበትን ሁኔታ እያጠና ለቦርዱ ሀሳብ ያቀርባል። Discipline Committee The Committee shall:- 1/ Set a system whereby it can monitor and ensure the Advocates’ and law firms’ performance is in compliance with Professional Code of Conduct; 2/ Investigate complaints, for violation of this Proclamation and the code of conduct of advocates, lodged against advocates and law firms and decide whether the advocate or the law firm should be called to defend himself/itself or not; 3/ If the Committee decides the advocate or the firm should defend the disciplinary action and evidence brought against him/it, it shall send summons to the advocate or the law firm so that he/it can submit his/its statement of defense, in writing, within 30 days; 4/ The Committee shall give its verdict after examination of the disciplinary charge, the evidence, and the defense of the advocate or the firm; 5/ Study and present proposals to the Board on the way the competence and standard of conduct of advocates can improve and develop as well as the dignity of the advocacy profession is respected.
፩/ የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴ ከዚህ በኋላ “የፈተና ኮሚቴ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። ፲፫ሺ፭፻፴፱ ፪/ የፈተና ኮሚቴው ከሚከተሉት አካላት የተውጣጡ በየተቋማቱ የሚመረጡና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የሚሾሙ ሰባት አባላት ይኖሩታል፡ሀ) ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት ተወካዮች፣ ለ) ከጠበቆች ማኅበር ሦስት ተወካይ፣ ሐ) ከፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንድ ተወካይ፣ መ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሕግ ትምህርት ቤት አንድ ተወካይ። ፫/ የአንድ የፈተና ኮሚቴ አባል የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ሲሆን ከሁለት ጊዜ በላይ በፈተና ኮሚቴ አባልነት ሊመረጥ አይችልም። ፬/ የፈተና ኮሚቴው ሰብሳቢ በጠበቆች ማኅበር የሚመረጥ ይሆናል። ፭/ የፈተና ኮሚቴውን ስብሰባ በተመለከተ፡ሀ) ኮሚቴው እንደ አስፈላጊነቱ በማንኛውም ጊዜ ሊሰበስብ ይችላል፣ ለ) ከኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ-ጉባዔ ይሆናል፣ እና ሐ) የኮሚቴው ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ፤ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል ከተከፈለ የሰብሳቢው ድምጽ ወሳኝነት ይኖረዋል። ፲፫ሺ፭፻፵ Advocacy Profession Entrance Qualification Exam Committee 1/ The Advocacy Profession Qualification Exam Committee, herein after called the “Exam Committee” is hereby established by this Proclamation; 2/ The Exam Committee shall have seven members comprised of the following bodies which nominated by the institutions and appionted by the Attorney General: a) two representatives from the office of the Attorney General; b) three members from Advocates’ Association; c) one member from the Federal High Court; and d) one member from Addis Ababa University School of Law. 3/ The term of a member of the Exam Committee shall be two years and no member shall be elected for more than two terms; 4/ The Chairperson of the Exam Committee shall be nominated by Advocate’s Association; 5/ The meeting of the Exam Committee shall be conducted as follows: a) The Committee shall hold its meeting at any time as may be necessary; b) There shall be quorum to conduct a meeting where more than half of its members are present; and c) Decisions shall be passed by a majority vote. In case of tie, however, the Chairperson shall have a casting vote.
ከሚሰጠው የሥራ ክፍል ጋር በመመካከር ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ የጥብቅና ችሎታ መመዘኛ ፈተና እያዘጋጀ በተወሰነ ጊዜ እና ቦታ ለአመልካቾች ይሰጣል፤ ፪/ የፈተናውን ሥነ-ሥርዓትና ጊዜ ይወስናል ፫/ የፈተና ወረቀቶችን ያርማል፤ ለማለፊያ የሚያበቃ ነጥብ ይወስናል፤ ውጤቱን በይፋ ያስታውቃል፤ ፬/ ፈተናውን በስኬት ላጠናቀቀ ተፈታኝ ፈተናውን ማለፉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይሰጣል፤ ፭/ የፈተና ሥነ-ሥርዓት ደንብ አዘጋጅቶ ለቦርዱ አቅርቦ ሲጸድቅ በሥራ ላይ ያውላል። Committee The Exam Committee shall have the following powers and duties: 1/ In consultation with the Advocacy License Department of the Attorney General, prepare advocacy competence qualification exams and examine applicants, at least twice a year, at a place and time agreed; 2/ Determine the procedure and time to administer the Exam; 3/ Evaluate answers to exams, grade and determine the pass mark, and publicize the result; 4/ Give certificate for the applicant who successfully pass the exam; 5/ Prepare exam procedure Regulation and implement when accepted by the Board.
፩/ ለአመልካቾች የጥብቅና ፍቃድ ሊሰጥ የሚገባው ስለመሆን አለመሆኑ የሚወሰን “የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ” በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። ፪/ ኮሚቴው ከሚከተሉት አካላት የተውጣጡ በየተቋማቱ የሚመረጡና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የሚሾሙ አምስት አባላት ይኖሩታል፡ሀ) ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት ተወካዮች፣ ፲፫ሺ፭፻፵፩ ለ) ከጠበቆች ማኅበር ሁለት ተወካዮች፣ እና ሐ) ከፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንድ ተወካይ። ፫/ የአንድ አባል የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ሲሆን ከሁለት ጊዜ በላይ በአባልነት ሊመረጥ አይችልም። ፬/ የኮሚቴው ሰብሳቢ ከአባላቱ መካከል በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የሚሰየም ይሆናል። Advocacy License Evaluation Committee 1/ “Advocacy License Evaluation Committee”, which decides whether advocacy license should be granted or not is hereby established by this Proclamation; 2/ The Committee shall have five members comprised of the following bodies which nominated by the institutions and appionted by the Attorney General: a) two representatives from the office of the Attorney General; b) two representatives from Advocate’s Association; and c) one representative from the Federal First Instance Court. 3/ The term of a member of this Committee shall be two years and no member shall be elected for more than two terms; 4/ The Chairperson of the Committee shall be nominated by the Attorney General from among the members of the Committee.
፩/ የአመልካቹን ማስረጃዎች መርምሮ አመልካቹ ፍቃድ እንዲሰጠው ወይም አንዳይሰጠው ይወስናል፤ ፪/ አመልካቹ ለፍትሕ ሥራ አካሄድ የሚስማማ የሥነ-ምግባር ብቃት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ማንኛውንም ሰው መጠየቅ ወይም ማስረጃ አስቀርቦ መመርመር ይችላል። Evaluation Committee The Committee፡- 1/ After examination of the applicant’s evidence decide, whether the applicant should be issued with the license or the application be rejected; 2/ Cause the appearance of any person and hear or cause the production of any evidence to verify that the applicant has a good conduct and meets the requirements of the justice process.
፩/ ኮሚቴው እንደ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል፤ ፪/ ከኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ-ጉባዔ ይሆናል፤ ፫/ የኮሚቴው ውሳኔዎች በስብሰባው በተገኙ አባላት በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ፤ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል፤ ፲፫ሺ፭፻፵፪ ፬/ በዚህ አንቀጽ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚቴው የራሱን የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል። Evaluation Committee 1/ The Committee shall hold its meeting at any time as may be necessary; 2/ There shall be quorum to conduct a meeting where more than half of its members are present; 3/ Decisions shall be passed by a majority vote. In case of tie, however, the Chairperson shall have a casting vote. 4/ Without prejudice to the provisions of this Article, the Committee may issue its own meeting procedure.
፩/ የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ የጥብቅና ፍቃድ እንዲሰጠው ለወሰነለት ባለሙያ የጥብቅና ፍቃድ ይሰጣል፤ ፪/ የጥብቅና ፍቃድ፤ የጥብቅና ድርጅቶችን እና ከጠበቃ እና ጥብቅና ድርጅቶች ጋር የሚሰሩ ሰዎችን ይመዘግባል፣ የጥብቅና ፍቃድ ያድሳል፣ ፫/ የጠበቆች ዲስፕሊን ጉባዔ በሚወስነው መሠረት የጥብቅና ፍቃድ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ፬/ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ በሚወሰነው መሠረት ለሚሰጠው የጥብቅና ፍቃድና ሌሎች አገልግሎቶች ክፍያ ይሰበስባል፤ ፭/ በጠበቆችና በጥብቅና ድርጅቶች ለሚሰጡ የሕግ አገልግሎቶች ከቦርዱ እና ከማኅበሩ ጋር በመመካከር መለኪያዎችን ያወጣል፤ ፮/ በፌደራል እና በክልል ያሉ የጥብቅና ሙያ አስተዳደደር ሥርዓቶች የተጣጣሙ እንዲሆኑ ጥረት ያደርጋል፤ ፲፫ሺ፭፻፵፫ ፯/ የሥነ-ምግባር ጥሰት ፈጽሟል ተብሎ ጥቆማ በቀረበበት ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ላይ የሥነ-ምግባር ጥሰቱ ስለመፈጸሙ ለማረጋገጥ ምርመራ ያካሂዳል፣ የዲስፕሊን ክስ ይመሰርታል፤ ፰/ ሌሎች በዚህ አዋጅ፤ ይህን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣ ደንብ እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች የተሰጡትን ሥልጣን እና ተግባራት ይፈጽማል፤ ፱/ በዚህ አዋጅ እና ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጡ ደንብና መመሪያዎች የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት በሙሉ ወይም በከፊል ለጠበቆች ማኅበር በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል፤ ፲/ የጥብቅና ማኅበሩ እንዲጠናከር ለማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶች እና ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፤ ማኅበሩ ከሌሎች ተቋማት ጋር ሕጋዊ ግንኙነት ስለሚፈጥርበት ሁኔታ ያመቻቻል፤ ፲፩/ አዋጁን ለማስፈጸም በማኅበሩ እና በቦርዱ የሚወጡ መመሪያዎችን በማዘጋጀት እና እንዲጸድቁ በማድረግ፤ እንዲሁም አጠቃላይ የጥብቅና አገልግሎትን በተመለከተ በማኅበሩ፤ በቦርዱ ወይም ሌሎች በሚመለከታቸው አካላት የሚነሱ አዲስ ሕግ እንዲወጣ ወይም የሕግ ማሻሻያ እንዲደረግ በሚያስፈልጉ ሀሳቦች ላይ እንደ አግባብነቱ የሕግ ረቂቅ በማዘጋጀት እና በሚመለከተው አካል እንዲጸድቅ በማድረግ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤ ፲፪/ ማኅበሩ በሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲደራጅ፤ ለመነሻ የሚሆን በጀት እንዲኖረው እና እንደተቋም ለመንቀሳቀስ እንዲችል አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤ ፲፫ሺ፭፻፵፬ General The Attorney General shall have the following powers and duties: 1/ Issue advocacy license to the person allowed to have advocacy license, by Advocacy License Evaluation Committee; 2/ Register advocacy license, law firms, support staff who work with advocates and law firms; and renew advocacy license; 3/ Suspend or revoke advocacy license based on the decisions of the Advocates’ Discipline Committee; 4/ Collect advocacy license fee or other payments determined by a Regulation to be issued pursuant to this Proclamation; 5/ In consultation with the Board and Association, set standards for the services offered by advocates and law firms; 6/ Endeavour to harmonize the system of the administration of advocacy service profession at the Federal and Regional States’ level; 7/ Investigate complaints for violations of disciplinary rules brought against any advocate or law firm and bring disciplinary action; 8/ Exercise powers and duties entrusted to it by this Proclamation, a Regulation to be issued pursuant to this Proclamation and other relevant law; 9/ Delegate the powers and duties entrusted to it by this Proclamation, a Regulation and a Directive to be issued for the implementation of this Proclamation, fully or partially, to the Advocates’ Association; 10/ Cause establishment of different structures and committees to strengthen the Association; create favorable conditions in which the Association establish legal relationship with other organs; 11/ Provide necessary support on drafting and ratification of Directives needed for the implementation of this proclamation; as well as on drafting and cause ratification of the necessary new laws or laws to be amended, on the advocacy service as a general, that are initiated by the Association, Board or other concerning organs. 12/ Provide necessary support to the Association to organize human resource; have starting budget and perform as an organization.
የሚከተሉትና መሰል በጠበቆች ሥነ-ምግባር ደንብ የተደነገጉ በጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የሚፈጸሙ ጥፋቶች ቀላል የዲስፕሊን ጥፋቶች ናቸው፡፩/ የጥብቅና ፍቃድን ለደንበኛ፤ ለፍርድ ቤት ወይም ለሚመለከተው አካል እንዲያሳይ በተጠየቀ ጊዜ ለማየሳት ፈቃደኛ ያለመሆን፤ ፪/ ጉዳዩ ያለበትን ሁኔታና የደረሰበትን ደረጃ በደንበኛው ሲጠየቅ በአግባቡ ያለማሳወቅ፣ ደንበኛን ማመናጨቅ ወይም ክብሩን መንካት፤ ፫/ ያለበቂና አሳማኝ ምክንያት በቀጠሮ ቀን መዘግየት እና ፍርድ ቤት ያለመገኘት፤ ፬/ ለጠበቆች ማኅበር መክፈል የሚጠበቅበትን ክፍያ ወይም መዋጮ በተደጋጋሚ እና በወቅቱ ያለመክፈል፤ ፭/ የጥብቅና ፍቃድን በወቅቱ አለማሳደስ፤ ፮/ ባልታደሰ የጥብቅና ፍቃድ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት፤ ፯/ የጥብቅና ፍቃዱን ለጥብቅና ፍቃድ ሰጪው ተቋም ሳይመልስ በሌላ ቋሚ ሥራ ተሰማርቶ መገኘት። ፲፫ሺ፭፻፵፭ The following and similar misconducts provided by the Advocates’ Code of Conduct, when committed by an advocate or a law firm, shall be considered as violation of non serious disciplinary rules: 1/ Refusal to show his/its advocacy license when requested by a client, a court or a concerned body; 2/ Failure to inform his/its client, about the condition and level of the case, when requested; or mistreat his/its client or degrade his dignity; 3/ Without good cause, delay and failure to appear before the court on the date of appointment; 4/ Failure to pay, repeatedly and on time, expected payment or membership contribution for the Advocates’ Association; 5/ Failure to renew the advocacy license on time; 6/ Rendering advocacy service without renewing the advocacy license. 7/ Being employed in a permanent work without returning the advocacy license to the license issuing body.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) ከተደነገጉት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የቃል ማስጠንቀቂያ በዲስፕሊን ጉባዔው ይሰጠዋል፤ ለሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ጥፋት ከፈጸመ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። ፪/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፫ ንዑስ አንቀጽ (፫) እና (፬) የተደነጉትን ጥፋቶች የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፫ ንዑስ አንቀጽ (፭) እና (፯) የተደነገጉትን ጥፋቶች የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት እንደነገሩ ሁኔታ ከብር አምስት ሺህ እስከ ብር ሰባት ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። Disciplinary Violations 1/ The Committee shall give oral warning to an advocate or a law firm who or which violates one of the disciplinary misconducts provided on Sub-Articles (1) and (2) of Article 83; An advocate or a law firm, who or which had been given oral warning twice, shall be served with a written warning when he or it violates the rules for the third time; 2/ An advocate or a law firm who or which violates disciplinary rules provided under Article 83 Sub-Articles (3) and (4) shall be served with a written warning; 3/ An advocate who or a law firm which violates Article 83 Sub-Articles (5) and (7) of this Proclamation shall, as the case may be, fined from Birr Five Thousand to Birr Seven Thousand.
የሚከተሉት እና መሰል በጠበቆች ሥነ-ምግባር ደንብ የሚጠቀሱ በጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የሚፈጸሙ ጥፋቶች ከባድ የዲስፕሊን ጥፋቶች ናቸው፡- ፲፫ሺ፭፻፵፮ ፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፰ ንዑስ አንቀጽ (፫) ሥር የተዘረዘሩ ሰዎችን በጠበቃ ረዳትነት ወይም በሕግ ጉዳይ ጸሐፊነት መቅጠር እና ማሰራት፤ ፪/ በሥሩ የቀጠራቸውን የጠበቃ ረዳትና ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች ለፍቃድ ሰጭው አካል ያለማሳወቅና ያለማስመዝገብ፤ ፫/ ያለበቂና አሳማኝ ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ በተደጋጋሚ መጠየቅና የፍርድ ቤት ጉዳይ እንዲጓተት ማድረግ፤ ፬/ የጥብቅና አገልግሎት መስጫ ቢሮ ሳይኖር የጥብቅና አገልግሎት መስጠት፤ ፭/ በሕግ ከተፈቀደው ምክንያት ውጭ ተከታታይ የግዴታ የሕግ ሥልጠና በአግባቡ አለመውሰድ፤ ፮/ የደንበኛን ምስጢር አለመጠበቅ፤ ፯/ ነጻ የጥብቅና አገልግሎት እንዲሰጥ በሚመለከተው አካል ሲመራለት ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆን፤ ፰/ የጥብቅና ሥራን በአገናኝ አማካኝነት መስራት ወይም ለሌሎች ጠበቆች የአገናኝነት ሥራ መስራት፤ ፱/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ ከተደነገገው በስተቀር ከደንበኛ ጋር የሚደረግ የጥብቅና አገልግሎት ውል ስምምነትን በጽሑፍ ያለማድረግ፤ ፲/ ያለበቂ ምክንያት የጥብቅና ውልን ማቋረጥ ወይም በጥብቅና ውሉ ከተገለጸው የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ በተጨማሪ ከደንበኛው ፍላጎት ውጪ ያለበቂ ምክንያት ተጨማሪ ክፍያ መቀበል፤ ፲፫ሺ፭፻፵፯ ፲፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፫ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የመድን ዋስትና ሳይገባ ወይም የመድን ዋስትናው በወቅቱ ሳይታደስ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት፤ ፲፪/ በፍርድ ቤት ወይም ሌሎች ውሳኔ በሚሰጡ አካላት ዘንድ የሚታዩ ጉዳዮችን በተመለከተ አግባብ ባልሆነ መንገድ ውሳኔ ለማግኘት መጣር፤ ፲፫/ የጥቅም ግጭት የሚያስነሳ ወይም የጥቅም ግጭት ያለበት ጉዳይ መሆኑን እያወቀ ጉዳዩን መያዝ፤ ፲፬/ ከተሰጠው የጥብቅና ፍቃድ ደረጃ በላይ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት፤ ፲፭/ የደንበኛውን ማስረጃ በአግባቡ ለፍርድ ቤት አለማቅረብና ከአቅም በታች በመከራከር መዝገቡ ውጤታማ እንዳይሆን ማድረግ፤ ፲፮/ የጥብቅና ፍቃድን በማንኛውም ሁኔታ ለሶስተኛ ወገን መጠቀሚያ አሳልፎ መስጠት፤ ፲፯/ ነጻ የጥብቅና አገልግሎት የመስጠት ግዴታውን እያወቀ ወይም በቸልተኝነት በአግባቡ ባለመወጣት የደንበኛን ጉዳይ እንዲበላሽ ወይም ውጤታማ እንዳይሆን ማድረግ፤ ፲፰/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፭ እና ፴፮ ንዑስ አንቀጽ (፩)፣ (፬) እና (፭) የተደነገጉትን ግዴታዎች በመተላለፍ ከደንበኛ የአደራ ሂሳብ አያያዝ ጋር የተያያዙ ጥፋቶችን መፈጸም፤ ፲፱/ ከተቃራኒ ባለጉዳይ ጠበቃ ጋር በመመሳጠር ወይም ማስረጃ በማጥፋት የደንበኛ ጉዳይ ውጤታማ እንዳይሆን ማድረግ፤ ፲፫ሺ፭፻፵፰ ፳/ የሕግ መሠረት የሌለውንና እንደማያዋጣ በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ያዋጣል በማለት መያዝና ከደንበኛ ክፍያ መቀበል፤ ፳፩/ ሀሰተኛ ማስረጃ በመጠቀም ወይም በማንኛውም ሁኔታ በማታለል የጥብቅና ፍቃድ ማውጣት፤ ፳፪/ ከጥብቅና ሙያ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በእምነት ማጉደል፣ ማታለል፣ ማጭበርበር፣ ሀሰተኛ ሠነድ ማዘጋጀት ወይም መገልገል፣ ሥርቆት፣ እና በመሳሰሉት ከሥነ-ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ መቀጣት፤ ፳፫/ ከጥብቅና ሙያ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ ወይም እንዲቀርብ ማድረግ፣ ሀሰተኛ ምስክር በማዘጋጀት በሀሰት ማስመስከር፣ ተከሳሽ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ወይም እንዲጠፋ ማድረግ ወይም መምከር፣ ለተቃራኒ ወገን ጠቃሚ የሆነን ማስረጃ እንዳይጠቀምበት በማሰብ ማጥፋትና ፍትሕ እንዲዛባ ማድረግ እና በመሳሰሉት ከሥነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ መቀጣት፤ ፳፬/ በታገደ ወይም በተሰረዘ የጥብቅና ፍቃድ መታገዱን ወይም መሰረዙን እያወቀ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት። ፲፫ሺ፭፻፵፱ Violations The following and similar misconducts provided by the Advocates’ Code of Conduct, when committed by an advocate or a law firm, shall be considered as violation of serious disciplinary rules: 1/ Employ and engage as a law clerk or advocate’s assistant, persons mentioned under Article 18 Sub-Article (3) of this Proclamation; 2/ Failure to declare and get registered advocate’s assistant and support staff, employed under him/it, with the licensing body; 3/ Prolonging the disposal time of court cases by repeatedly applying, without good cause, for change of adjournments; 4/ Rendering advocacy service without having an office; 5/ Failure to take properly, for reasons other than those allowed by law, the mandatory continuing professional legal training; 6/ Failure to keep the confidentiality of client’s information; 7/ Refusal to provide pro bono advocacy service when a case is assigned to him/it by the concerned body; 8/ Doing advocacy service with the medium of a intermediary or serving as a intermediary to other advocates; 9/ Failure to make the contract of advocacy service with a client in writing, except provided by Article 23 Sub-Article (1) of this Proclamation; 10/ Terminating the contract of advocacy service without good cause or demanding ,against the will of the client, additional service fee other than what is agreed upon on the contract of advocacy service; 11/ Providing advocacy service without securing insurance policy or renewing same within the period provided under Article 33 of this Proclamation; 12/ Try to obtain decisions inappropraitly from the courts or other decision making organs who entertain cases; 13/ Handling, with the knowledge, a case which may potentially cause, or has, conflict of interest; 14/ Providing advocacy service for the class which he/it is not licensed for; 15/ Failure to, properly, produce to the court the evidences of his client or performing under capacity with the view to make his client’s case ineffective; 16/ Transfer his/its license to the use of third parties so that third parties can make use of it in any way; 17/ Deliberately make his/its pro bono client lose his case or distort or render the case ineffective due to negligence; 18/ Committing misconducts in relation to handling of his/its clients trust account in violation of obligations specified under Articles 35 and 36 Sub-Articles (1), (4) and (5) of this Proclamation; 19/ Rendering his client’s case ineffective due to unacceptable and inappropriate relationship with the opponent’s advocate or concealing evidence; 20/ Handling cases which have clearly no cause of action and receiving fee for such inappropriate service; 21/ Obtaining advocacy license fraudulently or using a forged evidence; 22/ In relation to advocacy service, being found guilty and punished by the court for breach of trust, fraud, misrepresentation, forgery, or making use of such documents or for the act of theft and similar misconduct; 23/ In relation to advocacy service, produce forged evidence or cause to be produced; prepare false witnesses and get them falsely testify; advise the accused or defendant not to appear before the court or cause his disappearance or advising him to do so; conceal or destroy an evidence with a view to denying the opposing party the opportunity to make use of it and distortion of justice; and found guity and convicted with offences related to similar displinary violation; 24/ Rendering advocacy service, knowingly, with a license which is not renewed, suspended or revoked.
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፫ ከንዑስ አንቀጽ (፫) - (፭) ባሉ ቀላል የዲስፕሊን ጥፋቶች በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ፤ ወይም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፭ ከንዑስ አንቀጽ (፩) – (፯) ከተዘረዘሩት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ከብር ሰባት ሺህ አምስት መቶ እስከ ብር አስራ አምስት ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። ፪/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፭ ከንዑስ አንቀጽ (፰)- (፲፫) ከተዘረዘሩት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ከብር ሃያ ሺህ እስከ ብር ሠላሳ ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፭ ከንዑስ አንቀጽ (፲፬) - (፳) ከተዘረዘሩት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት እንደነገሩ ሁኔታ እስከ ስድስት ወር ለሚደርስ ጊዜ የጥብቅና ፍቃዱ ወይም የምዝገባ ምስክር ሰርተፊኬቱ ይታገዳል። ፬/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፭ ከንዑስ አንቀጽ (፳፩) - (፳፬) ከተጠቀሱት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጥብቅና ፍቃዱ ወይም የምዝገባ ሰርተፊኬቱ ይሰረዛል። ፲፫ሺ፭፻፶ ፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) ላይ የተጠቀሱትን ጥፋቶች ፈጽሞ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሁለት ጊዜ የተቀጣ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ሌላ ተመሳሳይ ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት የፈጸመ እንደሆነ የጥብቅና ፍቃዱ ወይም የምዝገባ ሰርተፍኬቱ ከ፮ ወር እስከ ፩ ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ሊታገድ ይችላል። ፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ሥር የተጠቀሰውን ቅጣት በሰባት ዓመት ውስጥ ለሁለት ጊዜ የተቀጣ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ሌላ ተመሳሳይ ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት ፈጽሞ ከተገኘ የጥብቅና ፍቃዱ ወይም የምዝገባ ሰርተፍኬቱ የሚሰረዝ ይሆናል። ፯/ በዲስፕሊን ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትና መቀጣት በወንጀል የሚያስጠይቁ የዲስፕሊን ጥፋቶችን በተመለከተ የወንጀል ተጠያቂነትን አያስቀርም። Violations 1/ An advocate who or a law firm which is proved to have violated Sub-Articles (3)-(5) of Article 83 of this Proclamation more than two times a year; or an advocate or a law firm who or which violated one of the disciplinary rules provided under Sub-Articles (1)- (7) of Article 85 of this Proclamation, shall be fined from Birr Seven Thousand Five Hundred to Fifteen Thousand; 2/ An advocate or a law firm who or which violated one of the disciplinary rules provided under Sub-Articles (8)-(13) of Article 85, shall be fined from Birr Twenty Thousand to Thirty Thousand; 3/ The license of an advocate or certificate of registration of a law firm who or which violated one of the disciplinary rules provided under Sub-Articles (14)- (20) of Article 85 of this Proclamation, shall be, as the case may be, suspended up to Six months; 4/ The license of an advocate or certificate of registration of a law firm who or which violated Sub-Articles (21) – (24) of Article 85 of this Proclamation shall be revoked; 5/ The license of an advocate or certificate of registration of a law firm who has been punished twice in five years as provided under Sub-Articles (1) and (2) of this Article shall be suspended for a period of six months to one year if he or it is found violating another similar serious disciplinary rule. 6/ The license of an advocate or certificate of registration of a law firm, who or which has been disciplined twice within Seven years for disciplinary measures provided under Sub-Article (3) of this Article, shall be revoked if he or it is found violating another similar serious disciplinary rule; 7/ Being punished for violation of disciplinary rules shall not be a ground for exemption from criminal liability.
፩/ የዲስፕሊን ክስ አቀራረብ እና የክርክር ሥነሥርዓት ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል። ፪/ በቀላል የዲስፕሊን ጥፋት ላይ የሚቀርብ ክስ የዲስፕሊን ጥፋቱ በተፈጸመ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል። ፲፫ሺ፭፻፶፩ ፫/ በከባድ የዲስፕሊን ጥፋት ላይ የሚቀርብ ክስ የዲስፕሊን ጥፋቱ በተፈጸመ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል። Limitation 1/ The procedure and how disciplinary proceedings are conducted shall be governed by a Directive to be issued by the Board; 2/ Charges brought in violation of non serious disciplinary rules shall be barred if not brought in one year from the date of the commission of the misconduct; 3/ Charges brought in violation of serious disciplinary rules shall be barred if not brought in two years from the date of the commission of the misconduct.
፩/ በዲስፕሊን ጉባዔው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን የዲስፕሊን ጉባዔው ውሳኔ ግልባጭ በደረሰው በሰላሳ ቀናት ውስጥ ለቦርዱ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። ፪/ የይግባኝ ክርክር ሂደት በመደበኛው የወንጀል ይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት አግባብ ይመራል። ፫/ በቦርዱ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን የሕግ ስህተት አለ ብሎ ካመነ የቦርዱ የውሳኔ ግልባጭ በደረሰው በሰላሳ ቀናት ውስጥ ይግባኙን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል። 1/ A party who has grievance against the decision of the Discipline Committee may lodge an appeal to the Board within Thirty days of receiving the copy of the decision; 2/ The proceedings of an appeal shall be governed by the regular criminal appeal procedure; 3/ A party who has grievance over the decision of the Board for mistake of law may apply to the Federal High Court within 30 days of receiving the copy of the decision.
በዚህ አዋጅ መሠረት የሚያስቀጡ የዲስፕሊን ጥፋቶች የወንጀል ድንጋጌዎችን ፍሬ ነገሮች የሚያሟሉ ከሆነ ጠበቃው ወይም የጥብቅና ድርጅቱ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ ይቀጣል። ፲፫ሺ፭፻፶፪ An advocate who or a law firm which has committed an act under the provisions of this Proclamation shall be punished by the relevant criminal law provided that such acts fulfills the ingredients of the crime.
፩/ በዚህ አዋጅና በአዋጁ መሠረት በሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት በከባድ የዲስፕሊን ጥፋት የተቀጣ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጥፋተኛነት ሪከርድ እንዲሰረዝለትና ሥሙ እንዲመለስለት መጠየቅ ይችላል። ፪/ የመሰየም አቤቱታ የሚቀርበው ለዲስፕሊን ጉባዔ ሆኖ አቤቱታው ሊቀርብ የሚችለው ቅጣቱን ከጨረሰ ከሁለት ዓመት በኋላ ነው። 1/ An advocate or a law firm who or which is punished for serious violation of disciplinary rules as provided under this Proclamation, Regulations and Directives to be issued there under, shall have the right to apply for reinstatement and his or its name deleted from the register of disciplinary measures; 2/ A reinstatement application shall be submitted to the Discipline Committee two years after the completion the disciplinary measure.
፩/ አመልካች ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የመሰየም አቤቱታውን ለዲስፕሊን ጉባዔው ያቀርባል፤ ፪/ የዲስፕሊን ጉባዔውም አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይም ሌላ የሚመለከተው አካል በአቤቱታው ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ፫/ የዲስፕሊን ጉባዔውም የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይም የሚመለከተውን አካል አስተያየት ከተቀበለና አመልካቹን በአካል በማነጋገር አስፈላጊውን ምርመራ ካደረገ በኋላ ጥፋቱ ከሪከርድ እንዲሰረዝ ሊወስን ይችላል። ፲፫ሺ፭፻፶፫ 1/ The advocate or a law firm seeking a reinstatement shall submit his/its application to the Discipline Committee; 2/ The Discipline Committee, if it finds it necessary, shall refer the application to the Attorney General or other concerned body for its opinion on the application; and 3/ The Discipline Committee may strike the disciplinary measure record from the register after, physically interrogating the applicant and receiving the opinion of the Attorney General or the concerned body and due examination of the case.
፩/ አመልካቹ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጥፋተኛነት ሪከርድ ይሰረዝለታል። ፪/ ሪከርዱ በማናቸውም ዓይነት ውሣኔ ላይ አይጠቀስም፤ ፍቃዱ ተሰርዞበት ከሆነ ለደረጃው የሚሰጠውን ፈተና ተፈትኖ ካለፈ እና በዚህ አዋጅ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ ፍቃዱ ይመለስለታል። ፫/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) ድንጋጌ ቢኖርም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፭ ንዑስ አንቀጽ (፳፩) - (፳፬) ሥር በተደነገጉት ከባድ የዲስፕሊን ጥፋቶች ምክንያት የጥብቅና ፍቃዱ የተሰረዘበት ወይም በእነዚሁ ድርጊቶች በወንጀል የተቀጣ፤ ወይም ከሚሰጠው የጥብቅና አገልግሎት ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል የተቀጣ፤ ወይም ታስቦ በሚፈጸም እና ከአስር ዓመት ጽኑ እስራት በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የተቀጣ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የተሰየመ ቢሆንም የጥብቅና ፍቃዱ አይመለስለትም፣ በጥብቅና አገልግሎት ሙያ ድጋሚ መሰማራት አይችልም። ፲፫ሺ፭፻፶፬ 1/ The record of the discipline measure taken against the applicant advocate or law firm shall be removed from the register; 2/ The record shall not be mentioned in any kind of decision; if his/its advocacy license was revoked, it shall be returned, on condition of taking the professional competency exam given to his class of license and satisfies the requirements of this Proclamation; 3/ Notwithstanding the provisions of Sub- Article (2) of this Article, any advocate or a law firm whose license was revoked for violation of serious disciplinary rules provided under Sub- Articles (21) – (24) of Article 85; or one who is punished for violation of the criminal law for similar acts; or one who is punished for violation of the anti- corruption law related with the advocacy service he renders; or one who is found guilty and punished for intentional crimes punishable by ten years or more rigorous imprisonment shall not get back his license and engage in advocacy service thereafter.
የዲስፕሊን ጉባዔው አንድ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት እንዲሰየም ሲወስን ጠበቃው ወይም የጥብቅና ድርጅቱ ጉባዔው ለሚወስነው ጊዜ ያህል ነፃ የማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ጉባዔው ለሚወስናቸው ጉዳዮች መጠን ያህል ነፃ የሕግ አገልግሎት እንዲሰጥ ሊያዝ ይችላል። When the Discipline Committee decides on the reinstatement of an advocate or a law firm, it may order the reinstated advocate or law firm, for a specified period, to render free public service and pro bono advocacy service.
መሰየምን የሚመለከቱ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በከባድ የዲስፕሊን ጥፋት ለተቀጡ ጠበቆችም ተፈጻሚ ይሆናል። The provisions of this Proclamation related with reinstatement shall also apply to advocates who had been punished for violation of serious disciplinary rules before the coming in to force of this Proclamation.
በቀላል ጥፋት የተቀጣ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የመሰየም አቤቱታ ማቅረብ ሳያስፈልገው ቅጣቱን ከጨረሰ አንድ ዓመት በኋላ ሪከርዱ ይሰረዝለታል ወይም ቀሪ ይደረግለታል። Disciplinary violations The record of an advocate or a law firm, who was punished for violation of non- serious disciplinary rules shall be removed or cancelled from the register after one year without the need for him or it to lodge an application for reinstatement.
ማንኛውም ከኢትዮጵያ ውጪ ካለ እውቅና ካለው ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው እና የጥብቅና ፍቃድ እንዲሰጠው የሚያመለክት ሰው የዲግሪውን አቻ ግምት በሚመለከተው አካል አሰርቶ ማቅረብ አለበት። ፲፫ሺ፭፻፶፭ ፺፯. ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም ደንብ ሊያወጣ ይችላል። ፪/ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ ቦርዱ እና ማኅበሩ በዚህ አዋጅ የተሰጣቸውን ሥልጣን እና ተግባራት ለማስፈጸም የሚያስችላቸውን መመሪያ ሊያወጡ ይችላሉ። Anyone who has got first degree in law from a recognized foreign Higher Education Institution and is applying for grant of advocacy license shall bring Equivalence Evaluation of his degree from a concerned organ.
1/ The Council of Ministers may issue Regulations for the implementation of this Proclamation; 2/ The Attorney General, the Board, and the Association may issue Directives to exercise the powers and duties assigned to each of them in this Proclamation.
፩/ ቦርዱ እና ማኅበሩ በዚህ አዋጅ መሠረት የተሰጣቸውን ተግባር እና ኃላፊነት በሁለት ዓመት ውስጥ ይረከባሉ። ፪/ ቦርዱ እና ማኅበሩ ኃላፊነታቸውን እስኪረከቡ ድረስ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በነባር ሕጎች መሠረት የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር ሥራን ይቀጥላል። ፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፸፬ ላይ የተመለከቱትን ለቦርዱ ተጠሪ የሆኑትን የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴ እና የጠበቆች ዲስፕሊን ጉባዔ ተጠሪነት ማኅበሩ እነዚህ ኃላፊነቶች ለመረከብ ብቁ መሆኑን ቦርዱ ሲወስን በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁለቱንም ወይም ከሁለቱ አንዱን ወደ ማኅበሩ ያስተላልፋል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማኅበሩ እነዚህን ኃላፊነቶች በአግባቡ ስለመወጣቱ ይከታተላል፣ አስፈላጊ ነው ብሎ ያሰበውን እርምጃ ይወስዳል ወይም የሚመለከተው አካል እንዲወሰድ ያደርጋል። ፲፫ሺ፭፻፶፮ ፬/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፸፬ ላይ የተመለከተውን ለቦርዱ ተጠሪ የሆነውን የጥብቅና ፍቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ ማኅበሩ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት ብቁ በሚሆንበት ጊዜ ተጠሪነቱ ለማኅበሩ እንዲተላለፍ ቦርዱ በማንኛውም ጊዜ ሊወስንና ሊያስተላልፍ ይችላል። ፭/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፹፪ ንዑስ አንቀጽ (፩)- (፬) እና (፮) ላይ የተመለከቱ ተግባራት ማኅበሩ ተደራጅቶ እና ኃላፊነቶቹን መረከብ እንደሚችል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሲያረጋጥ ኃላፊነቶቹን ሁሉንም ወይም የተወሰኑትን መመሪያ በማውጣት ወደ ማኅበሩ ሊያስተላልፍ ይችላል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እነዚህን ኃላፊነቶችን ካስተላለፈ በኋላ ተግባራቱ በአግባቡ ስለመፈጸማቸው መከታተል እና ኦዲት የማድረግ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ ወይም እንዲወሰድ የማድረግ ኃላፊነት አለበት። ፮/ ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮች ይህ ሕግ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ጸንተው በነበሩት ሕጎች መሠረት ውሳኔ ያገኛሉ። 1/ The Board and Association overtake within two years the power and duties provided to them as per this Proclamation. 2/ The Attorney General shall continue to manage the business of licensing and administration of the advocacy service until the Board and the Association, pursuant to this Proclamation, overtake their responsibility; 3/ The Accountability of both or one of the Advocacy Profession Entrance Qualification Exam Committee and Advocates Discipline Committee that are provided in Article 74 of this Proclamation shall be transferred to the Association within five years, when the Board decides the Association is capable of receiving these duties. The Attorney General follows up whether the Association performs these duties properly; takes or make other concerning organ to take appropriate measure; 4/ The Board may decide and transfer at any time the accountability of the Advocacy License Evaluation Committee provided in Article 74 of this Proclamation to the Association, when the Association is capable of performing the duties. 5/ When the Attorney General confirms the Association is organized and capable of receiving duties, it may transfer by enacting Directives, the whole or some of duties provided under Article 82 Sub- Articles (1) - (4) and (6) of this Proclamation. After transferring these duties, Attorney General shall follow-up and audit whether these duties properly performed; as well as take or make other concerning organ to take appropriate measure; 6/ Cases pending before the coming into force of this Proclamation shall be decided in accordance with the then valid laws.
፩/ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፍቃድ እና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር ፩፻፺፱/፩፱፻፺፪ በዚህ አዋጅ ተሽሯል። ፪/ ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ ወይም የአሠራር ሥርዓት በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም። ፲፫ሺ፭፻፶፯ 1/ The Federal Courts Advocates Licensing and Registration Proclamation No.199/2000 is hereby repealed. 2/ Any Proclamation, Regulation, Directive, or practice which is inconsistent with this Proclamation shall not be applicable on matters covered under this Proclamation.
፩/ በፌደራል ፍ/ቤቶች ጠበቆች ፍቃድ አሰጣጥ እና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር ፩፻፺፱/፲፱፻፺፪ መሠረት የወጡ ደንብ እና መመሪያዎች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተቃረኑ እና በሌላ ደንብና መመሪያ እስከሚተኩ ድረስ ተፈጻሚነታቸው ይቀጥላል። ፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ላይ የተጠቀሱት ደንብ እና መመሪያዎች እስከሚሻሻሉ ወይም እስከሚሻሩ ድረስ እንደ አግባብነታቸው በጥብቅና ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ። Continue 1/ Regulations and Directives which were issued based on The Federal Courts’ Advocates Licensing and Registration Proclamation No.199/2000 shall continue to apply as long as they are not inconsistent with this Proclamation and replaced by other Regulations and Directives. 2/ The provisions of Regulations and Directives cited under Sub-Article (1) of this Article, until they are amended or replaced, shall, as the case may be, be applicable on law firms.
ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል። አዲስ አበባ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፪ሺ፲፫ ዓ.ም ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፲፫ሺ፭፻፶፰ This Proclamation shall enter in to force on Done at Addis Ababa on this 5th Day of August,2021 SAHLEWORK ZEWDE PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA
Choose an article to open it.