English
1/ Where there are reasonable grounds to
believe that a computer crimeis to be
committed and it is necessary to prevent
and control the crime, provide early
warning to citizens, to minimize the risks
or for effectiveness of the investigation,
the Agency, in collaboration with the
investigatory organ, and upon court
warrant, may conduct sudden searches,
conduct digital forensic investigation,
provide appropriate security equipment or
take other similar measures on computers,
computer systems or infrastructures that
are suspected to be attacked or deemed to
be the sources of attack.
2/ For the implementation of the provision
of sub-article
(1) of this Article,as may be
necessary and upon request, concerned
organs shall have duty to cooperate.
አማርኛ
፩/ የኮምፒዩተር ወንጀል ሊፈፀም እንደሚችል በቂ
ጥርጣሬ ሲኖር እና ጥቃቱን ለመከላከልና
ለመቆጣጠር፣ ዜጎችን አስቀድሞ ለማስጠንቀቅ፣
የምርመራ ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ወይም
የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ኤጄንሲው ከመርማሪ
አካላት ጋር በመተባበር እና ከፍርድ ቤት ፈቃድ
በማውጣት የጥቃት ሰለባ ወይም መነሻ ሊሆኑ
እንደሚችሉ በተጠረጠሩ ኮምፒውተሮች፣
የኮምፒዩተር ሥርዓቶች ወይም መሠረተ ልማቶች
ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ወይም የዲጂታል ፎረንሲክ
ምርመራ ሊያካሂድ፣ ተስማሚ የሆነ የደህንነት
መሳሪያ ወይም አገልግሎት ሊያቀርብ ወይም ሌላ
መሰል ማንኛውንም እርምጃ ሊወስድ ይችላል።
፪/ ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ተፈፃሚነት
አስፈላጊ ከሆነ እና ጥያቄ ከቀረበ
የሚመለከታቸው አካላት የመተባበር ግዴታ
አለባቸው።