English
1/ The President shall manage the general
business of the Association and is
accountable to the General Meeting and
the Executive Committee;
2/ Without prejudice to the provisions of
Sub-Article
(1) of this Article, the
President shall have the following
powers and duties:
a) on behalf of the Association,
concludes contract, sue, defend;
appoint an advocate, to represent the
Association, who brings an action or
defends the Association or defends
the interests of the Association in
similar matters; appoint the
employee of the Association or a
third party to represent the
Association as may be necessary;
b) prepare and submit, to the Executive
Committee, the annual activity plan,
budget, performance and financial
reports;
c) prepare draft Directives necessary for
the functions of the Association and
implement same when approved by
the General Meeting;
d) hire and administer the employees
of the Association based on the
Human Resources Manual of the
Association;
e) perform the activities of the
Association and represent the
Association in its relation with third
parties in accordance with the
Directive given to him by the
Executive Committee;
f) follow up the implementation of the
decisions of the General Meeting and
the Executive Committee;
g) perform other tasks assigned to him
by the General Meeting and the
Executive Committee.
3/ The Vice President of the Association:
a) act on behalf of the President when
he is absent or unable to discharge
his duties and responsibilities;
b) perform other tasks assigned to him
by the Executive Committee or the
President.
አማርኛ
፩/ ፕሬዚዳንቱ አጠቃላይ የማኅበሩን ሥራ
የሚመራ ሆኖ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔው
እና ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይሆናል።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሬዚዳንቱ የሚከተሉት
ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡-
፲፫ሺ፭፻፴
ሀ) ማኅበሩን ወክሎ ውል ይዋዋላል፣ ይከሳል፣
ይከሰሳል፣ ማኅበሩ በሚከስበት፣
በሚከሰስበት ወይም በሌላ ተመሳሳይ
የሕግ ጉዳይ ማኅበሩን ወክሎ የሚቀርብ
ጠበቃ ይወክላል፣ የማኅበሩን ጉዳይ
ማስፈጸም እንዲችል የማኅበሩን ሠራተኛ
ወይም ሶስተኛ ወገን እንደ አስፈላጊነቱ
ይወክላል፤
ለ) የማኅበሩን ዓመታዊ እቅድ፣ በጀት፣ የሥራ
ክንውን እና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ
ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያቀርባል፤
ሐ) ለሥራ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን
ረቂቅ ያዘጋጃል፣ በሥራ አስፈጻሚው
ኮሚቴው ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
መ) በማኅበሩ የሰው ኃይል አስተዳደር
መመሪያ መሠረት የማኅበሩን
ሠራተኞች ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፤
ሠ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በሚሰጠው
መመሪያ መሠረት የማኅበሩን ሥራዎች
ያሰራል፤ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ባለው
ግንኙነት ማኅበሩን ይወክላል፤
ረ) የጠቅላላ ጉባዔና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
ውሳኔዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን
ይከታተላል፤
ሰ) በጠቅላላ ጉባዔውና በሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት
ያከናውናል፡
፲፫ሺ፭፻፴፩
፫/ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት፡ሀ) ፕሬዚዳንቱ በማይኖሩበት ጊዜ ወይም
ሥራውን ሊሰራ በማይችልበት ጊዜ
ተክቶ ይሰራል፤
ለ) በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወይም
በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች
ተግባራት ያከናውናል።