English
1/ Any advocate or law firm has the
obligations to perform his or its
advocacy service honestly and in a
manner that ensures loyalty to justice;
2/ Without prejudice to the general
provision provided under Sub-Article
(1) of this Article, any advocate or law
firm has the duty, not to unduly delay
cases without good cause; not to
organize false witnesses; not to produce
false evidence or cause such evidence to
be produced; appear before the court
duly prepared and make competent
arguments; reject cases which have no
cause of action and legal basis; keep the
confidentiality of his client’s
information and respect other similar
codes of conduct;
3/ Other similar codes of conduct related
with advocates’ conduct that are
initiated by the Attorney General, Board
or Association, are prepared by the
Attorney General and determined by a
Regulation to be issued by the Council
of Ministers.
አማርኛ
፩/ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት
የጥብቅና አገልግሎት ሥራውን በታማኝነት
የመስራትና ለፍትሕ አጋር የመሆን ግዴታ
አለበት።
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ጠቅላላ
ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ጠበቃ
ወይም የጥብቅና ድርጅት ያለበቂ ምክንያት
ጉዳይን ያለማጓተት፣ ምስክሮችን በሀሰት
ያለማደራጀት፣ ሀሰተኛ ማስረጃ ያለማቅረብ
ወይም ያለማስቀረብ፣ ተዘጋጅቶ የመቅረብና
ተገቢውን ክርክር የማድረግ፤ የሕግ መሠረት
የሌለውንና የማያዋጣ ጉዳይን ያለመያዝ፤
የደንበኛውን ወይም ባለጉዳዩን ምስጢር
ያለማውጣት እና ሌሎች መሰል የሥነምግባር ግዴታ አለበት።
፲፫ሺ፭፻፫
፫/ ሌሎች መሰል ከጠበቃ ሥነ-ምግባር ጋር
የተያያዙ ግዴታዎች በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣
በቦርዱ ወይም በማኅበሩ ሀሳብ አመንጪነት
በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል ተዘጋጅቶ
በሚኒስተሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ
የሚወሰን ይሆናል።