English
Without prejudice special provisions
stipulated under other laws,
1/ to prevent computer crimes and collect
evidence related information, the
investigatory organ may, request court
warrant to intercept in real-time or conduct
surveillance, on computer data, data
processing service, or internet and other
related communications of suspects, and
the court shall decide and determine a
relevant organ that could execute
interception or surveillance as necessary.
2/ Sub-article
(1) of this Article shall only be
applicable when there is no other means
readily available for collecting such data
and this is approved and decided by the
Attorney General.
3/ Notwithstanding the provisions of sub-
article
(1) and
(2) of this Article, the
Attorney General may give permission to
the investigatory organ to conduct
interception or surveillance without court
warrant where there are reasonable
grounds and urgent cases to believe that a
computer crime that can damage critical
infrastructure is or to be committed.
4/ The Attorney General shall present the
reasons for interception or surveillance
without court warrant under sub-article
(3) of this Article to the President of the
Federal High Court within 48 hours, and
the president shall give appropriate order
immediately.
5/ Any irrelevant information collected
pursuant to sub-articles
(1) to
(4) of this
Article shall be destroyed immediately
upon the decision of the Attorney General.
6/ Any service provider shall cooperate when
requested to carry on activities specified
under sub-articles
(1) and
(3) of this
Article.
7/ Without prejudice sub-article
(5) of this
Article, any information collected in
accordance with this Article shall be kept
confidential.
አማርኛ
በሌሎች ሕጎች የተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች
እንደተጠበቁ ሆነው፣
፩/ የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል እና
õሺíÿ÷
ለምርመራ መነሻ የሚሆኑ መረጃዎችን
ማሰባሰብ ተገቢ ሆኖ ሲገኝ የተጠርጣሪዎችን
በኮምኒዩኬሽን ሂደት ላይ ያለን የኮምፒዩተር
ዳታ፣ የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት ወይም
የኢንተርኔት እና ሌሎች መሰል ግንኙነቶችን
እንዲጠለፍ ወይም ክትትል እንዲደረግበት
መርማሪ አካል ለፍርድ ቤት ጥያቄ ሊያቀርብ
ይችላል። ፍርድ ቤቱም ተገቢውን በመወሰን
እንዳስፈላጊነቱ ጠለፋው ወይም ክትትል
የሚደረግበት ሁኔታ እና ትዕዛዙን
የሚያስፈፅመውን አካል ይወስናል።
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ
ተፈፃሚ የሚሆነው በሌላ አኳኋን ዳታውን
ማሰባሰብ የማይቻል ሲሆን እና ይኸው
በጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ተቀባይነት አግኝቶ
ሲወሰን ብቻ ይሆናል።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) እና
(፪) የተደነገገው ቢኖርም በቁልፍ መሰረተ ልማት
ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የኮምፒዩተር
ወንጀል ስለመፈፀሙ ወይም ሊፈፀም ስለመሆኑ
በቂ ጥርጣሬ ሲኖር እና አስቸኳይ ሁኔታ
ሲያጋጥም ጠለፋው ወይም ክትትሉ ያለፍርድ
ቤት ትዕዛዝ እንዲከናወን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ
ለመርማሪ አካል ሊፈቅድ ይችላል።
4/ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ በዚህ አንቀጽ ንዑስ
አንቀጽ
(፫) መሰረት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ
ለመጥለፍ ወይም ለመከታተል መነሻ የሆኑትን
ምክንያቶች በ፵፰ ሰዓት ውስጥ ለፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ማቅረብ
አለበት፤ ፕሬዚዳንቱም ተገቢውን ትዕዛዝ
ወዲያውኑ መስጠት ይኖርበታል።
፭/ በዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ
(፩) እስከ
(፬) መሠረት የሚገኝ ማንኛውም መረጃ ለጉዳዩ
አግባብነት ከሌለው በጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ውሳኔ
ወዲያውኑ መወገድ አለበት።
õሺíÿ÷í
፮/ ማንኛውም አገልግሎት ሰጭ አካል በዚህ
አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፩) ወይም ንዑስ
አንቀጽ
(፫) የተደነገገውን ለማካሄድ ሲጠየቅ
አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ አለበት።
፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(፭) የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አንቀጽ መሠረት
የሚሰበሰብ ማንኛውም መረጃ በምስጢር
መያዝ አለበት።