English
1/ Whosoever fraudulently causes a person to
act in a manner prejudicial to his rights or
those of third person by distributing
misleading computer data, misrepresenting
his status, concealing facts which he had a
duty to reveal or taking advantage of the
person’s erroneous beliefs, shall be
punishable with rigorous imprisonment not
exceeding five years and fine not
exceeding Birr 50,000.
2/ Whosoever, with fraudulent intent of
procuring any benefit for himself or for
another person, causes economic loss to
another person by any change, deletion or
any other damage of computer data shall
be punishable with rigorous imprisonment
not exceeding five years and fine from Birr
10,000 to 50,000 or in serious cases with
rigorous imprisonment not exceeding ten
years and fine from Birr 10,000 to 100,000.
አማርኛ
1/ ማንኛውም ሰው አሳሳች የኮምፒዩተር
ዳታዎችን በማሰራጨት፣ የራሱን ማንነት
ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ
የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን
ሰው የተሳሳተ እምነት በመጠቀም፣ ሌላውን
ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን
ማንኛውም ጥቅም የሚጎዳ ድርጊት
እንዲፈጽም ያደረገው እንደሆነ ከአምስት
ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከብር
፶ሺ በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል።
2/ ማንኛውም ሰው በተጭበረበረ መንገድ
የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው
ለማስገኘት የኮምፒዩተር ዳታን በመለወጥ፣
በማጥፋት ወይም ሌላ ማንኛውም ጉዳት
በማድረስ በሌላ ሰው ላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት
ያደረሰ እንደሆነ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ
ጽኑ እስራት እና ከብር ፲ሺ እስከ ብር ፶ሺ
በሚደርስ መቀጮ ወይም ወንጀሉ ከባድ በሆነ
ጊዜ እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ
እስራት እና ከብር ፲ሺ እስከ ብር ፩፻ሺ
በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።