English
1/ Any person who wishes to join the
advocacy profession may obtain
advocacy license by fulfilling the
following requirements:
a) to be an Ethiopian national or a
foreign national of Ethiopian origin;
b) have a minimum of first degree in
law from a recognized Ethiopian
Higher Education Institution;
c) able to present a statement from his
most recent employer indicating that,
in his last two years of employment,
he had not been subjected to
measures for serious disciplinary
infractions and can produce proof of
good conduct; and
d) meet the work experience required in
the legal profession and pass any
qualification examination that may
be necessary to obtain advocacy
license.
2/ Notwithstanding Sub-Article
(1) Paragraph
(b) of this Article, any person
who received his first degree in law from
a recognized Higher education institution
abroad may be granted advocacy license
provided he fulfills the criteria set out
under Article 12 Sub-Article (2), Article 13 Sub-Article
(2) and Article 14 Sub-
Article
(2) of this Proclamation;
3/ A person who fulfills the requirements
provided under Sub-Article
(1) of this
Article shall present his application for
advocacy license along with necessary
documents, to the Attorney General.
4/ The result of any qualification
examination referred to in Sub-Article
(1) paragraph
(d) of this Article shall be
valid only if it is presented within a year.
አማርኛ
፩/ ማንኛውም በጥብቅና ሙያ መሰማራት
የሚፈልግ ሰው የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት
የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት
ይኖርበታል፡ሀ) የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ወይም
ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ፣
ለ) እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ
ትምህርት ተቋም ቢያንስ በሕግ
የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው፣
ሐ) ለመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት
ተቋም ድርጅቱን ከመልቀቁ በፊት
ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ
ዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ እና
የመልካም ሥነ-ምግባር ማረጋገጫ
ማቅረብ የሚችል፣ እና
፲፫ሺ፬፻፹፯
መ) በሕግ ሙያ የሚፈለገውን የሥራ ልምድ
ያሟላ እና እንደ አስፈላጊነቱ ፍቃድ
ለማግኘት የሚሰጠውን የሙያ መግቢያ
ፈተና ያለፈ።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ፊደል-ተራ
(ለ) የተመለከተው ቢኖርም ከኢትዮጵያ ውጪ
ካለ እውቅና ካለው የከፍተኛ ትምህርት
ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተሰጠው
ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪
ንዑስ አንቀጽ (፪)፣ አንቀጽ ፲፫ ንዑስ አንቀጽ
(፪) እና አንቀጽ ፲፬ ንዑስ አንቀጽ
(፪) ሥር
የተመለከተውን መስፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ
የጥብቅና ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ላይ
የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ
ማንኛውም ሰው አስፈላጊ ሠነዶችን በማያያዝ
የጥብቅና ፍቃድ ማመልከቻውን ለጠቅላይ
ዐቃቤ ሕግ ማቅረብ ይኖርበታል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ፊደል-ተራ
(መ) መሠረት የሚቀርበው የፈተና ውጤት
ዋጋ የሚኖረው ውጤቱ በታወቀ በአንድ
ዓመት ጊዜ ውስጥ ከቀረበ ብቻ ነው።