English
1/ Any Ethiopian citizen or a foreign
national of Ethiopian origin who fulfills
the following requirements shall be
granted the All Federal Courts
Advocacy License:
a) has graduated with first degree in
law from a recognized Ethiopian
Higher Education Institution and has
a minimum of five years of
professional experience in the field
of law;
b) as may be necessary, has passed the
entrance qualification examination
set for the particular type of
advocacy license;
c) produces evidence, from his
immediate past employer, that
certifies he had not been subjected to
disciplinary measures for violation
of serious misconduct in the two
years prior to departure; and
d) Produce a certificate of good conduct
from his immediate past employer.
2/ Notwithstanding the provisions of Sub-
Article
(1) paragraph
(a) of this Article,
All Federal Courts Advocacy License
may be granted to a person who
graduated with a first degree in law
from a recognized foreign higher
education institution if he has a
minimum of seven years of professional
experience in the field of law in
Ethiopia and fulfills the other
requirements listed under Sub-Article
(1) of this Article.
አማርኛ
፩/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ
ኢትዮጵያዊ የፌደራል ማናቸውም ፍርድ
ቤት የጥብቅና ፍቃድ ይሰጠዋል፡ሀ) እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ
ትምህርት ተቋም በሕግ ትምህርት
የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው እና በሕግ
ሙያ ቢያንስ የአምስት ዓመት ልምድ
ያለው፣
ለ) እንደ አስፈላጊነቱ ለደረጃው የሚሰጠውን
የጥብቅና ፍቃድ መግቢያ ፈተና ያለፈ፣
ሐ) ለመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት
ተቋም ድርጅቱን ከለቀቀበት ጊዜ በፊት
ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ
ዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ፣ እና
መ) መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ስለመሆኑ
ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
፲፫ሺ፬፻፺፫
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ፊደል-ተራ
(ሀ) ሥር የተመለከተው ቢኖርም ከኢትዮጵያ
ውጪ ካለ እውቅና ካለው ከፍተኛ ትምህርት
ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው
ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ
ሙያ ለሰባት ዓመት ካገለገለ እና ሌሎች
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ሥር
የተመለከቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ
የፌደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና
ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል።