English
1/ A partner of a law firm shall have the
following rights:
a) the right to participate and vote in the
meetings of the firm;
b) based on his contribution, to share
profits of the firm or the proceeds of
liquidated assets of the firm at the
time of dissolution;
c) to get information about and follow
up the activities of the law firm;
d) get rights and benefits emanates from
the partnership agreement, this
Proclamation and other relevant laws
or other rights and benefits that
emanate from the nature of the firm;
2/ The partner of a law firm shall have the
following obligations:
a) pay the firm’s membership
contribution on time;
b) work diligently, at any time, to
materialize and achieve the purpose
of the law firm;
c) refrain from acts that may hamper
discharging his responsibilities and
activities that are detrimental to the
interests of the law firm, whether to
his personal benefit or not; and
d) Discharge his obligations provided in
the partnership agreement, in this
Proclamation, other relevant laws or
obligations indicated by the
partnership agreement or emanate
from the nature of limited
partnerships.
አማርኛ
፩/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪክ የሚከተሉት መብቶች
አሉት፡ሀ) በጥብቅና ድርጅቱ ስብሰባዎች የመካፈል
እና ድምጽ የመስጠት፣
ለ) በድርሻው መጠን ከጥብቅና ድርጅቱ
ትርፍ ወይም የጥብቅና ድርጅቱ ሲከስም
ከተጣራው የማኅበሩ ሀብት ከሚተርፈው
ሀብት የመካፈል፤
ሐ) የጥብቅና ድርጅቱን አጠቃላይ አሠራር
የመከታተል፣ የማወቅ፤
መ) በሽርክና ስምምነት፣ በዚህ አዋጅና
አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች
የተመለከቱ፣ ወይም ከሽርክና ማኅበሩ
ተፈጥሮ የሚመነጩ ሌሎች መብቶችና
ጥቅሞችን የመጠቀም።
፪/ የጥብቅና ድርጅት ሸሪክ የሚከተሉት
ግዴታዎች አሉበት፡ሀ) ለጥብቅና ድርጅቱ መክፈል
የሚጠበቅበትን መዋጮ በወቅቱ
መክፈል፣
ለ) በማናቸውም ጊዜ የጥብቅና አገልግሎት
ድርጅቱን ዓላማ ለማሳካት በትጋት
የመሥራት፣
ሐ) ለራሱ ጥቅም የሚያስገኝ ቢሆንም
ባይሆንም የጥብቅና ድርጅቱን ጥቅም
ከሚጻረሩ ድርጊቶች ወይም ኃላፊነትን
ከሚያጓድሉ ተግባራት መታቀብ፣ እና
፲፫ሺ፭፻፲፮
መ) በሽርክና ስምምነት፤ በዚህ አዋጅ፣
አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች፣
በሽርክና ስምምነት የተመለከቱ ወይም
ከሽርክና ማኅበሩ ተፈጥሮ የሚመነጩ
ሌሎች ግዴታዎችን የመወጣት።